Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday, 21 April 2012

ጠቅላይ ሚንስትሩና ንቀታቸው!!........... (ተሻገር ምትኩ)

ጠቅላይ ሚንስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት የሰጡትን ንግግር በሃፍረት ተሞልቼ ከጎደኞቼ ጋር ሳየው ቆየሁ። በሚገርም ሁኔታ ያሳፍራል። እንዴት ኣንድን ሃገር በሃላፊነት መራለሁ ከሚል ግለሰብ እንደዛ አይነት የወረደ ንግግር ይደመጣል? ያው እኔም እሱ የፈጠረኝ ትውልድ ስለሆንኩ ያሉት ባይገርመኝም እንዴት አንድ ሰው በ 20 አመት ውስጥ እራሱን ጠብቆ መናገር ያቅተዋል? እኛ አማሮች ላይ ያሉት ላይ እመለስበታለሁ ግን በትንሹ ስለኣስተማሪዎች የተሰጠውን አስተያየት ስላናደደኝ ትንሽ ልበል። እዚህ ላይ አንድ ነገር ካላልኩ በጣም እወዳቸው የነበሩትን አስተማሪዎቼን የማዋርድ ስለመሰለኝም ጭምርም ነው።
አስተማሪዎች የተከበሩና ትውልድ ለመቅረጽ የሚጫወቱትን ሚና ለኣንባቢ በማስረዳት ማሰልቸት ኣልፈልግም። ግን እንበልና (ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት) ከብዙ ሺ አስተማሪዎች ጥቂቶች መጥፎ ናቸው እንበል። እነዛ ግን በደካማነታቸው ስንት ሰው ጎድተዋል? 10 ሰው? 100 ሰው? 1000 ሰው? ምናልባተም በ አስር ሺዎች እንበል። ጠቅላይ ሚንስትሩና የሳቸው ጠባብ ፖሊሲ ኣንድ ትውልድ ደምስሶ ሁለተኛውን እያደነቆረ እንደሆነ አያውቃሉ? እሳችው ደካማ ሚልዋቸው አስተማሪዎች ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚሉትን ሰምተዋል? እንደሰማሁት ከሆነ ማይክራፎን ብዙ ግዜ ሲይዙ መስማት ይከብዳል ሲሉ እንጅ እስካሁን እውነት አልመሰለኝም ነበር።
ስለኛ አማሮች ደሞ ሲያወሩ ፡ ያው የለመደባቸውን ቤት ያፈራውን ከፋፍለህ ግዛን ሊጠቀሙብን የሞከሩ ይመስላል። ሲናገሩ “ምስራቅ ጎጃም” የሚለወን ቃል መጠቀማቸው ሌሎች አማሮች አፋችሁን ዝጉ ነው? ወይስ ጉዳዩ ጠቃላላ ኢትዮዽያዊያንን አይመለከትም ለማለት ነው? ያንን እንደወም እንደንቀትና ድፍረት ያዩ ፡ አማራው መደራጀት አለበት ብለው እየገፉበት ይገኛሉ። ስላልተደራጀን አንጠቃለን ሲሉን የነበሩትን ወንድሞቻችንን አሁን ጆሮቻንን ከፍተን መስማት ጀምረናል። ጠ/ሚንስትሩ ሚሉት በጣም ይገርማል ፡ የጉራ ፈርዳን አካባቢ አማሮች ምስራቅ ጎጃም አደረጉት የሚሉን ፣ ከ አንድ አካባቢ የመጡ ህዝቦች በመብዛታቸው የተነሳ የአራት ኪሎ ቤተመንግስቱንና አንዳንድ የ አዲስ አበባን ኣካባቢዎች የምኖች ሰፈር እየተባሉ እንደሚጠሩ ያውቃሉ?
የሰሞኑን የ ጠ/ሚንስትሩን ንግግር ወትሮው እንደምናደርገው ከ ጏደኞቼ ጋር አብረን ስንከታተለው ነበርን። በየጊዜው ስለሀገራችን ፖለቲካና ስለተለያዩ ጉዳዮች ተገናኝተን ምንወያይበት ሻይ ቤት (ኮፊ-ሀውስ) ተቀምጠን ሳለን ጏደኞቼ የተለመደውን ስድብና ዘለፋ ይሄ ሼባ ምናምን እያሉ ጠ/ሚንስትሩን ስብእና የሚነኩ ነገሮች ሲናገሩ ፡ ሁልግዜ ስራ በዝቶባቸው ነው እያልኩ እንደምከራከርላቸው ከትላንት በስትያ ግን ቃል ሳልተነፍስ ነገሩን ሳዳምጥ ቆየሁ። እንዴት ስራ አይብዛባቸው? በዚች ጉዳይ ላይ አስቡት እስቲ ፡ እራሳቸው መርማሪ ፖሊስ ፣ ከዛም አባራሪ ፖሊስ ፣ ባለሙያ ፍርድ ሰጪ(ወረቀት እጨርሳለሁ እንጂ ዝርዝሩ አያልቅም) እያለ ይቀጥላል። እናም እነዢህ ጏደኞቼ ሲያብጠለጥሉዋቸው “ይሄ ሼባ ጉራፈርዳን ምስራቅ ጎጃም አደረጉት ሚለን ሰሜን ጎንደርን ከነ ካርታው የምን ይዞታ አደረጉት እየተባለ እንደሚወራ አልሰማም እንዴ?” እያሉና የተለያየ ነገር በማንሳት ከፍ ዝቅ ሲያደርጉዋቸው አመሹ። ወጣትነት ጥሩ ነው። ከ ጠ/ሚንስትሩ ሚፈልቁትን የወረዱ ሃሳቦች ወይንም በትምህርት አለዛም በእድሜ የማስተካከል እድሉ አለን።

ይብላኘ ለሳቸው። እኛ ውጣቶች እንደውም ካስፈለገን የ አምስት አመት የ ስብእናና ውርደትን የመከላከል
ትራንስፎርሜሽን እቅድ አውጥተን 11 ፐርሰንት እድገት አክለንበት ምናሳካው ይመስለኛል።
በሰሞኑ የ ህዝብ ንግ ግር ላይ ጠ/ሚንዝትሩ ያለማፈር እንደዛ ሲተረተሩ እንዴት ከኔና ከኔ ትውልድ ጥሩ
ነገር ሊጠበቅ ይቻላል? ይሄ ሁሉ ውሸት አይናቸውን በጨው ኣጥበው ሲዋሹ እኔዴት ቢንቁን ነው? ከሱም
ብሶ አጎንብሶ አለ የሃገረ ሰው። ጠ/ሚንስትሩ ብሄራዊ ሆነው እኛ አማሮች ተነካን ስላልን ጎጠኞች ተብለን
የተፈረጅነው በየትኛው ስሌት ንው? እኔምለው ጠ/ሚንስትሩ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠረውን የኢትዮዽያ
ህዝብን ትተው በጥቂት ሚልዮን እንደውም ወርደው በመንደርና አካባቢ ተደራጅተው ስልጣ ላይ
መፈናጠጣቸውን ረሱት እንዴ? አልፈው ተርፈው ኢትዮዽያን እያስተዳደርኩ ነው እያሉን ዞር ብለው
የዛው ኣናሳ ስብስብ መሪ ሆነው እስከዛሬ ህዋሀትን እያስተዳደሩ እንዳሉ ዘነጉት እንዴ? ያም ሆነ ይህ
አይደለም በ ፓርላማ ፊት ቢወራጩ ነጠላ ዘቅዝቀው እያለቀሱ ቢነግሩንም ምናምናቸው ከመሰላቸው
አዝንላቸዋለሁ። እወነቱን እናውቃለን። እናም ያባረረ ቢረሳም የተባረረ አይረሳም!!!

እኔን ለማግኝት ከፈለጉ ፡ teshagermitiku@yahoo.com በሚለው አድራሻ እገኛለሁ።

No comments:

Post a Comment