Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday 26 April 2012

በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ግጭት 22 ሰው ሞተ......ፍኖተ ነፃነት


በኦሮሚያ ክልልና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ድንበር ላይ ሰሞኑን በተፈጠረው ግጭት 22 ሰው ሲሞት በርካታ ሰዎች ቆስለው በለቀምት ሆስፒታል በመታከም ላይ መሆናቸው አካባቢው ነዋሪዎች ለዝግጅት ክፍላችን ገለፁ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች  ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት ከሆነ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ልዩ ሥፍራው ጊዳ ኪራሞ እና ጊዳ አያና በተባሉ ወረዳዎች የተነሳው ግጭት መንስዔ አቤንቱ፣ ቄሎና ዋስኪ የተባሉ አካባቢዎች የይገባኛል ጥያቄ ነው፡፡ ከዚህ በፊት 2000 . የተፈጠረውና 200 ሰዎች የህይወት መጥፋት፣ለበርካቶች መቁሰልና መፈናቀል ምክንያት ከነበረው ግጭት የቀጠለ ነው፡፡ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ጨምረው እንደሚሉት ለዘመናት በጉርብትና በሠላም ይኖር የነበረው ሕዝብ መሀከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተፈጠረ ያለው ግጭት የኢህአዴግ የዘር ፖለቲካ የወለደው ነው፡፡ብለዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች አክለውም አካባቢው ሠላም እንዳይሆን ህብረተሰቡም ተግባብቶና ተዛዝኖ እንዳይኖር የኢህአዴግ
ካድሬዎችና የደህንነት አካላት በየጐሳቸው ግጭት እንዲፈጠር ካነሳሱ በኋላ ከወስጥ ይወጣሉ፡፡ካሉ በኋላ ለተፈጠረው ግጭት፣
ለጠፋው ህይወትና ለወደመው ንብረት ተጠያቂዎቹ የአካባቢው ኃላፊዎችና ሥርዓቱ ነው፡፡ብለዋል፡፡ ምንጮች አያይዘውም ሲገልጹ በአሁኑ ወቅት አካባቢው በከፍተኛ ጥበቃ ውስጥ ይገኛል፡፡ ጉዳዩ ወደ ወጪ እንዳይወጣ ተብሎ ማንም ሰው ወደዚህ አካባቢ እንዲገባ አይፈቀድም፡፡ የችግሩ ፈጣሪዎች የማይመለከታቸውን ሰዎች ተጠያቂ ለማድረግ እና ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን እየተሯሯጡ ይገኛሉ፡፡ እጃቸው በጉዳዩ ውስጥ የሌሉ የመንግሥት ኃለፊዎች ጉዳዩ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ አጥፊዎቹ ለህግ እንዲቀርቡ እንዲደረግልን በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚከሰተው ግጭት የመጨረሻ እልባት ያገኝ ዘንድ የሁለቱ ክልል መንግሥታትና የፌዴራሉ መንግሥትም ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራ ጥሪያችንን አቅርቡልን፡፡በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ለአካባቢው ኃላፊዎችና ለፌዴራል ጉዳዮች በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

No comments:

Post a Comment