Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 16 May 2012

ኢቴቪ በወንጀል እንጂ በፍትሐብሄር ልከሰስ አይገባም አለ


  - የነ አንዱዓለም ክስ ፍርድ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ
 አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ላይ የመሠረተው የስም ማጥፋት ክስ ሰፊ ክርክር ተደረገበት፡፡
ኢቴቪአኬልዳማበሚለው ዘጋቢ ፊልም ስሜን አጥፍቷል፣ ጋዜጠኛውም ቢሆን እንዲሁ ሲል አንድነት ፓርቲ በመሰረተው ክስ ላይ ግንቦት 3 ቀን 2004 . በፌደራል የመጀመሪያ /ቤት ልደታ ምድብ 9 ፍትሐብሄር ችሎት በክሶቹ ጭብጨት ላይ ክርክር ተደርጓል፡፡
ኢቴቪ በበኩሉ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ያለ መሆኑን ጠቅሶ ልከሰስ እንኳ የሚገባ ከሆነ በወንጀል እንጂ በፍትሐብሔር መሆን ስለሌለበት /ቤቱ ክሱን ውድቅ ያድርግልኝ ሲል እንዲያደርግለት ጠይቋል፡፡ የኢቴቪ ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ደግሞ የዘጋቢ ፊልሙ አዘጋጅ እኔ ስላልሆንኩ ልጠየቅ አይገባም ሲል ክሱን ተቃውሟል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ጠበቃ አቶ ገበየሁ ይርዳው በበኩላቸው ለኢቴቪ በሠጡት መልስ በፓርቲው ላይ የፈፀማችሁት የስም ማጥፋት በወንጀልና በፍትሐብሔር የሚያስጠይቅ ቢሆንም እኛ የመሠረት ነው ክስ የፍትሐብሔር ነው፤ ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ ነው የሚባለው ከተመሰረተው ክስ ጋር የሚያያይዘው ነገር እንደሌለ በመግለፅ መከራከሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ጋዜጠኛ አብዲን በተመለከተም ዘጋቢ ፊልሙ ላይ አዘጋጅ ያልተጠቀሰ በመሆኑና አቅራቢው እራሱ ስለሆነእኛ የምናውቀው አዘጋጅና አቅራቢ ራሱ ጋዜጠኛው አብዲ ከማል መሆኑን ነው ብለዋል፡፡

/ቤቱም የኢቴቪን ነገረፈጅ አቶ ተማም ሁሴንን የዘጋቢ ፊልሙ አዘጋጅ ማነው? ሲል የጠየቃቸው ሲሆን አቶ ተማምም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ከኢቴቪ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በመጨረሻም /ቤቱ ክሱ ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ ነው ተብሎ በኢቴቪ የተገለፀውን አስመልክቶ የክሱ የመዝገብ ቁጥርና ፋይሉ ተያይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን መርምሮ ምላሽ ለመስጠት ለግንቦት 10 ቀን 2004. ከቀኑ 815 ሰዓት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በተያያዘ ዜና በነ አንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ ፍርድ ይሰጣል ተብሎ ለግንቦት 3 ቀን 2004 . /ቤቱ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዕለቱ የፍርዱን ሂደት ለመታዘብ የአሜሪካን አምባሳደርና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የተከሻስ ቤተሰቦችና ወዳጆች፣ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች ተገኝተዋል፡፡ ነገር ግን የችሎቱ አዳራሽ በመጥበቡ ምክንያትም አብዛኞቹ ጋዜጠኞች፣ የተከሳሽ ቤተሰቦችና ወዳጆች እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ሳይገቡ መቅረታቸውን ለመታዘብ ችለናል፡፡ አቶ አንዱዓለም አራጌም ፍርዱን የሚታዘቡ ቤተሰቦቻችንና ጋዜጠኞች ስላልገቡ በሰፊ አዳራሽ እንዲሆን የጠየቁ ሲሆን / ቤቱ የቀረቡትን ማስረጃዎች መርምሮ አለመጨረሱን በመግለፅ በዕለቱ ፍርድ እንደማይሰጥ በማስታወቅ ፍርድ ለመስጠት ለሰኔ 14 ቀን 2004 . ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

No comments:

Post a Comment