Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday, 17 October 2012

አስፈሪ የህወሃትና የወያኔ ደጋፊዎች የመነጣጠል ሴራ!!! (በኢዮብ ብርሃነ)

በአሁኑ ወቅት በባሕር ማዶ የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በአገራቸው ጉዳይ ላይ እንዳይሳተፉና አስተያየት እንዳይሰጡ የማግለልና ማንቋሸሽ፣
የመከፋፈሉ ዘመቻ በሰፊው ተጀምርዋል። ይህ አንዱ የከፋፍለህ ግዛው ዘዴ ውጤት ነው። እንደ አገርቤቱ ሕዝባችን ሊጠረንፉዋቸው ስላልቻሉ ያለንበት ወቅት ነቃ ማለትን ይጠይቃል ኢትዮጵያዊ ሱዳን ሆነ ደቡብ አፍሪካ፣አላስካ ሆነ ጂንካ፣ጅዳም ሆነ ካናዳ፣አውሮፓ ሆነ አውስትራሊያ የትም ይሁን ማርስ ላይም ጭምር ሁሉም ዜጋችን በአገሩ ጉዳይ ላይ እኩል ያገባዋል።ባሕር ማዶ ያሉት ዜጎቻችን ለጦርነትና ለድርቅ መ

ዋጮ ሲሆን ብቻ እጅ ከምን የሚባሉበት ዘመን ያብቃ!በፖለቲካም ሆነ በስራ፣በትዳርም ይሁን ውጪ በመወለድ ከአገራቸው ውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው
ጉዳይ ያገባቸዋል ደም ከውሃ ይቀጥናልና!

አዲስ ነገር ጋዜጣን፣አውራምባ ታይምስን የቅርቦቹን ለምሳሌነት ብንወስዳቸው
ይህን ስል ሌሎቹን እረስቼ አይደለም መርሳት የሃበሻ በሃሪ አይደል? ያ የለብኝም
የቀድሞዎቹን ጦብያን፣ኢትዮጵን፣ምኒልክ ወዘተ...ቅጅዎቻቸውን ከወዳጄ ቤት እያሰስኩኝ
ሳነባቸው ይህን ሰናይ ጅማሮ እንዲጠፋና እንዲደበዝዝ ያደረጉትን ገዥዎቻችንን ሳስባቸው
ነፍሴ ትጠየፋቸዋለች።መስፍን ነጋሽ አሸባሪ ነው ስትሉኝ እናደዳለሁ አይደለማ
አብይ ተ/ማርያም ፈንጂ ከሚያፈነዱ ጋር አንድ ላይ ሲጠራ ያመኛል!በአገረ እንግሊዝ ሕግን
የተማረ ብሩሕ ዐዕምሮ ያለው ለአገሩ የሚያስብ ምርጥ ዜጋ ነዋ ይህን ለማወቅ ስራዎቹን ማየት ይበቃል በአካል አይቸውም አላውቅም ስራዎቹ ግን ዘላለም ይኖራሉ።
አቤቶክቻውስ ምን አጥፍቶ ነው ወንድሙን እስከ መግደል ሰይጣናዊ ስራ የተሰራው?
እውነት በማሽሟጠጡ ብቻ እኮ ነው!
እስክንድር ለምን በወሕኒ ቤት አበሳውን ያያል? ሃቁን በመናገሩ ነው`ኮ!
እንስቷ ጋዜጠኛ ዕርዮት ዓለሙ ስለፅፈች`አሸባሪ ስትባል ምፀት ነው!
የሙስሊሙን ወንድሞቻችንን ድምፅ የሚያሰሙት ወኪሎች ለምን ታሰሩ?መልሱ ቀላል ነው
አብዮታዊ ቅብ ሙስሊም ስላልሆኑ ብቻ ነው!
የገዳማት አባቶች ለምን ይሰቃያሉ? ዕምነታችን ይዞታችን ይከበር ስላሉ ብቻ ነው !
ብዙ ማለት ይቻላል ግን ብዙ ቢባል ምን ፋይዳ አለው? ሆድ ሲያውቅ... ነውና ነገሩ!

አቶ መለስ ቢሮ ውስጥ ሆኖ ስራውን እየሰራ ነው ያለን አዲስ አድማስ፣
ለእረፍት ውጭ አገር ናቸው ያለን ዘኢትዮጵያን ሪፖርተር
(ህወሃት ሪፖርተር ቢለው ይሻለው ነበር አማረ አረጋዊ)፣
አዲስ አበባ ዛሬ ተሽሏቸው ገብተዋል ያለን ፎርቹን አልተዘጉም አይዘጉምም...
የጠቅላዩ ጤንነት አጠራጣሪ ነው ያለው ፍትሕ ጋዜጣ ተዘጋ ጋዜጣዋም እውነትን
በመፃፍዋ እንደ መስቀል ደመራ የእሳትራት ተደረገች።ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም
ታስሮ ተፈታ ይቺ ናት እውነተኛዋ አገራችን ኢትዮጵያ ለአንዱ እናት ለሌላው የእንጀራ
እናት ሆናብናለች!
ባሕር ማዶ ያሉ ጋዜጠኞች`ኮ አገርቤት ነበሩ ማን አሰደዳቸው?
ማን አሰራቸው?
አገርቤት መፃፍ ለምን ተከለከሉ?
ውጪ ሆነው መፃፍቸው በምን መስፈርት ወንጀል ይሆናል?
መስከረም ይመጣሉ ያሉን በረከትና ኢቲቪ ሙታንን ማስነሳት ባይችሉም በሙታን መንፈስ
ሊኖሩ ይፈልጋሉ።ሙታንን ለሙታን ተዋቸው የተባለው ቃል እየተፈፀመ ይሆን?

አሁን የተያዘው ሁሉም ነገር ቀልድ ነው ዝናብ ቢዘንብ በጠቃልዩ ጥረትና ልፋት ነው ሊሉን
ይችላሉ በተለይ ግንቦት ላይ ቢዘንብ
"ያሁኑ ግንቦት ሃያ ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገው በዚህ ደረቅ ወር ላይ
ዝናብ የጣለው በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ያላሰለሰ የአካባቢ
ጥበቃ ውጤት ነው.." ይለናል ደፋሩ ኢቲቪ!
ወደ ቀበሌዎች ያደርሱታል አውርቶ አደር ካድሬዎች ዘመነ በቀቀን መች ያበቃ ይሆን?
ያን ቀን ለማየት ያብቃን "ሰው ከቆየ አፍሪካ ዋንጫ ያልፋል" አሉ ሽማግሌው የስታድዮም
ቋሚ ደጋፊ አሉ ነው አሉ ለዘላለም ትኑር በካድሬዎች ሰፈር!

ፈንጂ እያፈነዱ ንፁሃንን እያረዱ በዘር ፀበል ተረጭተው በጥላቻ ተኮትኩተው ያደጉ ባንዳዎች ዛሬ ፈራጅና አዛዥናዛዥ ሆነው ማየት ያስደምማል እንደ አፍሪካ ዋንጫው ይህንንም በአገር ሰው ቅኝ መገዛትን እናልፈዋለን ያኔ ግን አሸባሪ ያላችኋቸው የእናንተ የፀረ ሽብር አጋዦቻችሁ ያስጠጓቸው እነ አብይ የፍርድ ዳኝነቱን ይይዙታል እንደ ሲቪል ሰርቪሶቹ የጥላቻ ማሽኖች ሳይሆን በሕግ የስራችሁን ውጤት ታገኛላችሁ፣መስፍን ነጋሽ ማንም ጣልቃ ሳይገባበት በነፃነት አዲስ ነገርን ነፍስ ሲዘራባት፣አቤቶኪቻውና ዳዊት ከበደ፣ሲሳይ አጌናና አበበ ገላው ሳይሳቀቁ የሚዘግቡበት ቀን ይመጣል ቢጨልምም ዛሬ ብርሃን ይወጣል ጨለመብን ያሉት አጎብዳጅ ዘማርያን ያ የፍትሕ ቀን ታይትቷቸው ይሆናል ፍትሕ ሆይ ቶሎ ነይ!

ብዙ ጥያቄዎች አሉን ግን መልስ ከአቶ ኃይለማርያም የሚጠብቅም የለም መንትያ መለስ
መሆናቸውን ተናግረዋልና!!!!

No comments:

Post a Comment