ሰለሞን
ስዩም…ፍኖተ ነጻነት
ሚያዚያ
9/2004 ዓ.ም
አቶ
መለስ
ዜናዊ
በፓርላማቸው” የተለመደውን
‹‹የተጠየቁ›› ጥያቄዎችን
ባሻቸው
መንገድ
የመመለስ
ትርዒት
አካሂደዋል፡፡
ሙስናና
ኪራይ
ሰብሳቢነት
የመንግሥታቸው
አደጋ
መሆኑ
ክፉኛ
ያሳሰባቸው
ቢመስልም
በተለመደው
ሁኔታ
በቃል
ብቻ
በማውገዝ
አልፈዋል፡፡
ለነገሩ
ከዚህ
የሚዘሉ
ከሆነ
እርምጃው
ከቤታቸው
መጀመሩ
ይቀራል?
ነገር
ግን
ማውገዝ
ብቻ
የሚበቃው
አይመስለኝም፡፡
ፀረ-
ሙስና
ኮሚሽን
ያዘጋጀውን
የኢህአዴግ
ባለሥልጣናት
የንብረት
መዝገብ
ለህዝብ
ይፋ
ይደረግ፡፡
በመጀመሪያ
ፀረ
ሙስና
ኮሚሽን
የመዘገበው
ትክክል
ነው
ወይስ
አይደለም?
የሚለውን
ሕዝቡ
ይመረምራል፡፡
ሕዝቡ
በየዕለቱ
ከሚያየው
ጋር
ያነፃፅረዋል፡፡
መረጃው
ትክክል
ሆኖ
ከተገኘም
በህገ
ወጥ
መንገድ
የተገኘው
ገንዘብና
ንብረት
ለህዝብ
ተመልሶ
ሌቦቹ
ትክክለኛ
ፍትህ
ሊሰጣቸው
ይገባል፡፡
አሁንም
ወደ
ቤታቸው
ማምራቱ
መች
ይቀራል፡፡
አቶ
መለስ
መንግስት
የዋጋ
ንረቱን
ለመቀነስም
እየሰራ
መሆኑን
ገልፀዋል፡፡
የሥራ
ዉጤቱ
ግን
የለም፡፡
መሠረታዊ
ዕቃዎችን
መንግሥት
ከውጭ
ያስመጣል
ብለዋል፡፡
ታዲያ
ምን
አይነት
የኢኮኖሚ
ስርዓት
ነው
የገነቡት?
በማዕከላዊ
ፕላን
የሚመራ
ወይስ
በነፃ
ገበያ
የሚሰራ
ነው?
የዋጋ
ንረት
መንስዔዎችን
አሁን
አማካሪዎቹ
በደንብ
አይናገሩም
እንዴ?
በሀገራችን
ዋናው
የዋጋ
ንረት
መንስኤ
ብሔራዊ
ባንክ
በገፍ
እያሳተመ
ለመንግሥት
የሚያቀብለው
ገንዘብና
ሌሎች
ባንኮች
ለመንግሥት
የሚያበድሩት
ከፍተኛ
ብድር
ነው፡፡
ካድሬዎቹም
ጠቅላይ
ሚኒስትሩም
ብዙ
ጊዜ
የሚጠቅሷቸው
መንስኤዎች
ዓበይት
ሳይሆኑ
ንዑሶች
ናቸው፡፡
ለምሳሌ
ከውጭ
የሚዛመት
የዋጋ
ንረትን
አንድ
መንስኤ
ትጠቅሳላችሁ፡፡
ይህ ደግሞ
በመንግሥት
መረጃም
ከ5
በመቶ
በልጦ
አያውቅም፡፡
በውጭ
ምንዛሬ
ከውጭ
ሀገር
እቃዎችን
ማስመጣት
ስለሚቻል
ይህ
በዋጋ
ንረት
ላይ
የሚኖረው
ተፅዕኖ
ኢምንት
ነው፡፡
ምርት
ሁለት
አሀዝ
(double digit) ዕድገት
አሳይቷል
ባላችሁበት
አንደበት፣
የዋጋ
ንረቱ
አንደኛውና
ዋናዉ
መንስኤ
የምርት
አቅርቦት
ማነስ
ነው
ትላላችሁ!
ይህ
ከሆነ
ምርት
በሁለት
ድጂት
ቀርቶ
የአንድ
ድጂት
አጋማሽ
ድረስ
አላደገም
ማለት
እኮ
ነው፡፡
ድፍረት
ባይሆን
እኔ
ምክር
ልስጥ፤
የመንግሥት
የልማት
ፕሮጀክቶችን
ወጪ
ቀንሱ፤
ብሔራዊ
ባንክን
ጨምሮ
መንግሥት
ከማንኛውም
ባንክ
የሚበደረውን
ገንዘብ
መቀነስ
አሊያም
ጨርሶ
ማቆም
አለበት፡፡
የወለድ
መጠንን
ከፍተኛ
በሚባል
መጠን
መጨመር፡፡
አሁን
ካለበት
5 በመቶ
(በባንክ
ተቀማጭ
ገንዘብ
ላይ)
ወደ
ስምንት
በመቶ፣
ከዚያም
ሁኔታው
እየታየ
ወደ
አሥር
በመቶና
ከዚያ
በላይ
ቢሆን
ከግሽበቱ
የባሰ
ተፅዕኖ
አይኖረውም፡፡
ከተቀነሰው
የልማት
ፕሮጀክቶች
ወጪ
ላይ
በተለይ
የኑሮ
ውድነቱ
ለናጠው
የመንግሥት
ሰራተኛ
ደመወዝ
ማዋል፡፡
ነገር
ግን
አቶ
መለስ
ይህንን
ማድረግ
አይፈልጉም፡፡
ምክንያቱም
ኑሮ
የፈለገውን
ያክል
ቢወደድ
የመንግሥት
የልማት
ፕሮጀክቶች
ለውጥ
ካሳዩ
በነፃ
ምርጫ
ያላገኙትን
የሕዝብ
ፖለቲካዊ
ይሁን (legitimacy)
ይሰጠኛል
የሚል
አቋም
ያራምዳሉና፡፡
ለመምህራኑ
የተደረገውን
የደመወዝ
እርከን
ማስተካከያ
በተመለከተ
አቶ
መለስ
ከመምህራኑ
99.9 በመቶ
ተቀብለውታል
ነው
ያሉት፡፡
ይህች
የይሁንታ
ምጣኔ
ከ99.6
በመቶ
መብለጧ
በጣም
አስገርሞኛል፡፡
ኢህአዴግ
በ2002
ምርጫ
በ99.6
በመቶ
አሸንፌአለሁ
ብሎ
ነበር፡፡
ታዲያ
99.9 በመቶው
በሚቀጥለው
ዓመት
እንደሚደረግ
በሚጠበቀው
በአዲስ
አበባ
ምርጫ
የሚያሸንፍበት
መጠን
ይሆን?
የአቶ
መለስ
ካድሬዎች
እና
ሰላዮች
የደረሷቸዉ
መረጃ
በእጅጉ
የተሳሳተ
መሆኑን
መግለፅ
የዜግነት
ግዴታዬ
ይመስለኛል፡፡
ዘንድሮ
“አዲስ
ዘመንንም
አዲስ
ነገርንም
አላነብም” የሚሉበት
ጊዜ
አይደለም፤
ለማንኛውም
የደረስዎት
መረጃ
የተገላቢጦሽ
ነው፡፡
መምህራኑ
በተደረገው
እጅግ
አነስተኛ
የደመወዝ
ማስተካከያ
99.9 በመቶው
ነው
የበሸቁት፡፡
እውነቱን
ለመናገር
እኔ
መምህር
ብሆን
የምበሽቀው
በጭማሪው
ብቻ
ሳይሆን
በደመወዙም
ጭምር
ነው፡፡
በአዲስ
አበባ
በ1300
ብር
(የተጣራ)
ደመወዝ
ከወር
እስከ
ወር
መድረስ
ይቻላል?
ይቻላል
ከሆነ
ከእውነታው
እጅግ
ርቀዋል
ማለት
ነው፡፡
እኔ
በበኩሌ
1300 ብር
ለአስር
ቀን
እንኳ
አይበቃኝም፡፡
የጫትና
የመጠጥ
ሱስ
ያለብኝ
እንዳይመስል
ታዲያ!
አልጠጣም፣
አልቅምም፤
ደግሞም
አላጨስም፡፡
ሌላው
አስገራሚ
ነገር
“ከመቼ
ወዲህ
ነው
ህብረተሰቡ
መምህራንን
መቅጠርና
ማባረር
የመጀመረዉ?›› አቶ
መለስ
ማስመሰል
እያቃታቸው
ነው፡፡
አቶ
መለስ
ስለ
ሀይማኖት
የተናገሩት
ለአብዛኞቹ
ወዳጆቼ
አልጣማቸውም፡፡
ሙስሊሙ
በኢትዮጵያ
እስላማዊ
መንግሥት
እናቋቁም
ሳይሆን
ሙስሊሙ
ሙጅሊሱን
ይምረጥ፤
የአወሊያ
ት/ቤቶችም
መወሰን
ያለባቸው
በህዝብ
በተመረጠ
ሙጅሊስ
መሆን
አለበት
የሚል
መሆኑን
ያስረዳሉ፡፡
ክርስቲያኖችም
የሚጠይቁት
ቢሆን
ተመሳሳይ
ነገር
መሆኑን
አብዛኛው
ምዕመን
ያነሳል፡፡
መንግሥት
ባለፉት
20 ዓመታት
በኃይማኖት
ጉዳይ
ያራመደው
ፖሊሲ
ዛሬ
ሊከፋፍለን
ፍንጭ
በማሳየቱ
ንፁህ
ነኝ
ማለት
የቱ
ጋ
ነው?
አቶ
መለስ
ውሸትን
እውነት
የማስመሰል
ብቃታቸው
እንደከዳቸው
ያወቅሁት
የጉረፈርዳ
ተፈናቃዮችን
ባነሱበት
ጊዜ
ነው፡፡
የአማሮቹ
መፈናቀል
ተራራ
የሚያህ
እውነት
ሆኖ
ሳለ
አቶ
መለስ
ለመቀበል
መቸገራቸው
ምን
ይባላል?
ደን
ጨፈጨፉ
ማለት
ከቦታው
ይፈናቀሉ
ነው
ወይስ
በህግ
ፊት
ይቀርባሉ?
ለነዚህ
ሰዎች
የቸገረዉ
እኮ
በራሳቸዉ
ሀገር
የሌላ
ሉዓላዊ
ሀገር
ድንበር
እንደጣሰ
እዚያ
መገኘታቸዉ
በራሱ
ወንጀል
መሆኑ
እኮ
ነዉ፡፡
ለነገሩ
ሰዉየዉ
ማስመሰሉ
ትቷቸዉ
መብረሩን
ያወቅሁት
አንዱን
ጉዳይ
ብቻ
መናገራቸዉን
እየረሱ
ሲደጋግሙትና
ከአፋቸዉ
ይልቅ
በእጅ
መናገር
ማስቀደማቸዉን
ሳይ
ነዉ፡፡
No comments:
Post a Comment