“ያለውን” በመቅበር የሌለውን በመጥራት የሚታወቀው የጥቁር ራስ ስብስብ የሆነውን “ማህበረ ቅዱሳን” በጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲሁም በቤተ መንግሥት አከባቢ የታየውን ድንገተኛ ክስተት አጥፍቼም ብሆን እጠፋለሁ እንጅ ይህን ወለል ብሎ የተከፈተ በርስ ሳልጠቀመት አያልፈኝም!የሚል
ሞፈክር አነግቶ በሀገሪትዋ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንደቀዳዳ በማየትና ቀዳውን በማስፋት በዚህ ማኸልም ሸልኮ
በመውጣት ያልተጠራበት ዙፋን ለመጠቅለል በስውርም በይፋም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቀን ከሌሊት ሴራውን እየሸረበና
እየዶለተ እንደሚገኝ ምንም አያጠያይቅም።
ባሳለፍነው ሳምንት ሽብርና ህውከት በሚነዛባቸው መካነ ድሮቹ አመካኝነት “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የት ነዎት?“ሲል ሳይጠራ አቤት ሳይላክ ወዴት አንደማለት ያልተጠየቀውን ሲያመናታ ሲሳለቅ በሌላውኛው እጁ (በህጋዊው ድረ ገጾቹ) በኩል ደግሞ “ቤተ ክርስቲያንና የፓትርያርክ ምርጫ” በሚል ርእስ ቀደም ሲል ማኅበሩ አሁን በሚጥራበት “ማኅበረ ቅዱሳን” የሚለው
ስያሜ ከመያዙ በፊት አጠቃላይ ጉባኤ ተብሎ ይታወቅበት በነበረበት ዘመን ገድሎ የቀበራቸው ፓትሪያሪክ ቴዎፍሎስ
እንዲሁም ያለ አንዳች ተጨባጭ ማስረጃ ርዕሰ መናፍቃን በማለት የሚወቅሳቸውን ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ አሁን ደግሞ ሆን
ብሎ “ቀድሞም በእግዚአብሔር ፈቃድ ያልተሾሙ ናቸው” ሲል በመዋቹ ቅዱስ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ምትክ መንበሩ የሚገባው ለፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ ነው! የሚል ከየአቅጣጫው እየገፋ እየመጣ ያለውን የአብያተ ክርስቲያናት ድምጽና ለቤተ ክርስቲኒቱ ሰላም: ለተከታዮችዋ ምእመናን ደግሞ አንድነትንና ፍቅር በብርቱ የሚሹ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ምልከታ ለማሳጣት ብሎም ዕርቀ ሰላሙንም ለማደናቀፍ ይህን አደረገ።
“ከእኛ ፓትርያርኮች ሁለቱ ከምንኩስና አንዱ ከአጠቃላይ ጳጳስ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ሀገረ ስብከታቸውን ትተው የተሾሙ ናቸው። እነዚህም አቡነ ቴዎፍሎስና አቡነ መርቆሬዎስ ሲሆኑ በጣም የሚያስገርመው በእነዚህ በሁለቱም ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ፈተናዎች ከማስተናገዷም በላይ የሁለቱም ዘመነ ፕትርክናቸው አጭር ነበረ። ለራሳቸውም ሆነ ለቤተክርስቲያኒቱ ጥቁር ነጥቦች የተቀመጡትም በእነርሱ ዘመን ስለሆነ ከትውፊት መውጣታችን ባናስተውለውም እግዚአብሔር አምላካችን አልፈቅድላችሁም ያለን ይመስላል።”1
ልብ ይበሉ!ይህ የማህበሩ (“የማህበረ ቅዱሳን”) የአቋም ማሳያ ጽሑፍ ፓርቲያሪክ መርቆሪዮስ ወደ ቀድሞ መንበራቸው እንዳይመለሱ አመጽን የሚቀሰቅስ: በሀገር ቤት ያለውን ጉባኤም በመዋቹ ቅዱስ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ምትክ ከመካከሉ መርጦ ሌላ እንዲሾም የሚገፋፋናብሎም በቤተ ክርስቲያኒቱ መካከል የማይበርድ ጸብና ሁከት ለማንገስ ጨርሶ ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ የሚባል የለም! በማለት ሲመታቸውን በመግፈፍ የፕትርክና ማእረጋቸውንም እንደማይቀበል ቁልጭ ባለ አገላለጽ እመነቱን ግልጽ አድርገዋል። አሁን ማህበሩ ለማስተላለፍ የፈለገው የአመጽ መልዕክቱን አንድ በአንድ እንመልከታለን።
በጣም የሚያስገርመው በእነዚህ በሁለቱም ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ፈተናዎች ከማስተናገዷም በላይ የሁለቱም ዘመነ ፕትርክናቸው አጭር ነበረ” እንዲል ከዚህ ቀደም በሰነድ የተደገፈውን ሐተታዬ ላይ በስፋት እንዳስነበብኩት ይህ መሰሪ ማህበር የኢህዴግን መንግስት ለማስመታትና ለማስጠቆር ሲፈልግ: ወደ
ምዕራቡ ዓለም የከተሙ ወደ ተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉ ኢትዮጵያውያን መሃከልም የተገኘ እንደሆነ በመንታ ምላሱ
ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ በሃይል ተገፍተው ከመንበራቸው እንደተነሱ ምስክርነቱ ሲሰጥና ሲያምታታ አሁን የራሱ አጀንዳ
ላይ ሲደርስ ደግሞ ይሄው በማያሻማ ቋንቋ ይቅር እውነትም የተገፉና የተሰደዱ አባት ናቸው በማለት ሊያዝንላቸው ከዛሬ
ነገ ወደ ቀድሞ መንበራቸው ይመለሳሉ በሚል መረኑ የለቀቀ ፍራቻ ተውጦ የሚይዘው የሚጨብጠው አጥቶ ፓትሪያሪክ
ቴዎፍሎስ ጨምሮ ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስን የቤተ ክርስቲያን ነቀርሳ ነበሩ ሲል ገሲገልጻቸውና በጠራራ ጸሐይ ዘመቻ ሲከፍትባቸው እየተመለከትን ነው።
ማህበሩ በዚህ አልተመለሰም ”የሁለቱም ዘመነ ፕትርክናቸው አጭር ነበረ” እንዲል ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያትም ይላል “ማህበረ ቅዱሳን” የፓትሪያሪክ ቴዎፍሎስ በግፍ መገደልና የፓትሪያሪክ መርቆርዮስ ከመንበራቸው መወገድ ማለት ነው የስልጣን ዘመናቸው አጭር የመሆኑ ምስጢር ባይገባን ነው እንጅ ማእረገ ጵጵስናቸውም ሆነ የፕትርክና ሲመታቸው ቀድሞውኑ ትክክለኛና መንፈሳዊ አለመሆኑ ነው እያለ ሰምተነውም ሆነ አንብበነው የማናውቀው ለእኛ ለቤተ ክርስቲያን ልጆችም ሆነ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንግዳ የሆነ ታሪክ ፈብርኮ እየተረከ ነው:: እንዲህ
ያለ ከስህተት ትምህርት ይልቅ የከፋ ታሪክን የመበረዝና የማዛባት እኩይ ምግባር ደግሞ እንዲሁ በዋዛ ፈዛዛ
የሚታለፍ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን አጽንዖት ሰጥታ ተገቢ የሆነ እርምጃ ትወስድ ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ለሚመልከታቸው
አካላት ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
ሌላው እውነት ለመናገር ያክል ከዚህ ስመ መንፈሳዊ የሰይጣን ማህበር “ከማህበረ ቅዱሳን” በቀር
ፓትሪያሪክ ቴዎፍሎስን በክፉ የሚያነሳ ገጥሞኝም አያውቅ። ገድሎ ቀብሮአቸው ሲያበቃ ዛሬም አጥንታቸው ላይ ቆሞ
ከመራገም የአለመባዘኑ ምስጢር እንደሆነ ማህበሩ ምን ያክል በእኝህ አባት ታሪክ የማይረሳው ትውልድ የሚሻገር የጽድቅ
ስራ ማለትም ፓትሪያሪክ ቴዎፍሎስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ስርዓትንና ሕግ በመቅረጽ: የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ መዋቅር
መልክና ወጥነት ያለው አሰራር በማስተዋወቅ ከዚህም አልፎ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተመጭዋትነት ተላቃ ራስዋን በመቻል
ካህናትዎችዋን የምትመግብበትን የልማት ተቋማትን በመገንባት ያደረጉትን ትውልድ የማይረሳው መልካም ስራና ያበረከቱትን
አስተዋጽዖ በአጠቃላይ በዘመነ ፕትርክናቸው ለኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የዋሉት ውለታ ዛሬም ድረስ ምን ያህል ማህበሩን እያቃጠለው እንዳለና እንደሚኖር የሚያመላክት ነው።
በመቀጠልም “ለራሳቸውም ሆነ ለቤተክርስቲያኒቱ ጥቁር ነጥቦች የተቀመጡትም በእነርሱ ዘመን ስለሆነ ከትውፊት መውጣታችን ባናስተውለውም እግዚአብሔር አምላካችን አልፈቅድላችሁም ያለን ይመስላል” እንዲል። እዚህ ላይ እንግዲህ ከወደ መግቢያዬ አከባቢ ጠቅለል ባለ መልኩ እንደገለጽኩት “ማህበረ ቅዱሳን” እንዲህ
ባለ ሰዓት ላይ እንዲህ ያለ ታሪክ ይዞ ለመምጣት የተገደደበት ዋና ምክንያትና በሚያሰራጨውም ወሬ አተርፋለሁ ብሎ
ያሰላውን ትርፍ ቀደም ሲል እንደተገለጸ የሃይማኖት መሪዎቹ ከነ ቅራኔአቸው ማዶ ለማዶ እየተያዩ እንዲኖሩና በዚህም ሂደት ውስጥ በሚያካሂዱት የእርስ በርስ መጎሻሸም እድሜዬን አራዝማለሁ ብሎ ስለሚያምን ነው።
ከዚህም የተነሳ “ከትውፊት መውጣታችን ባናስተውለውም እግዚአብሔር አምላካችን አልፈቅድላችሁም ያለን ይመስላል“ሲል በድፍረት የታጠረ ነውራም አነጋገሩ ፓትሪያሪክ ቴዎፍሎስም ሆኑ ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ ድሮም የተሾሙት “ትውፊት ተጥሶ ነበር” (እዚህ ላይ ስለየትኛው ኢትዮጵያዊ ትውፊት እያወራ እንዳለ ለራሱ እጹብ የሚያሰኝ ነው) በህገ ወጥ ወደ መንበሩ የወጡና የተሾሙ ናቸው በማለት በሃይማኖት መሪዎቹ መካከል ለረጅም ጊዜያት የዘለቀውን አለመግባባትና መለያየት መቋጠሪያ ለማበጀት በሚደረገው አስታራቂ ነጥብ ማካከል ጣልቃ በመግባት የቀድሞ ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ የሚለውን ወሳኝ አስታራቂና መግባቢያ ሃሳብ ተግባራዊ እንዳይሆን “ማህበረ ቅዱሳን” በዚህ ለንባብ ባሰራጨው የአቋም
ጽሑፉ ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ ተመስልሰው በመንበረ ፕትርክናው የሚቀመጡበት ምንም ዓይነት መንገድም ሆነ ምክንያት
የለም በማለት በማያገባውና በማይመለከተው የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት መሞገቱ ማህበረ
ምን ያህል አደገኛና የቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ የተከታዮችዋ ሰላም የማይፈልግ ጸረ ሰላም ሃይል ለመሆኑ በተጨባጭ
የሚያረጋግጥ ነው።
ስለሆነም በአርባና በሰማንያ ቀንህ ስመ ቅዱሳንና ስመ ፃድቃን እየሰጠች በጥምቀት የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን ያገኘህ ወንዶችም ሴቶችም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ በሙሉ: ይህ
ራሱ የቅዱሳን ማህበር በማለት የሚጠራ ነፈሰ ገዳይ ስመ መንፈሳዊ ድርጅት ከዕለት ወደ ዕለት እየገፋበት እየሄደ
ያለውን ቤተ ክርስቲያኒቱ የማፈራረስና የማውደም ዓላማውን እንዲሁም የጸረ ሰላምና አንድነት የሆነውን እኩይ
እንቅስቃሴው በመቃወም ከእውነት ጋር እንቆምና እንሰለፍ ዘንድ በድጋሜ በእግዚአብሔር ስም ጥርዬን አቀርባለሁ።
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል