Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 28 November 2012

በሙት “ሌጋሲ” የተዋጡት ጠ/ሚኒስትር



ብስራት /ሚካኤል
afrosonb@gmail.com

ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ያደረጓቸውን በርካታ አሉታዊ ነገሮች ለመጥቀስ በቂ ጊዜና ቦታ ባይኖራቸውም ሰውየውን መልአክለማስመሰል ኢቴቪ እና ሌሎቹም የመንግስት የፕሮፖጋንዳ ማሽኖች የተለያየ ሙከራ አድርገዋል፡፡ መለስ ሲሞቱ ኢህአዴግ በራሱ መቆም እስከማይችል ድረስ በመለስ ተክለ ስብእና ተከልሎ መኖሩን የሚያረጋግጡ ክስተቶች ተስተውለዋል፡፡ ለዚህም አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ /ማርያምን በዋቢነት ማየት በቂ ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር 47 ዓመታቸው ራሳቸውን መሆን የቻሉ አይመስሉም፡፡ ስለዚህ ተፈጥሯዊውን ትክክለኛ ሰው ለመፈለግ በፋኖስ እንደባከነው ፈላስፋ እኛም ጧፍ አሊያም ላምባዲና ይዘን ትክክለኛውን /ማርያም ደሳለኝን ለመፈለግ መገደዳችን አይቀርም፤ ራሳቸውን ሆነው ስናገኛቸውም ኢዮሪካእንላለን፡፡ በተለይ የማይሞቱ ይመስሉ የነበሩት መለስ ከዚህ ዓለም መሰናበት ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ አቶ /ማርያም ራሳቸውን ሆነው መቅረብ አልቻሉም፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ ይሆነን
ዘንድ ጥቂት ማሳያዎችን እንምዘዝ፡፡

ከንቱ መወድስ

የአቶ መለስ ሞት ይፋ ከተደረገ በኋላ በወቅቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ /ማርያም እንደሟቹ የፈንጅና የቦንብ ጢስ እንዲሁም የጥይት አረር ያላሸተቱ በመሆናቸውና በኃይማኖት የታነፁ መሆናቸው ከአቶ መለስ በተሻለ ሊያስተዳድሩ እንደሚችሉ ይወራላቸው ነበር፡፡ ሰውየው በኃይማኖት ረገድም የሐዋርያት እምነትተከታይ እንደሆኑ በተደጋጋሚ ይገለፃል፡፡ ይሄንንም እሳቸው በአንድ ወቅት ምዕራፍከሚባል መጽሄት ጋር ባደረጉት ቆይታ አረጋግጠዋል፡፡

እርሳቸው በሚከተሉት ኃይማኖት ዘወትር የሚደመጥ የክርስቶስን ከፍ የሚያደርግ መወድስ አለ፣ ዘላለማዊ ክብርና ለኢየሱስየሚል፡፡ ጠንካራ ኃይማኖተኛ ናቸው የሚባሉት አቶ /ማርያም በቤተዕምነታቸው የለመዷትን ቃል ዘለዓለማዊ ላልሆኑት ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ያላቸውን አድናቆት ለመግለጽ ቃላት ቢያጥራቸው ዘለዓለማዊ ክብርና ሞገስ ለመለስየሚል ከንቱ መወድስ አቅርበው አረፉት፡፡ ይህ ንግግር ሰውየው ክርስቶስን ከመለስ ጋር መሳለመሳ ያስተካከሉበት ነበር፡፡ አምላካዊ መወድስን ለፖለቲካ ሸቀጥ ማዋላቸው በርካታ ክርስቲያኖች ቅር ከማሰኘቱም ሌላ የአቶ መለስ አምላኪ አስመስሏቸዋል፡፡

የእምባ አድርቅመፅናኛ

የሟቹ ግብዓተ መሬት እንደተፈፀመ በባለስልጣናቱ ከተረጋገጠ በኋላ ያኔ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር የተባሉት አቶ /ማርያም ለህዝቡ በተናጥል በሚመስል መልኩ የእምባ አድርቅ መፅናኛ ግብረ መልስ ሰጥተዋል፡፡ እዚህ ላይ እምባ አድርቅየሚባለው የሟች ግብዓተ መሬት ከተፈፀመ በኋላ ለሐዘንተኞችም ይሁን ልቅሶ ሊደርሱና ሊያፅናኑ ለመጡ እንግዶች የሚሰጥ የሚበላና የሚጠጣ ነገር ነው፡፡ የዚህ መፅናኛ ግብረ መልስ ደግሞ ሊያፅናና የመጣውን አሊያም ለሐዘንተኞቹ (ለሟች ቤተሰቦች) መልካም መፅናናትን ለተመኙ የሚሰጥ እናመሰግናለንምላሽ መልዕክት ነው፡፡
ያኔ አቶ /ማርያም ድርጅታቸው ኢህአዴግንና መንግስትንወክለው አስገራሚ የሆነ የእምባ አድርቅ መፅናኛ ግብረ መልስ ንግግር አድርገዋል፡፡



ነሐሴ 28 ቀን 2004 . የአቶ መለስ ብሔራዊ ሐዘን መጠናቀቁን ይፋ ባደረጉበት ወቅት የተከበራችሁ አምባሳደሮች፣ የተከባራችሁ በሰላማዊ ትግል በሀገር ውስጥ ያላችሁ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ የተከበራችሁ የጐዳና ተዳዳሪዎች . ..ብለው ያልተገባ ዝርዝር ነገር መናገራቸው ግርምትን ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡ አቶ /ማርያም ከውጭ ዲፕሎማቶችና መሪዎች ውጭ ያሉትን ኢትዮጵያውያን የተከበርከው የሀገራችን ህዝብማለት ተስኗቸው ሳይሆን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማማለል ያደረጉት የየዋህ ሙከራ ነበር፡፡

እዚህ ላይ አቶ /ማርያም የጐዳና ተዳዳሪዎችብለው ማመስገናቸው አዲሱ ሰውዬ የተጣለውንም የህብረተሰብ ክፍል የሚያስታውሱ ናቸውየሚል አስተሳሰብ ለመፍጠር ያቀናበሯት ነች ፡፡ እዚህ ላይ ማንም ሰው ወዶና ፈቅዶ የጐዳና ተዳዳሪ መሆን የሚፈልግ እንደሌለና ይልቁንም ባለዕራዕይ መሪእያሉ በሚያሞካሹዋቸው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም አባሎቻቸው በፈጠሩትየመንግስት ሌቦችስርዓት ዜጐች ለጐዳና
ተዳዳሪነት ህይወት እንደበቁና እየበቁ እንዳለ የገባቸው አይመስልም፡፡ የዛሬው ጠቅላይ ሚኒስትር ያኔ አቶ መለስ በየመድረኩ ለሰው ልጆች ክብር ያላቸው ለማስመሰል የተከበራችሁ ወጣቶች፣ የተከበራችሁ ሴቶች፣ የተከበራችሁ ወንዶች፣ አረጋውያን አዛውንቶች፣ የተከበራችሁ የድርጅታችን
አባላትና የልማት ሰራዊት . . .ያሉትን የኮረጁት አቶ /ማርያም ምስጋና ሲደረድሩ አምሽተው ነበር፡.

ከአስኬማ አልባ ክህነት በኋላ

እውነት ለመናገር አቶ /ማርያም ደሳለኝ ሀገሪቱን ለመምራት በድርጅታቸው ኢህአዴግ አመራሮች ፈቃድ ከነ ሙሉ ክብራቸው፣ ጥቅማቸውና ግዴታቸው ጋር በጠ/ሚኒስትርነት ተሹመዋል ማለት ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሾሙ በኋላም ራሳቸውን ሆነው ከመገኘት ይልቅ ሟቹን ለመምሰል ሲጥሩ እየተስተዋለ ነውና፡፡ በተደጋጋሚም የአቶ መለስን ራዕይ እናሳካለን፣ እሳቸው የጀመሩትንና የወጠኑትን በሙሉ እናስፈፅማለንእያሉ የሚጠበቅባቸውን የራሳቸውን ተሰጥዖና ድርሻ ተግባር ላይ ለማዋልም ሆነ አሻራቸውን ለማኖር የተዘጋጁ አይመስሉም፡፡

አቶ /ማርያም በሙት መንፈስ በመመራት ጥሩና መጥፎውን ሳይለዩ እንደወረደ እንደሚያስፈፅሙ በይፋ በየመድረኩ መግለፃቸው የተሰጣቸው ስልጣን ምሉዕ እንዳልሆነና በሌጋሲ ማስፈፀም ሰበብ ከጀርባ ሆኖ የሚመራ ዋነኛ አካል እንዳለ ሳያቁት አረጋግጠዋል፡፡ ስለዚህ ስልጣናቸው አስኬማ
አልባ ክህነት ሆኗል ማለት ነው፡፡ /ማርያም በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሾሙ በኋላም ራሳቸውን መሆን እንዳልቻሉ በቅርቡ በፓርላማ የመንግስትን አቋምና በማብራራት በቀረቡበት ወቅት አንፀባርቀዋል፡፡ በወቅቱ ፓርላማ ውስጥ ሆነው አቶ መለስ ያደርጓቸው የነበሩት እንቅስቃሴዎች፣ ቃላትና ንግግር ላየ አቶ /ማርያም መለስን መስለው እንደተወኑ ለመረዳት አይቸገርም፡፡ ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ ከቀረበላቸው በኋላ መልስ ሲሰጡ በንግግር ወቅት የፊት አዟዟራቸው፣ የማጅራታቸውን ቀኝ ጐን መዳበሳቸው፣ መነፅራቸውን በተደጋጋሚ ከፍ ለማድረግ መሞከራቸው፣ የመብት ጥያቄን አንስተው በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ የሚያቀርቡትን በመፈረጅና በማስፈራራት እሳት እንደመንካት ነውበማለት አቶ መለስን ሆነው ተውነዋል፡፡
ልክ እንደ አቶ መለስ በፓርላማ ከፈረዱና ካስፈራሩ በኋላ በወሎ ገርባ አካባቢ ኃይማኖታዊ የመብት ጥያቄ ያነሱ የሙስሊም ማኅበረሰብ ላይ ያለፍርድ ቤት ሞት በመበየናቸው ዜጎች ህይወታቸው አልፎአል፤ የቆሰሉም አሉ፡፡ አቶ መለስ የሽግግር መንግስቱ ፕሬዘዳንት እንደሆኑ 1985 . የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው የተገደሉ፣ የቆሰሉ፣ የተሰወሩ እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ አቶ /ማርያምምወደ መንግስት መሪነት ብቅ ካሉ ጀምሮ ድሮ ከሚታወቁበትና ከሚነገርላቸው ከራሳቸው ሙሉ ስብዕና ወጥተው በቁም እያሉ ሟቹን ሆነው እየታዩ ይገኛሉ፡፡

በርግጥ መልካም ተሞክሮንና ድርጊትን ወስዶከራስ ጋር ማስማማት ብልህነት ቢሆንም አቶ /ማርያም ግን ከነ አሰስ ገሰሱ አቶ መለስን ለመሆን መሞከራቸው ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍላቸው ይችላል፡፡ አሁን ባለው አካሄድ አቶ /ማርያም ራሳቸውን ሳይሆን ሟቹን አቶ መለስን ለመሆን መሞከራቸው በሙት ጥላ ስር እንዲወድቁና ማንነታቸውን እንዲጥሉ ያደረጋቸው ይመስላል፡፡ ይህ ሂደት የሚቀጥል ከሆነ የራስ ማንነት ቀውስ (personal identity crisis) ውስጥ በመግባት ከፍተኛ የጤና መቃወስ ሊገጥማቸው ስለሚችል ከአሁኑ አስበውበት ራሳቸውን ሆነው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ለማንኛውም አቶ /ማርያም ራሳቸውን እስኪሆኑ ድረስ በመለስ ሌጋሲውስጥ ተሰውረው ከመኖር ውጪ አማራጭ የላቸውም፡፡

No comments:

Post a Comment