Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Friday 10 August 2012

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተከሰሰ

ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
Feteh Newspaper owned and editorTemesgen Desalegnኢሳት ዜና:-በማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ሥራ ድርጅት አማካይነት በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት እየታተመ ለንባብ የሚበቃው የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝና ድርጅቱ ሶስት ክሶች ዛሬ ተመሰረቱባቸው፡፡
የፌዴራሉ አቃቤ ህግ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት ክስ የመሰረተባቸው በፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ እና በማስተዋል የህትመት እና ማስታወቂያ ስራ ድርጅት ላይ ነው።
አቃቤ ህግ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የመሰረታቸው ሶስት ክሶች ማለትም  ወጣቶች በአገሪቱ መንግስትና ህገ መንግስታዊ ስርአቱ ላይ እንዲያምጹ የመገፋፋትና ግዙፍ የሆነ የማሰናዳት ተግባር፣  የሀገሪቱን መንግስት ስም ማጥፋት እና የሀሰት ውንጀላ እንዲሁም የሀሰት ወሬዎችን በማውራት ህዝብን በማነሳሳት ወይም አስተሳሰባቸውን ማናወጥ የሚሉ ናቸው።
የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው በጋዜጣው የነሃሴ 23 ቀን ቅጽ 04 ቁጥር 149 እትም ላይ “ሞት የማይፈሩ ወጣቶች” በሚል ርዕስ የአጼ ሃይለስላሴን ስርአት ወጣቶች እንዴት እንዳፈረሱት እና አሁን ያለው ስርአትም አፋኝ እና ጨቋኝ መሆኑን በመግለጽና አሁንም ሞት የማይፈሩ ወጣቶች መኖራቸውን ጠቅሶ በአረቡ አለም የተከሰቱ የህዝብ አመጾችን በሀገራችን እንዲተገበር በማሰብ ወጣቶች አደባባይ ለአመጽ እንዲወጡ በጽሁፍ ቀስቅሷል ይላል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መከሰሱን የሰማው ከሬዲዮ ፋና መሆኑ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment