በአርሲ
አሳሳ
ባለፈው
አርብ
በተፈጠረው
ግጭት
በፌደራል
ፖሊስ
የተገደሉት
ሰዎች
ቁጥር
ወደ
ሰባት
ከፍ
ማለቱን
ከስፍራው
ያገኘናቸው
መረጃዎች
አመለከቱ፡፡
ባለፈው
አርብ
በአርሲ
አሳሳ
በሙስሊሙ
ህብረተሰብና
በፌደራል
ፖሊሶች
መሀከል
በተፈጠረው
ግጭት
የሞቱት
ሰዎች
5 የነበረ
ቢሆንም
ትላንት
በደረሰን
መረጃ
የሟቾቹ
ቁጥር
ወደ
7 እንደ
ደረሰ
አመላክቷል፡፡
ስለ
ግጭቱ
መንስኤ
መንግስት
ባወጣው
ዘገባና
እና
ከስፍራው
በሚወጡ
መረጃዎች
መካከል
ልዩነት
የሚታይ
ሲሆን፣
ስለሁኔታው
ከገለልተኛ
ምንጮች
ለማጣራት
አልተቻለም፡፡
ለጉዳዩ
ቅርበት
ያላቸው
ምንጮች
ለፍኖተ
ነፃነት
እንደገለፁት
ግጭቱ
የተቀሰቀሰው
ሼህ
መስኡድ
የተባሉ
የሀይማኖት
አባት
“አህባሽ
አይወክለንም” እንዲሁም“ለ20
ዓመት
ኢህአዴግን
ደግፈን
ኖረን
እንዴት
አሸባሪዎች
ናችሁ
ይለናል” የሚሉ
መልዕክቶችን
በትምህርታቸው
ውስጥ
አካተው
በማስተማራቸው
ነው፡፡
መንግስት
ግለሰቡን
ለመያዝ
ያደረገውን
ጥረት
የአካባቢው
ሙስሊም
ህብረተሰብ
በመከላከሉ
በተፈጠረው
አለመግባባት
ፖሊሶች
በተቃዋሚዎች
ላይ
በከፈቱት
ተኩስ
አንድ
የስድስት
አመት
ህጻንን
ጨምሮ
መገደላቸውን
ለመረዳት
ተችሏል፡፡
በጉዳዩ
ላይ
የመንግስትን
አስተያየት
ለማግኘት
የኮሙኒኬሽን
ጉዳዮች
ጽ/ቤት
ምክትል
ኃላፊ
የሆኑት
አቶ
ሽመልስ
ከማል
ጋር
ደውለን
ጉዳዩ
በምርመራ
ላይ
እንደሆነገልፀው
አስተያየት
ከመስጠት
ተቆጥበዋል፡፡
No comments:
Post a Comment