Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday 15 May 2012

አቡነ ጳውሎስ የሲኖዶስ ውሳኔን በመጣስ የልማት ኮሚሽኑን ሊቀጳጳስ አቡነ ሳሙኤልን ከቼክ ፈራሚነት ሰረዙ


. ሲኖዶሱ በመነጋገሪያ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ነው

ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ የኾኑት አቡነ ሳሙኤል በኮሚሽኑ ስም በተከፈቱት የተንቀሳቃሽና ቁጠባ ሒሳቦች ላይ ፊርማቸው እንዲሰረዝ ለአምስት ባንኮች የጻፉት ደብዳቤ በፓትርያሪኩና በሊቀጳጳሱ መካከል የተዳፈነውን አለመግባባት ዳግመኛ እንደቀሰቀሰው ምንጮችችን አረጋግጠዋል፡፡ አቡነ ጳውሎስ የፊርማ ስረዛውን ትእዛዝ የሰጡት በለጋሾች፣ በመንግሥት አካላት እና በኮሚሽኑ የጋራ ስምምነት ተፈርሞ በመጣው ገንዘብ ላይ ለበርካታ ጊዜ የሚያቀርቡትን አግባብ ያልኾነ ጥያቄ ሊቀጳጳሱ አቡነ ሳሙኤል በተደጋጋሚ በመቃወማቸውና በማገዳቸው መኾኑ ተገልጧል፡፡ ፓትርያሪኩ በአቡነ ሳሙኤል ምትክ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ፊልጶስ ከኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጋራ በጣምራ ፊርማ ቼኮቹን እንዲያንቀሳቅሱ ለኮሚሽኑ ያቀረቡት ጥያቄም ተቀባይነት እንዳላገኘ የኮሚሽኑ ምንጮች ለፍትሕ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቡነ ፊልጶስ የፓትርያሪኩ ጥያቄ ጥቅምት 12 ቀን 2000 . በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወስኖ በሥራ ላይ በዋለው መመሪያ አንቀጽ 17 ቁጥር 2- ‹‹በኮሚሽኑ ስም የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ሁሉ በኮሚሽኑ ሊቀጳጳስ፣ በኮሚሽነሩና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከሦስቱ በሚገኙት በሁሉ ጣምራ ፊርማ ይንቀሳቀሳሉ›› የሚለውን እንደሚፃረር በመጥቀስ በኮሚሽኑ በተከፈቱ ተንቀሳቃሽም ኾነ የቁጠባ ሒሳቦች ላይ እንደማይፈርሙ ሚያዝያ 22 ቀን 2004 . ለኮሚሽኑ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡ የአቡነ ፊልጶስ ተቃውሞ አላገዳቸውም የተባሉት አቡነ ጳውሎስ በቁጥር //439/301/04 በቀን 29/8/2004 . በቀጥታ ለአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አራት ቅርንጫፎች፣ ለወጋገን ባንክ እና ለአቢሲኒያ ባንክ በጻፏቸው ደብዳቤዎች ‹‹ብፁዕ አባ ፊልጶስ ሌላ ጉዳይ ስላጋጠማቸው አልተመቻቸውም›› በሚል የኮሚሽኑ የፋይናንስ መምሪያ ሓላፊ አቶ ከበደ በየነ ተተክተው ከኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጋራ ሒሳቦቹን በጣምራ ፊርማ እንዲያንቀሳቅሱ ባንኮቹ ትእዛዝ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተመልክቷል፡፡ ፓትርያሪኩ ጥያቄያቸው ተፈጻሚ እንዲኾን ትእዛዝ የሚያስተላልፉት በኮሚሽነሩ ኮሚሽነር / አግደው ረዴ በኩል ሲኾን የኮሚሽኑ ሊቀጳጳስ አቡነ ሳሙኤል በበኩላቸው የኮሚሽኑ ሥራ ሕግንና ደንብን ተከትሎ እንዲከናወን በማሳሰብ ኮሚሽነሩ / አግደው ረዴ ‹‹ለግለሰባዊ ፍላጎትና ሐሳብ ቅድሚያ ከመስጠትና ተባባሪ ከመኾን እንዲቆጠቡ›› መጋቢት 24 ቀን 2004 . እና ሚያዝያ 22 ቀን 2004 . በቃል እና በጽሑፍ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ምንጮቹ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment