Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday, 26 April 2012

ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሞግዚት እየተመራ እንደሆነ ተጠቆመ............ፍኖተ ነጻነት


በሕዝብ ብዛትና በቆዳ ስፋት የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዘው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሞግዚት እየተመራ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን ገልፁ፡፡ ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚሉት ክልሉ በህገ መንግሥትና በህጋዊ የህዝብ ተወካዮች በሚመሠረት ክልላዊ የመንግሥት አስተዳደራዊ መዋቅር እንዳለው ቢታወቅም በየደረጃው የተቀመጡት ባለሥልጣናት በሙስና በመዘፈቅ፣ኢ-ፍትሐዊ ውሳኔ በመወሰን፣በቡድን በመደራጀት ወደ ተለያየ አቅጣጫ በመጓተት አለመግባባት ይታያል፡፡ የክልሉ ፕሬዝዳንት አጀንዳ ለማስያዝ የማይችሉበት ሁኔታዎች አሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ከክልሉ ውጪ ባለ ግለሰብ የክልሉ መስተዳድር በትዕዛዝ እየተመራ ነው፡፡በማለት በቅሬታ ይገልጻሉ፡፡ የውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚሉት የክልሉ ፕሬዝደንት እንደማንኛውም የኦህዴድ አባላት የተዛባ የፖለቲካ አመለካከት፤ኢ-ፍትሐዊ የአስተዳደር መርህን የሚከተሉ፤ጎጣዊ የጎሳ አመለካከት አለባቸው እየተባሉ ቢታሙም በግለኝነት፣በራስ ወዳድነትና
በሙስና የማይጠረጠሩ ናቸው፡፡ እንዲያውም ሙሰኞችን አምርረው በመታገላቸውና አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰዳቸው የሙሰኞቹ ቡድን ህይወታቸውን እስከማጥፋት ሙከራ ያደረጉባቸው ከመሆኑም በላይ በድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ
አጀንዳ እንዳያሲዙ ሁሉ ተጽኖ ስለሚደረግባቸው በክልሉ መስተዳድር አመራር ላይ ተጽኖ ፈጣሪ መሆን አልቻሉም፡፡ሲሉ ያብራራሉ፡፡ ምንጮቻችን አያይዘውም ሲዘረዝሩ በአሁኑ ጊዜ ክልሉን የሚመሩት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ሳይሆኑ /ሚኒስትሩ /ቤት የሚገኙት አቶ /ተንሳይ /ተንሳይ የተባሉ ግለሰብ ናቸው፡፡ይላሉ፡፡ ከዚህ በፊት አቶ ሰለሞን ተስፋዬ (ሰለምን ጢሞ) ኦህዴድ /ቤት ቢሮ ከፍተውና ተቀምጠው ድርጅቱንም የክልሉን የመንግሥት
አመራር እግር በእግር እየተከታተሉ፣እየገመገሙና አመራር እየሰጡ ይመሩ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ አቶ /ተንሳይ /ተንሳይ ቢሮአቸውን /ሚኒስትሩ / ቤት ውስጥ አድርገው ከዚህ በፊት ሰለሞን ጢሞ ሲሰራ የነበረውን ሥራ ተክተው እየሠሩ ናቸው፡፡ በክልሉ ውስጥ ተደማጭነትና ተቀባይነት ያለው የክልሉ ፕሬዘዳንት ትዕዛዝና መመሪያ ሳይሆን የአቶ /ተንሳይ መመሪያና ትዕዛዝ ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬም ኦሮሚያ በሞግዚት አስተዳደር እየተመራ ነው፡፡ በማለት ቅሬታቸውን ይገልጻሉ፡፡ በጉዳዩ ላይ የክልሉን ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳንና የአቶ /ተንሳይ ሐሳብን ለማካተት ያደረግነው ሙከራ
ለጊዜው አልተሳካል፡፡

1 comment:

  1. የመድኃኒት ንግድ ሥራዬን ለማስፋፋት በተጠቀምኩበት ብድር ለመርዳት ሚስተር ቤንጃን ከሚያስፈልጓቸው በላይ አልፈዋል ፡፡
    እነሱ ለመስራት ወዳጃዊ ፣ ባለሙያ እና ፍጹም ዕንቁዎች ነበሩ ፡፡ እኔ ለማነጋገር ብድር የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው እመክራለሁ ፡፡ Lfdsloans@outlook.com.WhatsApp ... +19893943740.

    ReplyDelete