Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 18 August 2012

የነበረከት ስምኦን አንጃ በአቦይ ስብሃት ላይ የሃያ አራት ሰአት ክትትል እንዲደረግባቸው ለደህንነት መመሪያ ሰጠ






ከቅርብ ግዜ ወዲህ በባህሪያቸው የማን አለብኝነትን ባህሪ እያሳዩ የመጡትን አቦይ ስብሃትን የማያቋርጥ ክትትል እንዲደረግባቸው እና ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ በበረከት ስሞን ከሚመራው አንጃ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልጠውልናል።
 
ይህንን በማያያዝም አቦይ ስብሃት ነጋን ያሞጋግሱ የነበሩ ማናቸውም አይነት ጽሁፎችም ሆኑ ቃለመጠይቆች የህውሓት አቀንቃኝና ደጋፊ ከሆኑ ድህረ ገጾች ለይ ተለቅመው እንዲነሱም መመሪያ ተሰጥቷል።

ይህንን በመከተል በአይጋፎረም፣ ትግራይ ኦንላይን እንዲሁም ዋልታ ኢንፎርሜሽን ድህረ ገጽ ላይ በቅርብ ግዜ ተለጥፈው የነበሩ የአቦይ ስብኃት ከቪኦኤ እና ከዶቾቬሌ ጋር እርገዋቸው የነበሩ የአቶ መለስን ጤንነት የሚመለከቱ ቃለምልልሶች መነሳታቸውን ልናረጋግጥ ችለናል በመሆኑም ከአሁን በኋላ ምንም አይነት ቃለ ምልልስ ከማንኛውም ሚዲያ ጋር እንዳያደርጉም ከአቶ በረከት አንጃ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቶአቸዋል።

ከቅርብ ግዜ ወዲህ አቦይ ስብሃት ማንንም ባለመፍራት አቶ መለስንና ሚስታቸውን ጨምሮ ማንኛውንም ሰው በሃይለ ቃል እየዘለፉ እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ሲሆን በተለይ ከአቶ መለስ መሰወር ጋር የሚሰጧቸው ቃለመጠይቆች የተደበቀውን ሚስጥር እንዳይወጣ ሌት ከቀን የሚለፉትን የአቶ በረከት አንጃን ክፉኛ አስቆጥቷል በመሆኑም የአቦይ ስብሃት ነጋን እንቅስቃሴ ከሚታገሱት በላይ ሆኖብናል ይላሉ።

ጥያቄው አቶ ስብሃት ነጋ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ይተገብራሉ ወይስ የሚለው አጓጊ ሆኖአል? ቀጣይ ሂደቶችንና ክንውኖችን እየተከታተልን እናቀርባለን።

1 comment: