Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Friday, 10 August 2012

የአቶ መለስ መሰወር የስልጣን ሽኩቻና ፍርሀትን ጋርጧል ተባለ

የአቶ መለስ ለረጅም ግዜ ከስልጣን መሰወር፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ድብቅ የስልጣን ሽኩቻ፤ በአፍሪካው ቀንድ ደግሞ፤ ፍርሀትን እንደፈጠረ ፋይናንሳል ታይምስ የተሰኘው ጋዜጣ ዘገበ።
መንግስት አቶ መለስ ከሕመማቸው እያገገሙ እንደሆነ ቢናገርም፤ የአቶ መለስ ዜናዊ መሰወር ግን የጎሳ ፖለቲካን አደጋዎች እንዲያገጡ በሚያደርግና፤ ስርአቱን ለአደጋ በሚያጋልጥበት መለኩ ድብቅ የስልጣን ሽኩቻን ጭሯል ሲል ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል።
“ስለአቶ መለስ ጤና ሁኔታ ምንም አይነት መረጃ የለንም” ያለው፤ የኬንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ፤ “ግልጽ የስልጣን ተተኪ ባለመኖሩና የዚያች አገር ፖለቲካ በቋፍ በመሆኑ፤ ሁኔታው አሳስቦናል” ሲሉ ተናግረዋል።
ተቃዋሚዎችን ቢያፍኑም፤ ጋዜጦችን ቢዘጉም፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከምርጫ ጋር በተያያዘ ቢገድሉም፤ እንዲሁም ሕዝቡን በድህነት ቢይዙም፤ አቶ መለስ የምእራባዊያን መንግስታት ድጋፍ አላቸው ያለው ፋይናንሺያል ታይምስ፤ አንድ ምእራባዊ ዲፕሎማትን ጠቅሶ፤ “ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ባላቸው ሚና፤ እንደበርማ ከመወገዝ ተርፈዋል” ሲሉ አትቷል።
ኢትዮጵያ በይስሙላ የአራት ፓርቲዎች ግንባር በሆነው ኢህአዴግ የምትመራ፤ ነግር ግን በአቶ መለስ የሚመራው ሕወሀት አብላጫውን ስልጣን የያዘባት አገር እንደሆነችና፤ አንዳንዶች አቶ መለስ ባይኖሩም ችግር አይፈጠርም ቢሉም፤ አቶ መለስ ባላቸው ሰፊ ስልጣን የተነሳ፤ ለረጅም ግዜ በዙሪያቸው ያሉትን ሰዎች እንዳሻቸው ሲሾሙና ሲሽሩ ስለኖሩ፤ እሳቸውን የመተካት ሂደት በፓርቲው ልሂቃን መካከል ትልቅ የስልጣን ሽኩቻ ይፈጥራል ብሏል።
ፋይናንሺያል ታይምስ፤ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖምን፤ አቶ ብርሀነ ገ/ክርስቶስንና ወ/ሮ አዜብ መስፍንን በስልጣን ተፎካካሪነት አስቀምጠል።

No comments:

Post a Comment