Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 1 December 2012

12-year-old video released: How Meles crushed his rivals Eyerusalem Araya December 1, 2012








የተለቀቀው ቪዲዮና የፖለቲካ ውጥንቅጡ እንደምታው

(በሕወሓት ውስጥ ከ12 ዓመት በፊት የተፈጠረውን የፖለቲካ ውዝግብ…..የሚያሳየውን ፊልም አሁን ባልታወቁ ወገኖች ተለቆዋል፣ ለረጅም አመት ይህ ፊልም እንዳይታይ ተደርጎ ቆይቶዋል ....... ብዙዎች ትርጉሙን ለማወቅ በመጠየቃቸው....... ወደ አማርኛ ለመመለስ ተሞክሮዋል....... ተርጓሚው የትኛውም ወገን ደጋፊ እንዳልሆነ ይታወቅ.......) ...... by Eyerusalem Araya December 1, 2012
 
በመስሉ እንደሚታየው የመጀመሪያው ተናጋሪ አቶ ገብሩ አስራት ናቸው፣ ይህን አሉ፣ “ የመጣነው ካድሬው ጥሪ ስላደረገልን ነው፣ እየተመለከትን ያለነው ነገር ግልጽ አይደለም፣ ካድሬው የጠራን ያለንን ሃሳብ እንድናቀርብ ነው፣ ከዛ ባሻገር ይህን ስብሰባ በተመለከተ የምንለው ይኖረናል፣ ከዚሁ ጎን ለጎን ያለውን መረጃ ማቅረብ እንችላለን፣ ይህንን ለማለት ነው እዚህ ስብሰባ ላይ የመጣነው፣ * የለም ይህ አያስፈልግም * የምትሉን ከሆነ ግን ሁሉም ነገር አብቅቶለታል ማለት ነው:: ሃሳባችንን ልትሰሙን፣ ስብሰባውንም በተመለከተ ያለንን አቁዋም ከቻላችሁ አዳምጡን:: ይህንን ኢንፎርሜሽን ግልጽ ለማድረግ ነው እዚህ ስብሰባል ላይ የተገኝነው:: ”

የተለያዩ ድምጾች ከተሰሙ በኳላ አቶ ተወልደ ተረኛ ተናጋሪ ለመሆን ቆሙ፣ እንዲህም አሉ “ እዚህ ስብሰባ ላይ የተገኘነው መረጃ ለመስጠት ነው:: እኛ በበኩላችን ይህ ስብሰባ ጠቀሜታ /ፋይዳ/ አለው ብለን አናምንም፣ እናንተ ካድሬዎች መምጣት አለባችሁ ስላላችሁ ይኸው ተገኝተናል:: ህግ እና ደንብ አለ፣ የቁጥጥር ኮሚሺን ህገ ደንቡ እንደተ ጣሰ በመግለጽ * ህገ ወጥ * ነው ብሎታል:: የኛም አቁዋም ይህ ነው!      

……አቶ መለስ ቀበል አድርገው የቀረበውን ሪፖርት አዳምጠን ወደ አስተያየት እንሄዳለን:: በዛ መሰረት እንቀጥላለን:: ”    ሲሉ እነ ተወልደ የመለስን ንግግር አላስጨረሷቸውም…… ከተቀመጡበት ተነስተው ሲወጡ……በአዳራሹ ጫጫታ ለቅሶ  ልመና  ተደበላለቁ…….ስዩም መስፍን ግራ ተጋብተው ይታያሉ…….ስዬ፣ አባይ ጸሃዬና ገብሩ……እያለቀሱ የሚማጸኑዋቸውን ገፍቶ ላለመሄድ ይመስላል  ተመለሰው ተቀመጡ…...አዳራሹ እየተበጠበጠ እያለ….አቶ መለስ:-
« ..እባካቹ…እባካችሁ..» ይላሉ…የሚያዳምጣቸው ሲያጡ ..መለስ ድምፃቸውን በጣም ከፍ አድርገው በቁጣ « አንድ ጊዜ …አንድ ጊዜ … ሁላችሁም ተቀመጡ…ስነ ስርዓት አድርጉ..?..ስነ ስርዓት ያዙ?..» ከዛም ቀጠሉ «.. በዚህ ስብሰባ ላይ ያልፈለገ..አሞራ ብቻ ነው..».. ብዙ እጆች ከተሰብሳቢው ተቀስረው ይታያሉ፤..ጫጫታና ጉምጉምታው..ቀጠለ..
« አንድ ጊዜ ተረጋጉ..» አሉ መለስ፤ በአዳራሹ የተወሰነ ዝምታ ከሰፈነ በሁዋላ ንግግራቸውን ቀጠሉ፦
« ፓርቲያችን ትፈራርሳለች ብላችሁ አታስቡ…ድርጅቱ ሊፈርስ አይችልም! ማንም ሰው ሊያፈርሰው አይችልም!..እኔ አሁን ይህንን ግድግዳ ላፍርሰው ብል..ይፈርሳል?.፣ የማይሆን ነገር ነው! በፍፁም!...ስለዚህ ፓርቲው አይፈርስም..የሚፈርስ ነገር የለም!..
..እንዴ ምን ማለታቹ ነው?..ያልሞተን ሰው <ሞተ> ብሎ መቅበር አለ እንዴ? ..ያልሞተ ሰው ይቀበራል?..ፓርቲያችን እኮ አልሞተም፤..ላልሞተ ሰው ደግሞ አይለቀስም። ለሞተ ግን ይለቀሳል። ..ድርጅታችን ታሞዋል፤ .ጥሩ …ምን ይደረግ?..ማለት አለባችሁ… ..
ከዚህ የከፋ መድረክ ሊመጣ ይችላል… የቀብር ስነስርአት አይደለም እየሰራን ያለነው..እንደ ሃኪም ድርጅት የማዳን ስራ ነው እየሰራን ያለነው፤..» አሉና ወደ አንድ አቅጣጫ እየተመለከቱ..
« ..ስዬ፡ ገብሩ፡ አባይ.. ከሌሎች ተለይታችሁ በራሳችሁ መልካም ፈቃደኝነት ከኛ ጋር አብራችሁ ለመቀጠል እንደምትፈልጉ ለተሰብሳቢው..ይህንኑ ተናገሩ» ..በአዳራሹ ጉምጉምታው በማየሉ..ንግግራቸውን ለመግታት የተገደዱት መለስ.. «..እባካችሁ አንዴ ተረጋጉ፤ ..አንድ ጊዜ እንደማመጥ፤.. ይህቺ የመጨረሻ ዕለት አይደለችም፤..ይህን አማራጭ የማይቀበሉ ከሆነ ..ሌላ ቀን እድል እንዲያገኙ እንፈቅድላቸዋለን። አለበለዚያ ግን ተቆራረጥን ማለት ነው።.. አቅጣጫ አስቀምጠን እንሂድ፤ በምናስቀምጠው አቅጣጫ (መርሕ) ላይ እኰ ልናገኛቸው (ልናጠምዳቸው) እንችላለን።…. ( የመለስ ንግግር..” እሰራላችዋለው” አይነት ነው፤ )..
« ..ስለዚህ አሁን ተረጋግተን ..ድርጅቱን በማዳን ዙሪያ በተቀመጠው አቅጣጫ ዙሪያ እንወያይ፤ በዚህ መልኩ ልቀጥል?.» .. የተለያዩ ድምፆች ተከተሉ…፤ . አባይ ፀሓዬ፡ ስዬና ገብሩ..ከተቀመጡበት የፊት ወንበር ብድግ አሉ፤ ..ውዝግቡ በጫጫታ ታጅቦ ቀጠለ…
ስዬ ወደ ተሰብሳቢው ዞረው ይናገራሉ..የሚናገሩት ግን ምን እንደሆነ በጥራት አይሰማም፤..አባይ ፀሓዬም ይናገራሉ..ከዛም እነ ስዬ እጃቸውን እያወናጨፉ ጥለው ሲወጡ ይታያሉ..
በጫጫታው መሃከል..« እባካችሁ እንደማመጥ…?.. እባካችሁ?» የሚል የአቶ መለስ ድምፅ ይሰማል፤…. ከዚያ ፊልሙ ተቆርጦ እንደቀጠለ ያስታውቃል፤.
…..መለስ ወንበር ላይ ተቀምጠው ይህን አሉ፦ « ቀብር የለም! ታመን ነበር፤ ይህቺ ነበረች ችግራችን። ..ከተደነባበርን፡ የችኰላና ጥድፊያ መንገድ ከተከተልን… በሽታው ይባባሳል። መቶ በመቶ ልትተማመኑበት የሚገባ አንድ ነገር፦ እናንተ እያላችሁ ይህ ፓርቲ አይፈርስም። አይፈርስም!..አሁን ተረጋግተን ስብሰባችንን እንቀጥል»
 

No comments:

Post a Comment