Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 2 May 2012

ኢህአዴግ በ አማራ ተወላጆች ላይ እየፈጸመ ያለውን የማፈናቀል ተግባር ቀጥሎበታል

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-እንደ ጋዜጣው ዘገባ፤በደቡብ ክልል በጉራ ፈርዳ ወረዳ ይኖሩ የነበሩ አማሮች ፦”ወደ አገራችሁ ሂዱ” ተብለው መባረራቸው ህዝባዊ ተቃውሞ ባስነሳበት
በሁኑ ጊዜ፤ በቤንሻንጉክ ጉሙዝ ክልል ይኖሩ የነበሩ የ አማራ ተወላጆችም ተመሣሳይ ዕጣ ገጥሟቸዋል።
እንዲሁም  በሰሜን ጎንደር ዞን ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው አርማጭሆ ወረዳ ውስጥ በኢብርሀጂራ  አካባቢ በእርሻ ሥራ  ተሰማርተው ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች የ እርሻ መሬታቸውን ተነጥቀው ሰሞኑን መባረራቸውን፤ የአካባቢውን አርሶአደሮች ተናግረዋል።
በድርጊቱ የተበሳጩት አርሶ አደሮች፦  ኢህአዴግ በአማራ  ላይ ጣቱን ቀስሯል”ሲሉ በምሬት መናገራቸውን ፍኖት ገልጿል።
ከተለያዩ ቦታዎች ከይዞታቸው እየተፈናቀሉ ያሉት አርሶአደሮች ምንም መቋቋሚያ  ስላልተሰጣቸው የከፋ ችግር ላይ እየወደቁ መሆናቸውም ተመልክቷል።
ከ አርማጭሆ አካባቢ ሰሞኑን የተፈናቀሉት አርሶ አደሮች፤ ከ1998  ዓመተ ምህረት ጀምሮ በስፍራው ሲኖሩ የቆዩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አርሶ አደሮች  ከይዞታቸው በሚነሱበት ጊዜ፦”መሬቱ በብሎክ ስለሚደለደል፤ ያለሰለስኩት ማሳዬ ስለሆነ ለኔ ይገባኛል “የሚል  ጥያቄ እንዳያነሱ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም ገልጸዋል።
 አርሶ አደሮቹ  የተፈናቀሉት መንግስት አካባቢውን  ቆርሶ ለሱዳን በመሰጠት በመወሰኑ እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህም ባሻገር፤በታች አርማጭሆ ወረዳ ፤ሳንጃ ውስጥ ለረጂም ዓመታት የቤተ-ክርስቲያን መገልገያ የሆነን ሥፍራ “ለልማት” ተብሎለአንድ ባለሀብት እንዲሰጥ በመወሰኑ ፤በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ መፈጠሩን  ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል ፡፡
የአካባቢው ህብረተሰብ በውሳኔው መቆጣቱ ያሣሰባቸው  የወረዳው ኃላፊዎች ህዝቡን ሰብስበው ለማግባባት ቢሞክሩም ህዝቡ በተቃውሞው በማምረሩ  በአካባቢው ውጥረት መንገሱን  ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ወረዳው፤ በምርጫ 97 ኢህአዴግ አንድም ድምጽ ያላገኘበት አካባቢ በመሆኑ ፤ ነዋሪው በተለይ  ከዚያን ጊዜ ወዲህ ባሉት  ዓመታት ከፍ ያለ አስተዳደራዊ በደል ሲፈጸምበት መቆየቱን የዜናው ምንጮች አስታውሰዋል።
 “በአሁኑ ጊዜ የአካባቢውን ህብረተሰብ ነፃነቱ ሙሉ በሙሉ ተገፏል፤ሁሉም ዜጋ የቁም እስረኛ ተደርጓል፡፡ ከሚኖርበት
ቀበሌ ወደ ሌላ ማናቸውም ቀበሌ ለመሄድ ቢፈልግ እንኳ፤ ለአካባቢው ኃላፊዎች አሳውቆ የይለፍ ወረቀት መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
የፍቃድ ወረቀት ሳይኖረው ከሚኖርበት ቀበሌ ተነስቶ ወደ ሌላ ቀበሌ ቢሄድ ይታሰራል” ሲሉም- በ አካባቢው  የሚታየው ውጥረት ምን ያህል የከፋ እንደሆነ ምንጮቹ ለማመልከት ሞክረዋል።
መንግስት በዋልድባ የስኳር ፋብሪካ ለመስራት የጀመረውን እንቅስቃሴ ተከትሎ  ውጥረት ነግሶ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን፤ ከሰሞኑ ደግሞ  የሰሜን ጎንደር ህዝብ ዶማ፣ አካፋና ጦር እየያዘ ወደ ስፋራው እየተመመ እንደሚገኝ  መዘገቡ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment