Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 25 April 2012

በሶማሊያ በቦምብ ፍንዳታ 2 የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገደሉ

ሚያዚያ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሶማሊያ በቦምብ ፍንዳታ 2 የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገደሉ፤በአፀፋዉ ሰላማዊ ዜጎችን ገደሉ        
በሶማሊያ በለደ-ወይኒ ከተማ በመንገድ ዳር በተጠመደ ቦምብ ሁለት የኢትዮጵያ ወታደሮች ሲገደሉ በሰባት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን በስፍራዉ የነበሩ የዓይን ምስክሮች መግለፃቸዉን ሬዲዮ ጋራዌ የመረጃ ምንጭ አስታዉቋል።
በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ 3 በአካባቢዉ የነበሩ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸዉና ከሟቾቹ መካከል ሶስተኛዉ ህይወቱን ለማትረፍ የሸሸዉ ሰዉ በወታደሮቹ ማሳደድ የተገደለዉ መኖሪያ ቤቱ አካባቢ እንደደረሰ መሆኑ ታዉቋል።
ከዚሁ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ባላዱል-አሚን ተብሎ በሚጠራዉ የአካባቢዉ መንደር ዉስጥ ነዋሪ የሆኑ 2 ሌሎች ሰዎችን ከመኖሪያ ቤታቸዉ በማዉጣት የኢትዮጵያ ወታደሮች መግደላቸዉን አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአይን ምስክር መግለፃቸዉን የዜና ምንጩ በተጨማሪ አስታዉቋል።
ባለፈዉ አመት የኢትዮጵያ ወታደሮች በለደ-ወይኒን ከአልሼባብ አማፅያን ካስለቀቁ ወዲህ በአካባቢዉ የሰብኣዊ መብት ረገጣና ህገወጥ/የጅምላ ግድያ መፈፀማቸዉን በመጥቀስ አለምአቀፉ የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች መክሰሱ ይታወቃል።  
የአልሸባብ የጥቃት እንቅስቃሴ መቀነሱ ሲታወቅ የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያን ለቆ እንደሚወጣ ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ መግለፃቸዉን የዜና ምንጩ አመልክቷል።

No comments:

Post a Comment