Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday, 26 April 2012

በጋሞ ጐፋ ዞን ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ...ፍኖተ ነጻነት


በጋሞ ጐፋ ዞን መለኮዛ ወረዳ ለሀ ከተማ በተነሳ ግጭት አንድ ሴት እና አንድ ወንድ በታጣቂዎች መገደላቸውን የደቡብ ክልል
ምንጮች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡ የአንድነት የደቡብ ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት ግጭቱ የተከሰተው ሰኞ ሚያዝያ 8 ቀን 2004 . ሲሆን የግጭቱ መንስኤ ህዝቡ ከማንነት ጥያቄና ከመልካም አስተዳደር እጦት ጋር
በተያያዘ ባነሳው ተቃውሞ ነው፡፡ ከአካባቢው ያሰባሰብናቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ህዝቡ ማንነቱ እንዲታወቅለት ያቀረበው ጥያቄ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ በመጡ ኃላፊዎች መሎ የሚባል ብሔር የለም የሚል ውሳኔ በመወሰኑ ህዝቡ ተቋውሞውን በሰላማዊ መንገድ ገልፃóል፡፡ ሆኖም የአካባቢው ታጣቂዎች ለተቃውሞ በወጣው ህዝብ ላይ ተኩስ በመክፈታቸው ከህዝቡ መካከል ሁለት
ሰዎች ተገድለዋል፡፡ የአካባቢው ምንጮችም በሰጡት አስተያየት ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ ተኩስ ከፍተው ግድያ የፈፀሙት አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ህጋዊ እርምጃ ካልተወሰደ የሟቾችን አስክሬን ላለመቀበል በመወሰኑ ከሦስት ቀን ላላነሰ አስክሬኖቹ በጤና ጣቢያ እንደተቀመጡ አስረድተዋል፡፡ አክለውም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የወረዳው የፖሊስ አዛዥ እና አንድ ሌላ ታጣቂ
በግድያው ተጠርጥረው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የአካባቢው ህዝብ የማዳበሪያ እዳ በአንድ ጊዜ እንዲከፍል እንዲሁም ተጨማሪ ማዳበሪያም በግዳጅ እንዲገዛ በአካባቢው አስተዳደር እና በፖሊስ መገደዱን በመቃወም የካድሬዎች መግቢያያላቸውን ዋና ዋና የመኪና መግቢያ መንገዶች በመዝጋት ተቃውሞውን የገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አካባቢው በፀጥታ ኃይሎችና ደህንነቶች መከበቡን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ በደቡብ ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማዳበሪያ ዕዳ ምክንያት በሚወስዱ እርምጃዎች መንስኤ በርካታ ዜጐች ህይወታቸውን ማጣታቸውንና መሰወራቸውን አቶ ዳንኤል ሺበሺ አስታውሰዋል፡፡ ስለጉዳዩ ለማጣራት የዞኑ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳይ
መስሪያ ቤቶች ጋር ጥረት ብናደርግም ለጊዜው አልተሳካም፡፡

No comments:

Post a Comment