Dawit Wasihun
ጸሃፍት
ወይም ጋዘጠኛ አይደለሁም ነገር ግን እንዳቅሜ ሰዎች የጻፏትንና እኔም የምሞክራትን ጽሁፍ የማሰፍርባት አንድ ብሎግ ከፍቼ ወደ አንድ
ወር አስቆጥሬያለሁ ከአገር ቤትም ሆነ ከውጭ ብዙ ወዳጆች አፍርቼባታለሁ ሲጻፍ እለጥፋለሁ ሰውም አንብቦ አስተያየቱን ይሰጠኛል እኔም
እቀጥላለሁ…ጠዋት እንደተለመደው ፌስቡኬን ስክፍት አንድ ወዳዴ ከአገር ቤት ብሎጌ እገታ እንደደረሰባት አረዳኝ ደግሞ እንዲሞክር
ብጠይቀው ይህንኑ አረጋገጠልኝ ለመሆኑ የኔብቻ ነው ወይስ የሌሎችም ስለው የአቤ ቶክቻው፤ የተስፋዬ ገብረአብ እና የወዳጄም ብሎግ
እገታ እንደደረሰበት አረዳኝ ላምን አልችልኩም ምክንያቱም የተጠቀሱት ጸሃፍት የገነነ ስም አላቸው ወዳጄም ቢሆን ቀላል የሚባል ሰው
አይደለም እኔ ግን ከምን ገብቼ ነው፤ ይህ የሚያሳየኝ መልካም ስራ እየሰራሁ እንዳለ ነው።
ለውድ የብሎጌ አንባብያን ይህንን ጽሁፍ እስከማዘጋጅ
ድረስ ብሎጌ እንደታገደ ነው እስከ 24 ሰአት ምንም ለውጥ ከሌለ አዲሱን ብሎጌን የማስተዋውቅ መሆኑን በአክብሮት እገልጻለሁ።
No comments:
Post a Comment