Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Sunday 21 October 2012

የአቶ በረከት ሚስት .....By: Asress M.

እየሩሳሌም አርዓያ በመባል የሚታወቅ ጸሃፊ ሰሞኑን በኢትዮ ሜዲያ ድረ ገጽ “ከፖለቲካ ፍጥጫው በስተጀርባ” በሚል ርእስ በጻፈው ጽሁፍ ባሁኑ ሰዓት በህውሃት እና በብአዴን መካከል እየጦፍ ያለውን የበላይነት ፉክክር በተለይም አቶ በረከት በሚመሩት እነ ወይዘሮ አዜብ መስፍንን ጄነራል ሰአረ መኮንን ቴዎድሮስ ሃጎስ ተፈራ ዋልዋ አዲሱ ለገሰን እንዲሁ ጠቅላይ ሚንስትሩን ሃይለማርያም ደሳለኝን ባቀፈው ቡድንና በተቃራኒው ደግሞ በነስብሃት ነጋ በኩል ስዩም መስፍን፣ ሃይለኪሮስ ገሰሰ፣ አባዲ ዘሞ እና ቢተው በላይን ባቀፈው ቡድን መካከል ያለውን የቡድን ፖለቲካዊ ፍጥጫ እና ሴራ አስነብበውናል:: ስለዚህ የፖለቲካ ፍጥጫ እና ሴራ መረጃ ስሌለለኝ የምለው የለኝም ::

እኔን የገረመኝ ጸሃፊው የአቶ በረከት ሚስት ወይዘሮ አሰፉ ከወይዘሮ አዜብ ጋር በሙስና መጨማለቅ መጀመሯን በጨረፍታ አንስቷል በመቀጠልም የአቶ በረከት ሚስት ወይዘሮ አሰፉ ህውሃትን አጥብቃ እንደምትጠላ እና በተደጋጋሚ ይህን አቋሟን በይፋ ስታንጸባርቅ መታየቷን ጠቅሷል:: ይህንንም ጽሁፍ ኢሳት በድረ ገጽ ዳሰሳው አቅርቦታል:: በውነቱ ጸሃፊው ያልተገነዘቡት ነገር ባሁኑ ሰዓት ህውሃትን በይፋ አጥብቆ የሚጠላ ሰው እንዴት ነው በሰላም አስመጭና ላኪ ሆኖ ንግዱን ሊያጧጡፍ የሚችለው? ለምን ይዋሻል? ጸሃፊው የአቶ ስብሃትን ቡድን በመደገፍ የአቶ በረከት ሚስት ህውሃትን ትጠላለች በማለት አዜብ መስፍንን ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና ቴዎድሮስ ሃጎስን ከነበረከት ቡድን እንዲርቁና ወደ አቶ ስብሃትን ቡድን እንዲቀላቀሉ ከሆነ ይንገረን በግለጽ ካለበለዚያ ግን ሁሉን አውቃለሁ ባይል ይሻለዋል:: በግሌ የአቶ በረከትን ባለቤት አውቃቸዋለሁ በፍጹም አቶ እየሩሳሌም አርዓያ እንደሚላቸው አይነት ሰው አይደሉም:: ይልቁንም ወይዘሮ አሰፉ በኢህዴን (የአሁኑ ብአዴን) ውስጥ ከናታቸው ከወንድሞቻቸው እና ከእህቶቻቸው ጋር የትግሉ መስራች በመሆን የታገሉ እና ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉ ናቸው:: በትግሉም ግዜም ታጋይ እህታቸውን በጦር ሜዳ በሞት የተነጠቁ በመጨረሻ በድሉ ማግስት አብዛኛዎቹ የታገሉት እህትና ወንድሞቻቸው በህውሃት ተገፍተው ከስልጣንም ከሃብትም ባዶ እጃቸውን አጨብጭበበው የቀሩ ናቸው:: 


እንደሚታወቀው በዘመነ ኢሃዴግ ማናቸውም የብአዴን ሆነ የኦህዴድ ባለስልጣናት ሚስቶች ይቅርና እራሳቸው የብአዴን እና የኦህዴድ ባለስልጣናት ምንም አቅም የላቸውም:: ማንኛዋ የብአዴን ወይም የኦህዴድ ባለስልጣናት ሚስት ናት ህውሃትን በግልጽ መጥላቷ እየታወቀ ከዱባይ አዲስ አበባ ያለቀረጥ ንግዷን የምታጧጥፍ?

ባጠቃላይ የአቶ በረከትን ብአዴንን እና ኦህዴድን የአማራው እና የኦሮሞው ህዝብ ሲሰደድ ሲታሰር ሲሰደብ ሲዋረድና እና ሲገደል እያዩ አንድም ቃል ሳይተነፍሱ 20 አመት ሙሉ ህውሃትን በመፍራት ተለጣፊ በመሆናቸው ልንወቅሳቸው ይገባል:: ነገር ግን ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ ሊጻፍላቸው የሚገባ የሙስና እናቶች እያሉ ታግለው እንዳልታገሉ በህውሃት ተገፍተው ከስልጣንም ከሃብትም ባዶ እጃቸውን አጨብጭበበው ስለቀሩት ሳያጣሩ መዘባረቅ ያስተዛዝባል::

No comments:

Post a Comment