ላልተከተለ ጋሻውን ለማንሳት
ላልደፈረ የተዜመ ዜማ ነበረ። የቀድመዋ ቀዳማዊት እመቤት ባለቤት አቶ መለስ ዜናዊ አዜብ መስፍንን በፓራላማቸው
ላይ ‘ቆራጥ ታጋይ’ ሲሉ አወድሰዋቸው ነበር።የዳኛ ብርቱካን መዴክሳ በታጋይነታቸው ሰማቸው በኢትዮጵያዊያ ዘንድ
እየገነነ መምጣቱ፤ የባለቤታቸውን ታጋይነት ሰለአጠላበት ነው በቁጭት የተናተሩት ያሉም ነበሩ። የወያኔ ተጋዳዮችም
ቀዳማዊት እመቤትን እንደ ( Popular Front for Liberation of Palestine) ‘የፍልስጤም
ሕዝባዊ ነፃነት ግንባር’ አባል የሆኑትን የእውቋንና ዝነኛዋን ሌዕላአ ካህሌድ (Leila Khaled) እንደ አስራ
አምስተኛው ምዕተ ዓመት ዝነኛ ፈረሳዊት ጅግኒት የካቶሊክቱ ቅድስት ጆኖ ኦፍ አርክ (Joan of Arc) ጋር
ያመሳስሏቸዋል። በተለይ ራሳቸው ላይ ጣል የሚያደርጓት ሻሽ መሰል ኮታ ቁርጥ ሌዕላአ ካህሌድን አስመስሏቸዋል።
(AK 47) ክላሽስኮብ ይዘው ፎቶ ተነሰተው በኢቲቪ ባለመቅረባቸው ጅግንነታቸው አልታወቀም።አፈሩን ገለባ
ያድርግላቸውና ባለቤታቸው ቢሆኑ የአርጀቲናዊን ማርክሲስት ቼ ኮቬራ (Che Guevara) መለያው የሆነችውን ቆብ
ደፋ ያደርጉ ነበር። ይህ ከውጪ የተጨለፈ የትግል ስልት ‘የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር’ (ሕውሃትን) ፈጥሮልናል።
በቅርቡ የድርጅቱ መስራች አቦ ሰባት ነጋም እንደነገሩን ትግራይን ለማስገንጠል ሣይሆን የአማራውንና የኦርቶዶክ
ሃይማኖት ተከታዩን የኢትዮጵያ ሕዝብ አከርካሪ ለመስበር መሆኑን ነው።
ይህ ሁኔታ በልጅነቴ የሚነገር
ተረት አስታወሰኝ። ጦጢት ሰው የሚያደርገውን በመኮረጅና መስሎ ለመታየት በምታደርገው ተግባሯ ትታወቃለች ።
በዕውቀት ደከም ያሉትን የሕብረተሰቡን ክፍል በማታለልም ወደር የላትም። በተለይ የገበሬውን ምርት አታላ በመብላት
ሌሎች እንሰሳት አይደርሱባትም። የሚያሸንፋት ተማሪ ብቻ ነው ተብሎ ይነገራል። ከዕለታት አንድ ቀን ተማሪው ጦጢት
ወደአለችበት በመሄድ ከምታየው ከፈተኛ ሥፍራ ላይ ቆሞ፣ ቢላዋ አንስቶ፣ በደነዙ በኩል ማጅራቱ ከገዘገዘ በኋላ
ቢላዋውን ይወረውርላታል፤ ጦጢትም ቢላዋውን አንስታ በደመ ነፍስ በስለቱ በኩል ማጅራቷን ትገዘግዛለች ፣ ደሟ
ሰዥረዥር፣ እሪ ብላ ትጮሃለች፤ ተማሪው ሊረዳት ቢሞክርም ወደ ዱሯ ትነጉዳለች ። ይህ የጦጢት ታሪክ አዲሱንም
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝንም ይመለከታል።
ወደ ዋናው ወደተነሰሁበት አርዕሰት ልመለስ፤
በተጋዳይ አካባቢ የሚፈከረው መፈክር ‘ጓድ ቢሞት ጓድ ይተካል’ ነውና ወይዘሮ አዜብ መስፍን የሟቹን ባለቤታቸውን
ጋሻ አንስተዋል። አነሳሳቸው ስዕላዊና ታሪካዊ ነው። አለባበሳቸው ጥቁር በጥቁር ነው፤ የትግል ጉዞቸውን ለማያውቁ
ለባላቸው ሐዘን የለበሱት ነው ብለው በየዋህነት ሊገምቱ ይችላሉ። ጥቁሩ መስከረም( Black September)
(Leila Khaled) ሌዕላአ ካህሌድ አባል የሆነችበት የፍልስጢም ድርጅት አርማ ነው። ታጋይቱ በዚህ ዓይነት
አለባበስ ይታወቃሉ። በታጋይ ነኝ አለባበስ ቀዳማዊት እመቤት በቲቪ መስኮት ብቅ በማለት ‘መለስ የትግራይ ክልል
በኢንዱስትሪ ለማሳደግ የነደፈውን ጹሑፍ ስላለ ያንን በሥራ ላይ አውላለሁ’ ብለውን እርፍ አሉት። ይታያችሁ አዜብ
መስፍን የፓርላማ አባል ናቸው። ባለቤታቸውም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመባል ነበር የሚታወቁት፤ መግለጫቸውን
ስንሰማ የትግራይ ብቻ ተጠሪ ሆኑ ብለን አዘንን። በባለቤታቸው የቀብር ሥነሥረዓት ላይ ‘ከኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ
ሐብት የለንም’ ብለውን ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሥልጣን ስላጡት ወደ ትግራይ ኮበለሊ ያሉም አሉ።ሌሎች
እንደሚሉት የተመረጡበትን ፓርላማና አዲስ የተሾሙትን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ላይ ጦርነት ማወጃቸው
ነው የሚሉም አልጠፉም።
ያም ሆነ ይህ አዋጃቸውን በቁምነገር ወስደነው የትግራይ ክልል በኢንዱስትሪ አድጎ
‘በትግራይ የተሠራ’ የሚል ዕቃ በገዛን ባልከፋን ነበር። ከሃያ ዓመት ቀደም ብሎ ቢያንስም ቢያድግም ለፍጆታ
የሚስፈልጉንን ቁሳቁሶች ማምረት ችለን ነበር። ዛሬ ግን ለወጥ ማማሳያ፣ ለቡና መቁያ፣ ለምግብ ማብሰያ፣
የምንለብሳቸው ልብሶችና ጫማዎች ሳይቀሩ በቻይና የተሠሩ ናቸው። ይህን ያየ በአገራቸን በሆነ ክልል ውስጥ ዕቃዎች
ቢመረቱ፣ ጥጃ ጠባ ሆድ ገባ ነበር።ግን ቁምነገሩ ያ! አይደለም። ለትግራይ ሕዝብ ሲዋሽለት የነበረውን የመገንጠል
አጀንዳ ፉርሽ መሆኑ ነው። በትግራይ ማስገንጠል ስም ለኤርትራ መገንጠል፣ በመቶ ሺ የሚቆጠር የትግራይ ወጣት አውደ
ጦርነት ላይ ተማግዷል። አቶ
ስባት ነጋ ‘አማራውንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዩን አኮታኩተነዋል’
እንደሉትም አይደለም። በመቶ ሺዎች ያለቁበትም ባድሜ የትግራይ ክልል ሆኗል ሲባል፤ ሐቁ የኤርትራ መሆኑ ነው።
በሕውሃት ወያኔ መሪነት ያጣነው የባሕር በር እስከዘለቄታው እንደማናገኘው በቅርቡ በረከት ስምዖን በአደባባይ
ግልጽ አድርጎታል። ትግራይን በኢንዱስትሪ የማሳደጉ ውዥንብር ይህን ሁሉ ጥፋት ይሸፍነው ይሆን? የአልሞት
ባይ ተጋዳዮች የጥቂት የትግራይ ጉጄሌዎች ማወናበጃና ጊዜ መግዣ እንጅ ፋይዳ ያለው ነገር አይደለም። ኢንዱስትሪ
በትግራይ ውስጥ ለምን ተገነባ ብሎ እንቅልፍ አጥቶ የሚያድር ኢትዮጵያዊ የለም።
በትግራይ ሕዝብ ነፃነት
ግንባር ስም በመላው ሃገሪቱም ሆነ በትግራይ ሕዝብ የተፈጸመው ግፍ ታሪክ ሲያወሳው የሚኖር ነው።ዙሪያ ጥምጥም
ከሚሄድ ይልቅ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ያቆራረጡትን ቆምንለት የሚሉትን የትግራይን ሕዝብ በአደባባይ ይቅርታ ይጠይቁት።
ኢንዱስ
ትሪው ይቋቋም ቢባል እንኳን ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከኢፈርት ገንዘብ ወጪ፣ አድርገው ነው ወይስ ከክልሉ ግብር
አስከፍለው? ከመላውየኢትዮጵያ ሕዝብ እንደይሉ ፓርላማው አልመከረበትም፤ ያም ግልጽ አልሆነም። እያደር እንደሚታየው
ወይዘሮ አዜብ በዋናነት የሚቆጣጠሩትን የኢፈርት ንብረት የራሳቸው አድርገው ከሆነ ያ ሌላ ነው። ወታደር ሊቀጥሩበት
ይችላሉ። ኢንዱስትሪ የተባለው ሽፋን ነው። በአሁን ጊዜ በወያኔ አምባ የሚታየው መደነባበር እንጂ ልማት አይደለም።
ወይዘሮ አዜብስ ቢሆኑ የትኛው ብቃታቸው ነው? ኢንዱስትሪ ለማቋቋም የሚረዳቸው? ከአጥፍቶ መጥፋቱ አዝማሚያ
ተቆጥበው፣ የባለቤታቸውን ሐዘን በወግ ቢወጡት ይሻላል።በለቅሷቸው ላይ ‘አልጋው ባዶ ነው’ እንደሉት የሉምና
ካልጋዎ ወርደው ሰሌን አንጥፈው ማቅ ለብሰው መጸለዩ ባህላዊም ሃይማኖታዊም ነው። ከእንግዲህ ምን ዓለም አሎት?
ግማሽ አካሎን አተዋል፤ ከዋልድባ ገዳም ቆብ ደፍተው መመልኮሱ ይብዛቦ? ወልቃይት ጤገኔም ቢሆን የአባቶ ሃገር
ነው፤ግን ‘ ሰው ከሚጠጣው ወኃ ምራቁን አይተፋም’ በማለት ያማርሮታል፤ የዋልድማው ገዳም ጉዳይ ገና
አልተቋጨም።የኢትዮጵያ ሕዝብም ቢሆን አዝኖቦታል። ከገንዘብ ዘረፋው እስከ ቡቃቅላ ወጣት ሴት ልጆቹን ለአረብ አገር
ማሻገሩን እንደባሪያ ፈንጋይነት ቆጥሮታል።
የሚያነሱት ጋሻ የገንዘብ ፍቅርን፣ የእርኩስ መንፈስን፣ የሥልጣን ጥማትን የሚመክት መሆን አለበት።
ኢትዮጵያንና ልጆቿን ዓምላክ ይታደጋቸው። አሚን!
ታደለ መኩረያ
tadele@shaw.ca
tadele@shaw.ca
No comments:
Post a Comment