Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday, 2 May 2012

ምስራቅ ወለጋ ፎጌ ወረዳ….ፍኖተ ነጻነት


ለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ወለጋ ድንበርና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ድንበር ላይ በተፈጠረው ግጭት መፈናቀል ማስከተሉን የዜና ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ ምንጮቻችን እንደሚሉት በተፈጠረው ግጭት እስከአሁን ድረስ 26 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ግጭቱ በፈጠረው ከፍተኛ ሥጋት በአካባቢ መፈናቀልን አስከትሏል፡፡ይላሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የሚፈልጉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ እንደሚሉት በግጭት ከሦስት በላይ አባወራዎች ከመኖሪያ ቦታቸው ተፈናቅለው ወደ ምስራቅ ወለጋ ፎጌ ወረዳ ውስጥ የተሰባሰቡ ሲሆን የተወሰኑ ግለሰቦች ደግሞ ፋፊጋ በሬዳና በሎ በሬዳ በተባሉ ቀበሌዎች ተሰባስበው ለችግር ተጋልጠዋልብለዋል፡፡ እንደ ምንጮቻችን አባባል የአካባቢው ነዋሪዎች ቤታቸውንና ንብረታቸውን ጥለው የቤተሰባቸውን ህይወት ለማትረፍ በመሸሻቸው መጠለያ፣ ምግብና ውሃ እጥረት ገጥሞአቸዋል፡፡ እርዳታም ማግኘት ባለመቻላቸው ችግር ውስጥ ናቸው፡፡ሲሉ ያብራራሉ፡፡

No comments:

Post a Comment