Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday 15 May 2012

21 የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደታሰሩ ይገኛሉ አንድ ተማሪ በጥይት ቆስሏል፣ በከባድ ሁኔታ የተደበደቡ ተማሪዎች በርካታ ናቸው ‹‹በርካታ ፖሊሶች በዩኒቨርስቲው ግቢና ውጪ በመኖራቸው በነፃነት መንቀሳቀስ አልቻልንም››/ተማሪዎች/


ከእሁድ ሚያዚያ 28/2004 .. አመሻሽ ጀምሮ በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ከምግብ ጥራት ጋር በተያያዘ በተነሳው ተቃውሞና ፖሊስ በወሰደው የኃይል እርምጃ ሳቢያ ተማሪዎች እስከ አሁን ድረስ በመደበኛ የትምህርት ገበታቸው ላይ አለመሆናቸውን የፍትህ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ እሁድ ዕለት በተነሳው ተቃውሞ አብዛኛው ተማሪ ቁጣውን የዩኒቨርስቲውን መስታወቶች በመሰባበር እንደገለፀና ምሽት ላይ በድንገት ወደ ግቢ የገቡት ታጣቂዎች በተማሪዎቹ ላይ ከመጠን ያለፈ ኃይል በመጠቀም ጉዳት እንዳደረሱ የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹ እሁድ እና ሰኞ የተፈጠረው ችግር የአንድ ቀን የእራት ችግር ሳይሆን የታወቀ የፍትህ፣ እኩልነትና ነፃነት ማጣት ብሶትና በደል ውጤት መሆኑን ጠቅሰው ሃሳባቸውን ያለፍርሃት ሲገልፁ መሰማታቸውን ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰው መረጃ ያስረዳል። የተቃውሞው መነሻ ምክንያትም አንድ ተማሪ የምግብ ቤት አስተናጋጇን ‹‹ዛሬም ሽሮ ነው?›› ሲላት፤ አስተናጋጇ መልሳ ‹‹የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪ እንኳን ሽሮ እንጨት ቢሰጡት ይበላል›› በማለቷ የቆየው የተማሪዎች ችግር መፈንዳቱን የፍትሕ ምንጮች ይገልፃሉ።
ተማሪዎቹ ‹‹ዩኒቨርስቲው እየተመራ ያለው በዩኒቨርስቲው አመራሮች አይደለም። በአራቱ የኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅቶች አስተባባሪ ነው፡፡ /ቤታቸውም ከግቢ ይውጣበመማር ማስተማሩ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው። የድርጅቱ መሪዎች መታወቂያ ይቀሙናል፣
ያስፈራሩናል፡፡ በተለይም ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ውጭ ያለን ተማሪዎች ችግራችን ተነግሮ አያልቅም›› የሚል ቅሬታም አላቸው። የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ችግራችን ቢፈታልን ብለው ለፓርቲ አስተባባሪዎች ጥያቄ ቢያቀርቡም ‹‹ሞክሩትና እንተያይ›› የሚል መልስ እንደተሰጣቸው በመጥቀስ ዩኒቨርስቲው የትምህርት መስጫ ተቋም ሳይሆን የፖለቲካ (የኢህአዴግ) ማዕከል መሆኑንና ተማሪው ሀሳቡን በነፃነት እንዳይገልፅ መደረጉን ምንጮቻችን ያስረዳሉ።
የተማሪዎቹ መሰረታዊ ጥያቄዎች ‹‹የፖለቲካ ድርጅቱ ከግቢ ይውጣ›› የሚል መሆኑንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል። በተፈጠረው ረብሻም 60 ያላነሱ ተማሪዎች ታስረው እንደነበረ፣ አሁንም 21 የሚሆኑት ታስረው እንደሚገኙ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች መደብደባቸው፣ አይናቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ መኖራቸው፣ እጅና እግራቸው የተሰበሩ፣ በመኪና የተገጩና በተፈጠረው ሁኔታ በስነ ልቦና የተረበሹ መኖራቸው ታውቋል።
‹‹ከቁርጭምጭሚቴ በላይ በጥይት ከተመታው በኋላ በደብረማርቆስ ሆስፒታል ሕክምና ተደርጐልኝ ወጣሁ›› የሚለው 2 አመት
የማናጅመንት ተማሪ ኢብራሂም መሃመድ፣ ዛሬ በድጋሚ ሆስፒታል ቀጠሮ እንዳለው ለፍትሕ በስልክ የተናገረው በአቅራቢያው የሚገኝ
ዘመድ ቤት እንደተጠለለ ነው። በፖሊስ ዱላና ሽመል ጀርባውና ደረቱ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት ማክሰኞ ዕለት ከሆስፒታል መውጣቱን ለፍትሕ የተናገረው ደግሞ 1 ዓመት የሲቪል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ገብረኪዳን ብርሃኔ ‹‹ስቃይ እየተሰማኝ ነው›› ብሏል።
ዩኒቨርስቲውም ‹‹በእስር ላይ ያሉ ልጆች በቂ ቅጣት እስኪሰጣቸው ድረስ እናንተ ተማሩ›› የሚል ማስታወቂያ አውጥቶ እንደነበረ
የሚገልፀው ተማሪ ገብረኪዳን ተማሪዎች ‹‹ጓደኞቻችን ታስረው፣ ሆስፒታል ተኝተው እንዴት እንማራለን? አንማርም!›› ብለው ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ትላንት ምሽት ድርስ ትምህርት አለመጀመራቸውን ለፍትሕ ገልጿል።
ከዚሁ ተያይዞ ባገኘነው መረጃ መሰረት ተማሪዎች በአስተማሪዎቻቸውና በተማሪዎች ተወካይ አማካኝነት በካፍቴሪያ ለመመመገብ፣ በዶርሚተሪ ለመጠቀም፣ በትምህርት ገበታ ላይ ለመገኘትና በግቢው ውስጥ ለመንቀሳቀስ ‹‹ጊዜያዊ ወረቀት›› የመውሰድ ግዴታ ከትላንት ጀምሮ እንደተጣለባቸው ነው፡፡ ይሄንን ያደረጉ ተማሪዎች መኖራቸውንም ፍትህ ለማወቅ ችላለች፡፡ ነገር ግን፣ የታሰሩ ተማሪዎች
ከእስር ተፈትተውና በድብደባ ጉዳት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች አገግመው ወደ ትምህርት ገበታቸው በሰላም ካልተመለሱ በስተቀር ትምህርት
ለመጀመር ብዙሃኑ ተማሪ ዝግጁ አለመሆኑን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ተማሪዎች ለፍትህ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የታጠቁ
በርካታ ፖሊሶች በሁለት በኤፍ ኤስ አር መኪና ተጭነው በመምጣት በዩኒቨርስቲው ዙሪያና ውስጥ ፈስሰው እንደሚገኙ የተናገሩት ምንጮች ግቢው የትምህርት ተቋም እንጂ ወታደራዊ ካምፕ አለመሆኑን በመጥቀስ ተማሪዎች ‹‹ፖሊሶች ከግቢያችን ይውጡ›› እያሉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ ተማሪዎቹም በፍርሃትና በስጋት ውስጥ እንደሚገኙም ለፍትህ አልሸሸጉም፡ በፍትህ በኩልም ስለጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡

No comments:

Post a Comment