Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 16 May 2012

ተማሪዎች በት/ቤት የደኢሕዴን ልሳን እንዲያነቡ መደረጋቸውን ወላጆች አወገዙ


በደቡብ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ አንዳንድ /ቤቶች ውስጥ በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች ጣልቃ እየገቡ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ልሳን እንዲያነቡና እንዲወያዩበት መደረጉ ህገ-ወጥ ተግባር ነው ሲሉ ወላጆች ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ ወላጆች እንደሚሉትበአሁኑ ጊዜ በደቡብ ክልል በሚገኙ /ቤቶች 9-12 ክፍል ያሉ ተማሪዎች በደኢህዴን ልሳን እንዲወያዩ ይደረጋሉ፡፡ ውይይቱ የትምህርቱ አካል ተደርጎ ስለሚቀርብላቸው ተማሪዎች ያለማንበብ ወይም ያለመስማት መብት የላቸውም፡፡ እድሜውና እውቀቱ ባልፈቀደበትና ለመደበኛ ትምህርት በተላከ ተማሪ ላይ ይህንን መፈፀም ወንጀል ነውሲሉ ያወግዛሉ፡፡
ወላጆች አያይዘውም ሲገልጹ ‹‹በትምህርትና በአመለካከታቸው ፈጠን ያሉ ተማሪዎችን በመመልመል ተማሪውን አንድ ለአምስት በማደራጀት የፖለቲካ አስተሳሰባቸውን ለማሸከም ይሰራሉ፡፡ወጣት ፓርላማእያሉ ንጹህ የህፃናትን ጭንቅላትን ተገቢ ላልሆነ ባህርይ እየዳረጓቸው ነው፡፡ ተገቢውን ትምህርት ከማስተማር ይልቅ እድሜ የማይፈቅድላቸውን የዘረኝነት፣ የጥላቻና የልዩነት መርዝ ይግቷቸዋል፡፡ ልጆቻችን መደበኛ ትምህርታቸውን ትተው ተገቢ ባልሆነ ሥራ ተጠምደዋል፡ ›› ሲሉ ያማርራሉ፡፡ በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸውን አካላት ሐሳብ እንዲሰጡበት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

No comments:

Post a Comment