Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday, 24 October 2012

ከሚሴ በልዩ ሁኔታ በፌደራል ፖሊሶች ተወራለች


ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ ከሚሴ አካባቢ በፌደራል ፖሊሶች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መከበቦን ነዋሪዎች ገለጡ::
ከከሚሴ ኢሳት ሬዲዮ ያናገረው አንድ ሙስሊም እንደገለጠው የአካባቢው ሰዎች በግዴታ ስብሰባ እንዲያደርጉ ተጠርተው ሽብር ፈጥራችኋል፤ ከዚህ ተግባራችሁ ታቀቡ ያለበለዚያ ግድያው ይቀጥላል ብለው እንዳስፈራሯቸው ገልጠዋል::
ከትላንት በስቲያ በገርባ ፖሊሶች በሰላማዊ መንገድ ሰላማዊ ጥያቄ ባነሳው የሙስሊሙ ህዝብ ላይ ተኩስ ከፍተው ሁለት ሰው ከገደሉና ሌሎችን ካቆሰሉ በሆላ የተፈጠረው ውጥረት እንደቀጠለ መሆኑን የገለጡልን የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ጥያቂያቸው መልስ እስካላገኘ ድረስ ተቃውሞቸውና ጥያቄያቸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል::
ከተለያዩ ቦታዎች በዳፍ መኪኖች የተጫኑ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊሶች በከሚሴና በደሴ አካባቢ እየገቡ መሆናቸውን የገለጹልን ምንጮቻችን፤ በወታደርና በመሳሪያ ጋጋታ ጥያቂያችንን ለማፈን የሚደረገው ጥረት አይሳካም ብለዋል::
በመንግስት ተይዘው የታሰሩ የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት እንዲፈቱን ጨምሮ የተለያዩ ጥያቄዎች ይዘው የተነሱት ሙስሊሞች ጥያቄቸውን በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ማሰማት ከጀመሩ ወራቶች ያለፉ ሲሆን፤ በተለይ ከትላንት በስቲያ በሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ የመንግስት ወታደሮች የወሰዱት የግድያ እርምጃ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የዜና ሽፋን እየሰጡት ይገኛል::
በዚህ መሰረት የእሁዱን ግድያ ከዘገቡት መሀከል ቺካጎ ትሪቡን ኒውስ ቱዌኒ ፎር እና ኦል አፍሪካ ይገኙበታል::

No comments:

Post a Comment