Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 2 May 2012

ትላንት ንግድ ባንክ ገንዘባቸውን በሚያወጡ ደንበኞች ተጨናንቆ ዋለ.........ፍኖተ ነጻነት


በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ገንዘባቸውን በሚያወጡ ደንበኞች ሰልፍ ተጨናንቀው መዋላቸውን የዝግጅት ክፍላችን ተባባሪ ሪፖርተር ዘገበ፡፡ ሪፖርተራችን በተዘዋወረባቸው ተክለሃይማኖት፣ፒያሳና አራት ኪሎ በሚገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክቅርንጫፎች እንደተመለከተው በርካታ የባንኩ ደንበኞች ገንዘባቸውን ለማንቀሳቀስ እስከረፋድ በባንኮቹ በራፍ ላይ ተሰልፈ ነበር፡፡ ባንክቤቶቹ በአንፃሩ አገልግሎት ሳይሰጡ አርፍደዋል፡፡ ለባንኩ ቅርበት ያላቸው ምንጫችን ባንኩ የሲስተም ችግር ሳያጋጥመው እንዳልቀረ ጠቁመውናል፡፡ የዝግጅት ክፍላችን ጉዳዩን ከባንኩ ለማጣራት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

No comments:

Post a Comment