Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 21 November 2012

የኢቲቪ ጋዜጠኞች ቤትና ንብረት በእሳት ቃጠሎ ወደመ

በየማነ ናግሽ (Reporter)
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በተለምዶ ፍላሚንጎ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ሦስት የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋዜጠኞች መኖርያ ቤትና ንብረት በእሳት ቃጠሎ ወደመ፡፡ ከትናንት በስቲያ ጠዋት ሁለት ሰዓት ገደማ የተነሳው ይኼው የእሳት ቃጠሎ መንስዔ ያልታወቀ ሲሆን፣ የሁለት ጋዜጠኞችን ቤትና ንብረት ሙሉ ለሙሉ ሲያወድም የሦስተኛው ጋዜጠኛ ንብረት በከፊል ሊድን ችሏል፡፡ በአጠቃላይ በመቶ ሺዎች ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡

ጋዜጠኞቹ ደባስ ባይለየኝ፣ በቀለ ተመስገንና ኢትዮጵያ በዲቻ ሲባሉ፣ እሳቱ የተነሳው ብቻውን ከሚኖረው ከኢትዮጵያ በዲቻ ክፍል ነው ተብሏል፡፡ እሳቱ ሦስቱ ጋዜጠኞች የሚኖሩበትን የመንግሥት ቤት ሙሉ ለሙሉ ሲያወድም፣ አጠገቡ ወደሚገኘው አቢሲንያ ሆቴልና ሌሎች ቤቶች እንዳይዛመት በአካባቢ በነበሩ ፖሊሶችና ነዋሪዎች ርብርብ መከላከል መቻሉ ታውቋል፡፡

ቁጥራቸው እስከ ስድስት መቶ የሚገመት ነዋሪዎች ተረባርበው ቃጠሎውን ሲያጠፉ፣ በአካባቢው የሚገኙ ፖሊሶችም ከነዋሪዎች ጋር በመሆን እሳቱን ለማጥፋት ሲንቀሳቀሱ ተመልክተናል፡፡ ነዋሪዎቹንም ምሥጋናቸውን ችረዋቸዋል፡፡

ከመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ፖሊሶች ቀድመው ሲደርሱ፣ በአካባቢው የሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማና የፌዴራል ፖሊሶችም ተቀላቅለው እሳቱን ለመከላከል ችለዋል፡፡ በቦታው አግኝተን ያነጋገርናቸው ምክትል ሳጅን አንቺአየሁ ብርሃኑና ሳጅን ሱንዱቅ አብዱልቃድር ይህንኑ አረጋግጠውልናል፡፡

ነዋሪዎቹ የእሳት ቃጠሎውን በማጥፋት ላይ ሳሉ ዘግይቶ የደረሱት የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ኤጀንሲ ሠራተኞች በነዋሪዎቹ ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶባቸዋል፡፡ ስልክ ከተደወለ አንድ ሰዓት ያህል ዘግይተው መድረሳቸው በነዋሪዎች ተነግሯቸዋል፡፡ ፖሊሶችም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡ ዘግይተው ደረሱ የተባሉት የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች በመጥፋት ላይ የነበረውን እሳት ጨርሰው ማጥፋት የቻሉ ሲሆን፣ ይህን ያህል ጊዜ ለምን እንደዘገዩ ላቀረብንላቸው ጥያቄ የመንገድ መዘጋጋትን በምክንያትነት አቅርበዋል፡፡ ፖሊሶቹ ግን ከዚህ በፊትም በአካባቢው ተመሳሳይ አደጋ ደርሶም ዘግይተው መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡

በየአካባቢው የእሳት አደጋ መከላከል ጣቢያ እንዲኖር ሲያስቡ የነበሩ አንዳንድ ነዋሪዎች፣ ‹‹የሠፈሩ ሰው ባይኖር’ኮ አልቀናል ነው የሚባለው›› ሲሉ ቅሬታቸውን ለድርጅቱ ሠራተኞች አቅርበዋል፡፡

No comments:

Post a Comment