Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday 15 May 2012

መትረየስና ጠመንጃ የሰረቁ በእስራት ተቀጡ


የአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሎጀስቲክ ዋና መምሪያ ባልደረቦች ይገኙበታል

አንድ ብሬን መትረየስ እና አንድ ባለሰደፍ ጠመንጃን የሰረቁ ስምንት ግለሰቦች በፌዴራል ከፍተኛ /ቤት 15 ወንጀል ችሎት ከትናንት በስትያ ስምንት አመት በሚደርስ እስርና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላለፈ። 1ኛተከሳሽ መቶ አለቃ ደረጀ ተስፋዬና 2 ተከሳሽ መቶ አለቃ ዘመድኩን /ዮሐንስ በአገር መከላከያ ሚኒስቴር በሎጀስቲክ ዋና መምሪያ የኦርድናንስ መምሪያ የናዝሬት ጦር መሳሪያ ዲፖ
የግምጃ ቤት ኃላፊዎች መሆናቸውን የክሳቸው ዝርዝር ያስረዳል። 3 ተከሳሽም ሃምሳ አለቃ ዲጋሞ ደፌ በጥበቃ ስራ ላይ ተመድቦ የሚሰራ የሰራዊቱ አባል ሲሆን ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሳቸው ለማግኘትና 4ኛ፣ 5ኛ፣ 6 እና 7 ተከሳሾች ለማስገኘት አስበው ነበር። 1 ተከሳሽ 2ኛና 3 ተከሳሽ ጋር በመመሳጠር በኃላፊነት ከሚቆጣጠረውና በአደራ ከተረከበው የጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት ውስጥ የመለያ ቁጥር - 049 የሆነ አንድ ብሬን መትረየስ እና የመለያ ቁጥሩ 782288 የሆነ አንድ ባለሰደፍ ክላሽ ጠመንጃዎችን ፈታትቶ በማዳበሪያ ይጠቀልላል። ከዚያም 3 ተከሳሽ የጥበቃ ሽፍት ጊዜ በሆነበት ሐምሌ 22 ቀን 2004 .. ከምሽቱ 300-400 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ አውጥቶ ጠመንጃዎቹን
ለሚያሻሽጠው 4 ተከሳሽ እንዲሰጥ 3 ተከሳሽ ይሰጣል።
3 ተከሳሽም ጠመንጃዎችን 1 ተከሳሽ ተረክቦ የጦር መሳሪያ ዲፓ ከሚገኝበትና ከሚጠብቀው ካምፕ አጥር ውጪ አውጥቶ በማስቀመጥ 4 ተከሳሽ ጠመንጃዎቹን ከደበቁበት ቦታ አንስቶ እንዲወስድ አድርጐ ነበር። 2 ተከሳሽም ቀደም ሲል በሰው የተዋወቀውን 4 ተከሳሽ የሚሸጥ የጦር መሳሪያ እንዲያፈላልግለት በነገረው መሰረት ከላይ የተጠቀሱትን ጠመንጃዎች 1 ተከሳሽ እንዲሸጥለት በማሳመን መሳሪያዎቹ 3 ተከሳሽ አማካኝነት እንዲመጡ ያስደርጋል። ከዚያም 4 ተከሳሽን በስልክ በመጥራት ጠመንጃዎቹን እንዲወስድ በማስደረጉ 4 ተከሳሽም 2 እና 3 ተከሳሾች መሳሪያዎቹ ከተደበቁበት አንስቶ እንዲወስድ በስልክ ደውለው በነገሩት መሰረት ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ጠመንጃዎቹ ከተደበቁበት ቦታ አንስቶ በመውሰድ ናዝሬት ከተማ ቀበሌ 09 ክልል ውስጥ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ያስቀምጣል። በነጋታው ሐምሌ 23/2002 .. በግምት ከቀኑ 800 ሰዓት ሲሆን 7 ተከሳሽ ለማስረከብ እና ጠመንጃዎቹ የተሸጡበትን ዋጋ ብር 18000 ብር በመቀበል ከዚሁ ብር 16100
ብር 1 ተከሳሽ፣ 2 ተከሳሽ ደግሞ 2000 ብር መስጠቱን የሚያስረዳው ክሱ ነው። 1 ተከሳሽ ሐምሌ 25/2002 .. ካምፕ ውስጥ 3 ተከሳሽን በመጥራት ‹‹ድርሻህ ነው›› ብሎ 2000 ብር ሰጥቶታል። እንዲሁም 5 እና 6 ተከሳሾችም 7 ተከሳሽ የጦር መሳሪያዎቹን
ጭኖ ከናዝሬት ወደ አዲስ አበባ የሚወስድ ተሽከርካሪ ይዘው እንዲመጡ በነገራቸው መሰረት ሐምሌ 23/2002 .. አንድ የቤት መኪና 8
ተከሳሽ ይኮናተራሉ። ቀጥሎም ተከሳሾች ናዝሬት በመድረስ የጦር መሳሪያውን 4 ተከሳሽ ቤት አውጥተውና በልብስ ሻንጣ ጭነው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ቃሊቲ ፍተሻ ጣቢያ ላይ ለመያዝ ችለዋል። በሁለተኛ ክስ የተከሰሰው 8 ተከሳሽ ብቻ ነበር፡፡ ተከሳሽም ከላይ የተጠቀሱት የጦር
መሳሪያዎች በሙስና ወንጀል ድርጊት የተገኙ ለመሆናቸው በቂ ምክንያት እያለው እንዳላወቀ በመምሰል በቃሊቲ ፍተሻ ጣቢያ ላይ እጅ ከፍንጅ
እስኪያዝ ድረስ አገባብ ላለው ባለስልጣን ሳያሳውቅ በመቅረቱ ክሱ ሊቀርብበት ችሏል፡፡ ፍርድ ቤቱም 1ኛ፣ 2ኛ፣5ኛና 6 ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በስምንት አመት ፅኑ እስራትና 5000 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ውሳኔ ሲያስተላልፍ በሌሎቹም ላይ እንደወንጀላቸው
መጠን የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷቸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment