Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 20 October 2012

ኢትዮጵያ በመልካም አስተዳደር ከአፍሪካ አገሮች 33ኛ ወጣች

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአፍሪካ ሀገራት የመልካም አስተዳደር ይዘትን የሚያጠናውና ደረጃ የሚያወጣው የ ሞ-ኢብራሂም ፋውንዴሽን ባወጣው የ2012 ሪፖርት፤ ኢትዮጵያ ከመቶ 47 ነጥብ በማግኘት 33ኛ ደረጃ መውጣቷን ይፋ አደረገ።
በትውልድ ሱዳናዊ፤ በዜግነት እንግሊዘዊ በሆኑት ቢሊዮኔር ዶ/ር ሞሀመድ ኢብራሂም የተቋቋመው ይህ ተቋም፤ የአፍሪካ ሀገራትን በተለያዩ ዘርፎች በመመርመርና በማወዳደር በሰጠው ደረጃ፤ ሞሪሸስ በ83 ነጥብ የአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ተመዝግባለች።
ኬፕ ቬርድና ቦትስዋና በ78 እና 77 ነጥብ በ2ኛና ሶስተኛ ደረጃ ሲከተሉ፤ ጋና ደቡብ አፍሪካና፤ ታንዛኒያ ከፍተኛ ነጥብ በማግኘት ከቀዳሚዎቹ 10 ሀገራት ውስጥ ተመድበዋል። ኢትዮጵያ በ32 አገራት ተበልጣ፤ 19 ሀገራትን ቀድማ፤ በ47 ነትብ 33ኛ ሆና ተቀምጣለች።
ይሁን እንጂ፤ የአህጉሩ አማካይ 48 ከመቶ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያ ያገኘችው ከአማካይ በታች ነው።
ሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን፤ በ4 ዋና ዋና ክፍሎች፤ 88 ንኡስ ርእሶች በመውሰድ በዝርዝር ባደረገው በዚህ ጥናት በህዝባዊ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ የተሰጠው ነጥብ ከመቶ 25 ነው። የአህጉሩ አማካይ፤ 45 ሆኖ ተመዝግቧል።
ሰብአዊ መብትን በተመለከተም በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ የተሰጠው ነጥብ 44 ሆኗል።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከአማካይ በላይ ያገኘችዉ በጾታ እኩልነት ሲሆን፤ በዚህም የአፍሪካ አማካይ 54 ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ያገኘችዉ 59 ከመቶ ነው።
በትምህርትና በጤና መስክ፤ ኢትዮጵያ ከ50 ነጥብ በላይ ያገኘች ቢሆንም፤ የአፍሪካ አማካይ በሆኑት 54 እና 66 ላይ መድረስ አልቻለችም።
ሀገሪቱ ለንግድ ያላት አመቺነትን በተመለከተ ያገኘችው ነጥብ 28 በመቶ ሲሆን፤ የአፍሪካ አማካይ 50 ሆኗል።
በመሰረተ ልማት ግንባታ ኢትዮጵያ ያገኘችው ነጥብ ከመቶ 33 ሲሆን፤ የአፍሪካ አማካይ 32 ሆኖ ተመዝግቧል።
በዶ/ር ሞሀመድ ኢብራሂም የተቋቋመው ሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን የአፍሩካ አገራትን የመልካም አስተዳደር ደረጃ እየገመገመ ባለፉት 6 አመታት ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ ከግርጌ አገራት ተርታ እንደተሰለፈች ቀጥላለች።

No comments:

Post a Comment