Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday 15 October 2012

ጅጅጋ፤ ሀረርና ድሬዳዋ ካለፉት ስድስተ ቀናት ወዲህ ጨለማ ውስጥ ናቸው

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ምስራቅ ከተማዎች ላለፉት 6 ቀናት የመብራት አገልግሎት እንደተቋረጠባቸው የታወቀ ሲሆን፤ የደብረዘይት ከተማ ነዋሪዎች ላለፉት 7 ቀናት የውሀ አገልግሎት እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ምንጮቻችን ገልጸውልናል።
ከድሬዳዋ ጅጅጋና ሀረር ከተሞች የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የሀረር፤ ድሬዳዋና ጅጅጋ ከተሞች ላለፉት 6 ቀናት የመብራት አገልግሎት አልነበራቸውም።
የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው አመት ለጅቡቲ 20 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ መሸጥ መጀመሩን መናገሩ የሚታወስ ሲሆን፤ በቀጣዮቹ አመታትም ለሱዳንና ለኬንያ ሀይል የመሸጥ እቅድ እንዳለውም ይታወቃል።
ኢትዮጵያ 45 ሺህ ሜጋ ዋት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም እንዳላት ቢገመትም እስካሁን ማምረት የምትችለው 2000 ሜጋ ዋት ብቻ ነው።
የኢህአዴግ አስተዳደር እስከ 2015 ድረስ የኢትዮጵያን የሀይል አቅርቦት በአራት እጥፍ ለመጨመርና 10 ሺህ ላመድረስ እቅድ የያዘ ሲሆን፤ ላለፉት 21 አመታት ተጨማሪ 1600 ሜጋ ዋት ብቻ መጨመር የቻለው ኢህአዴግ በቀጣዮቹ ሶስት አመታት የሀይል ቀእርቦቱን 10 ሺህ ለማድረስ ያስቸግረዋል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
በሌላ ዜና፤ የደብረ ዘይት ከተማ ነዋሪዎች ላለፉት 7 ቀናት የውሀ አገልግሎት እንደሌላቸው ታወቋል። የውሀ አገልግሎቱ የተቋረጠው፤ በምን ምክንያት እንደሆነ አልታወቀም።
የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ባለፈው ወር ከ20 ቀናት በላይ የውሀ አገልግሎታቸው ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment