Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday, 16 August 2012

የአቶ መለስ ጉዳይ ዛሬም አለየለትም

         -“በዚህ የሚጠመዘዝ የዓረና/መድረክ አባል የለም”-አቶ አስገደ /ስላሴ
      -“በህይወት ካሉ ለምን በቴሌቪዥን አለሁ አላሉም?”- የአዲስ አበባ ነዋሪዎች  
-“በስልጣን ሽኩቻው ዙሪያ ገና በጉባዔ ነው የሚወሰነው”- አቶ ስብሐት ነጋ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የጤና ጉዳይ ዛሬም አለየለትም፡ በተለያዩ ዓለም አቀፍ እና የማኅበረሰብ ብዙኃን መገናኛ ላይ በአቶ መለስ ዜናዊ ጤና ዙሪያ የተለያዩ መረጃዎች እየተዘገቡ ይገኛሉ፡፡

ባለፈው አንድ የግብፅ ከፍተኛ ባለሥልጣንቢኪያ ሞሳርለተባለ ድህረ ገጽ አዲስ ከሚመጣው የኢትዮጵያ አመራር ጋር በተሻለ ሁኔታ እንሰራለንማለታቸውን ተከትሎ የአቶ መለስ የጤና ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እንዳደረገው ያነጋገርናቸው አንዳንድ የአዲስ አበባና የክልል ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢህአዴግ ቁልፍ ሰው እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ስብሐት ነጋ ባለፈው ከጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታየስልጣን ሽግሽግ ላይ እንዳለ የሚያመላክት እሳቤን አንፀባርቀዋል፤ ይህ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላ አይሰሩም የሚል ድምዳሜን ያሳያልሲሉ ገልፀዋል፡፡

በአሁን ወቅት ደግሞ በኢህአዴግ ውስጥ የስልጣን ሽኩቻ እንዳለ እና የነ አቶ ስብሐት ነጋ ቡድንም በዓረና ትግራይ /መድረክ ውስጥ ያሉ የቀድሞ የህወሓት አባላትን እያነጋገሩ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ይህን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የቀድሞ የህወሓት መስራች አባል የነበሩና የአሁኑ የዓረና /መድረክ አመራር የሆኑት አቶ አስገደ /ስላሴ የአቶ ስብሐት ነጋ ቡድን መጥቶ ያነጋገረን የለም በዚህ የሚጠመዘዝ አንድም የዓረና /መድረክ አባል የለም፤ በዓረና ውስጥ ያለን የቀድሞ የህወሓት መስራች አባላትም 30 አንበልጥምሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ስብሐት ነጋ በበኩላቸውበስልጣን ሽግሽግ ዙሪያም ሆነ ከዓረና/መድረክ አባላት ጋር የተነጋገርነው ነገርም የለም፣እኔ ገና ከውጭ መግባቴ ስለሆነ ለኔም አዲስ ነገር ነው፤ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሚመለከት አቶ በረከት ስምዖንን ጠይቋቸው፣ አለ በሚባል በየስልጣን ሽኩቻ ዙሪያ የህወሓት መደበኛ ጉባዔ ገና ስለሆነ ያኔ ነው በጉባዔ የሚወሰነውሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡

በተለይ ያነጋገርናቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳሉት ከሆነኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ ምን ያህል እንደናቀ በተግባር አረጋግጦልናል፤ ለዚህም ማሳያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም ከእኛ ተደብቆ ከውጭ ሀገር ከሴኔጋሉ ፕሬዘዳንት ሰማን፤ አሁን ደግሞ ምን ላይ እንዳሉና ሀገሪቱ በማን እየተመራች እንዳለች አመራሮቹ እየደበቁን ሳለ የግብፅ ባለሥልጣን በኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ አመራር ሊመጣ እንደሆነ በተዘዋዋሪ ነግረውናልሲሉ ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡  

ስማቸውን መግለፅ ያልደፈሩ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ አመራር በበኩላቸውህዝቡ ስለመሪውም ሆነ ስለሀገሪቱ ምንነት የማወቅ መብቱን ተነፍጓል፤ እውነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ  እየተመለሰ ከሆነ ለምን በቴሌቪዥን መስኮት ለህዝቡ አለሁ፣ አላሉም? ይሄ እኮ ያለ ነው፣ ሰው ሆኖ የማይታመም የለምሲሉ ትዝብታቸውን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውምእኔ የጠቅላይ ሚኒስትሩን በህይወት መኖር ራሱ እጠራጠራለሁ፤ ምክንያቱም ቢያንስ እንደ ኩባው የቀድሞ ፕሬዘዳንት ፊደል ካስትሮና እንደ ቬንዙዌላው ሁጐ ቻቬዝ አሊያም እንደቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት እየታከሙ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው መግለጽ ይሳናቸዋል የሚል እምነት የለኝምናብለዋል፡፡

የሚወራውን በተመለከተ የሚመለከታቸው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን ያለውን እውነታ እንዲነግሩን ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ስልካቸውን ሊያነሱልን አልቻሉም፡፡ ምክትላቸው የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማልን ያገኘናቸው ቢሆንም ስለጉዳዩ ካነሳንላቸው በኋላ መልሳችሁ ደውሉልኝ ብለው የሰዓት ቀጠሮ የሰጡን ሲሆን የዝግጅት ክፍሉም ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ስልካቸውን ደግመው ባለማንሳታቸው የመንግስትን አስተያየት ማካተት አልቻልንም፡ ከዚህ በፊት አቶ በረከት ስምዖን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህክምናቸውን ጨርሰው በቅርቡ ወደ ስራቸው ይመለሳሉ ብለው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡




No comments:

Post a Comment