Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday, 22 September 2012

የአቶ መለስ መቃብር በልዩ ሁኔታ እየተጠበቀ ነው…………..ከፍኖተ ዘመቻ ነጻነት “እናሸንፋለን” we will win (www)



አስከሬኑ ከነሰንደቅ ዓላማው መቀበሩ አነጋጋሪ ሆኗል


አራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የተቀበሩት የኢፌዲሪ / ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ መቃብር ልዩ ጥበቃ እየተደረገለት እንደሆነ ተገለፀ፡፡
ምንጮቻችን እንደሚሉት አቶ መለስ ከተቀበሩ በኋላ ባልተለመደ ሁኔታ የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በሮች የተቆለፉ ሲሆን መቃብሩ በተለየ ኃይል ልዩ ጥበቃ እየተደረገለት ነው፡፡ የመረጃ ምንጮቹ ጨምረው እንደገለፁት ከቀብሩ በኋላ በወክማ ወይም በመንፈሳዊ ኮሌጁ አቅጣጫ ያለው በር ሙሉ በሙሉ ተቆልፎ የሚውል ሲሆን ቀን ቀን በዋናው በር ወደ ቤተክርስቲያኑ የሚገባ ካለ የት እንደምሄድ ለምን መግባት እንደፈለገ ተጠይቆ ከታመነበት ብቻ እንደሚገባና ሲገባና ሲወጣም ከትትል ይደረግበታል፡፡

ምሽት ላይ የዋናው በር የሰው መግቢያ ብቻ የሚከፈት ሲሆን በርካታ ሰው ለፀሎት የሚገባ ቢሆንም የአቶ መለስ የቀብር ቦታ በልዩ ጥበቃ እየተጠበቀ ነው፡፡ በቀብሩ ዕለት አስክሬኑ የለበሰው የሰሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ አብሮ መቀበሩ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ቅሬታን የፈጠረ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ትርጉም እየተሰጠው ይገኛል፡፡ ሰንደቅ ዓላማ ከአስክሬን ጋር ይቀበራልን በማለት የጠየቅናቸው አንዳንድ ሰዎች በሰጡን አስተያየትየኢህአዴ መንግስት በአገር ሰንደቅ ዓላማ ላይ ሲፈጽም ከቆየው ጥፋት አሁንም አለመላቀቁን ያሳየበት ነው፡፡ የአንድ ሉዓላዊ አገር ባንዲራ አይቀበርም፡፡

ሰንደቀ ዓላማ ከማንም በላይ ነው፡፡ ማንም ይሙት ማን የአገር ባንዲራ አብሮ የሚቀበርበት ህግ የለም፡፡ ታሪካዊ ወንጀል ተፈጽሟልሲሉ ተችተዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አቶ መለስ ከሁለት ወር በላይ ያሉበት ሁኔታ አለመታወቅና ሞቱ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ አስክሬናቸው እንደ አንድ የአገር መሪ በግልጽ በመስታወት አለመታየቱ በህብረተሰቡ ዘንድ አነጋጋሪ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እደሚሉት ኢህአዴግ የአቶ መለስን መታመም ለብዙ ጊዜ ደብቆን ቆይቷል፡፡ ሞቱ ብሎ ከነገረን በኋላ ህክምናቸውን ሲከታተሉበት የነበረውን ሆስፒታል ደበቀ፡፡ የህክምና ማስረጃቸውንም ይፋ አላደረገም፡፡ከዚህም አልፎ ተርፎ
አስክሬናቸውንም አላሳየንም፡፡ ከተቀበሩም በኋላ አስክሬኑን አሁን ባለው ሁኔታ መጠበቅ ለምን አስፈለገ ከአስክሬኑ ሳጥን ጀርባ ምን ሚስጥር አለ?” በማለት ያላቸውን ጥርጣሬ ገልፀዋል፡፡

በተለይ የመቀሌ ነዋሪዎች የአቶ መለስ አስክሬን አለመታየት በግልጽ ሚስጥሩ ምንድ ነው የሚል ጥያቄ አንስተው እንደነበረ የመረጃ ምንጮቻችን ከሥፍራው ገልፀዋል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አዘጋጆች በቀብሩ እለት በሥፍራው ተገኝተው የቀብሩን ሥነ ሥርዓት እንዳይዘግቡ በመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች የተከለከሉ በመሆናቸው በሥፍራው ተገኝተው መዘገብ አልቻሉም፡፡ ከቀብሩ በኋላም በህዝብ የሚነሱትን ጥያቄዎች ለማጣራት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

No comments:

Post a Comment