Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday 15 October 2012

ወ/ሮ ሚሚ ስብሀቱ ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ያላቸውን ድጋፍ ገለጡ

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሥነምግባር ችግር ከተባረሩ በኋላ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትዕዛዝ ያለጨረታ የደቡብ ክልል
መገኛኛ ብዙሃን የቴክኒክ ሥራን ተረክበው በአቋራጭ ከባለሃብት ጎራ የተቀላቀሉት ወ/ሮ ሚሚ
ስብሃቱ ፣ ዛሚ በተሰኘው ራዲዮ ጣቢያቸው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአጃቢ ጋዜጠኞች ጋር በመሆን ሲሟገቱ ውለዋል፡፡
ሰሞኑን የወጡ ጋዜጦች ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግስቱን ለአቶ ኃይለማርያም አላስረከቡም በሚል ያወጡትን ተከታታይ
ዘገባዎች የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ በሚለው ዝግጅታቸው ጋዜጠኞችን ሲተቹና እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል።
ወ/ሮ ሚሚ “እንዲህ ዓይነቱ ጥያቄ ከአዲሱ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ዳሳለኝ መጥቶ ከሆነ የሚያሳዝን ነው በማለት ተናግረዋል።የወ/ሮ አዜብ የቅርብ ጓደኛ የሆኑት ወ/ሮ ሚሚ በጋዜጦቹ የቀረበው ዘገባ እውነትነትን ሳይክዱ አርባ እና ሰማንያ ሳይወጣ፣ የጠ/ሚኒስትሩ ውለታ ሳይረሳ እንዴት እንዲህ ይጻፋል ከማለት አንስተው ደርጊቱ በጠ/ሚኒስትሩ ሌጋሲና ውርስ ብቻ ሳይሆን በቀጣዩ ልማት ላይ የተቃጣ አደጋ ነው በማለት ገልጸዋል።
በጋዜጦቹ ዘገባ ክፉኛ የተበሳጩት ወ/ሮ ሚሚና ባልደረቦቻቸው ” አንድ ጊዜ ቤተመንግስት መኖር ያን ያህል
የሚያጓጓ አይደለም ሲሉ የተደመጡ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጋዜጦቹ ጉዳዩን መዘገባቸው ከፍተኛ ድፍረት ብቻም
ሳይሆን ለአቶ መለስ ሐዘኑን የገለጸው ሕዝብን መናቅ ነው በማለት የቅስቀሳ ሥራ ለመስራት ሞክረዋል፡፡
ወ/ሮ ሚሚ ለጓደኛቸው ለወ/ሮ አዜብ ውለታ ለመመለስ በሚመስል ድምጸት ወግነው ነገሩን ሲያቀጣጥሉ የአዲሱ ተተኪ
ጠ/ሚኒስትር ደህንነት ጉዳይ ጨርሶ እንደማያሳስብ እና ጠዋትና ማታ በመንገድ መዘጋት ለሚንገላታው ሕዝብ ደንታ
እንደሌላቸው አሳይተዋል በማለት አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ጋዜጠኛ ለኢሳት ተናግሯል።
አቶ ኃይለማርያም ለደህንነት አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዲሰሩና እንዲሸማቀቁም እንዲሁም የመለስ ራዕይ፣ ሌጋሲ የሚሉ ቃሎችን በማስተጋባት ለመናገር መሞከራቸው በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በወ/ሮ አዜብ መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት ጥሩ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ጋዜጠኛው አክሎ ተናግሯል።
ወ/ሮ ሚሚ ጣቢያቸው ያን ያህል በሕዝብ ተደማጭ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ የቀጠሩዋቸውን ጋዜጠኞች ወርሃዊ ደመወዝ እንኩዋን ለመክፈል የማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸው ይታወቃል፡፡
ኢሳት ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግስቱን እንዲለቁ መጠየቃቸውን መዘገቡ ይታወሳል። በአገር ቤት ደግሞ ሰንደቅ የተባለው ጋዜጣ ተመሳሳይ ዘገባ አቅርቦ እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።

No comments:

Post a Comment