Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 2 May 2012

የሰሜን ጐንደር ሕዝብ የቁም እስረኛ ሆኗል......ፍኖተ ነጻነት



ኢህአዴግ በአማራ ብሔር ላይ ጣቱን ቀስሯልሲሉ አንዳንድ የሰሜን ጐንደር አርሶአደሮች ለዝግጅት ክፍላችን ገለፁ፡፡ የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ኢህአዴግ የአማራውን ህዝብ ከመኖሪያውና ከሥፍራው ለማፈናቀልና የሃይማኖት ብጥብጥ ለማስነሳት እቅድ ይዞ እየሰራ ነው፡፡ ደቡብ የሚገኙ አማሮችን በመመሪያ እያፈናቀለ ይገኛል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ያለውን ቀጥሎአል፡፡ ተፈናቅለው የሚመለሱትም እንዲቋቋሙ ምንም ዓይነት ድጋፍ አይደረግምብለዋል፡፡ እነዚህ ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተልን ነው የሚሉት አርሶ አደሮች እንደሚሉት ሰሞኑን ደግሞ በሰሜን ጐንደር ሱዳን ድንበር አካባቢ በምትገኝ ምዕራብ አርማጭሆ /ኢብርሃጂራ/ በምትባል ወረዳ በእርሻ ሥራ ተሰማርተው የሚኖሩ አርሶአደሮች የእርሻ መሬታቸውን ተነጥቀው
ተባረዋል፡፡ 1998 . ጀምሮ በአካባቢው በእርሻ ሥራ ላይ ያሉትን አርሶ አደሮች መሬቱ በብሎክስለሚደለደል
ያለሰለስኩቱ ማሣዬ ነው፤ ለኔ ይገባኛል የሚል ጥያቄ እንዳያነሱ ማስጠንቀቂያም ተሰጥቷቸዋል፡፡ አንዳንድ ታዛቢዎች የኢትዮጵያን መሬት ቆርሶ ለሱዳን በመሰጠት በሥፍራው ያሉትን አርሶአደሮች አፈናቅሏልይላሉ፡፡ የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ታች አርማጭሆ ወረዳ /ሣንጀ/ ለረጂም ዓመታት ኪዳነምህረት ቅዱስ ሚካኤል ጽላት ማደሪያ ሥፍራ ለልማት በሚል ስልታዊ አባባል ለአንድ ባለሀብት መወሰኑ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሮአል፡፡ ውሳኔው የአካባቢው
ህብረተሰብ ባለመቀበሉ የወረዳው ኃላፊዎች ህብረተሰቡን ሰብስበው ለማግባባት ቢሞክሩም ህዝቡ አንቀበልም በማለቱ በአካባቢው ውጥረት ነግሷል፡፡ በምርጫ 97 ኢህአዴግ ምንም አይነት ድምጽ ያጣበት አካባቢ በመሆኑ የአካባቢውን ህብረተሰብ እንደጠላት እያየ ከፍተኛ የሆነ አስተዳደራዊ በደል ሲፈጽምበት የቆየ አካባቢ ነው፡፡ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ምንጮች እንደሚሉት በአሁኑ ጊዜ የአካባቢውን ህብረተሰብ ነፃነቱ ሙሉ በሙሉ ተገፏል፡፡ ሁሉም ዜጋ የቁም እስረኛ ተደርጓል፡፡ ከሚኖርበት
ቀበሌ ወደየትኛውም ቀበሌ ለመሄድ ቢፈልግ ለአካባቢው ኃላፊዎች አሳውቆ የይለፍ ወረቀት መያዝ ይጠበቅበታል፡፡ የፍቃድ ወረቀት ሳይኖረው ከሚኖርበት ቀበሌ ተነስቶ ወደ ሌላ ቀበሌ ቢሄድ ይታሰራልብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment