Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 8 August 2012

ለውይይት የተጠሩት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ


Unity for Democracy and Justice Party በፌደራሉ ከፍተኛ /ቤት ልደታ ምድብ 3 ወንጀል ችሎት ውሳኔ ተስጥቶበት በተዘጋው በነ አንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ ቁጥር 112546 “ተከሳሽዓቃቤ ህግ በሚል ደብዳቤ ለውይይት ተብሎ ፍርድ ቤት የተጠራው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፤ ተወካይ ከፍተኛ አመራሮች የተከበሩ / ነጋሶ ጊዳዳ፣የተከበሩአቶ ግርማ ሰይፉ እና አቶ አስራት ጣሴ ትናንት ሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2004.. ከሰዓት በኋላ በድንገት ችሎት ፊት እንዲቀርቡ ተደረገ፡፡



አንድነት በእነ አንዱዓለም አራጌ ላይ የተሰጠውን የፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ በተቃውሞ መግለጫ መስጠቱ በፓርቲው ፍርድ ቤቱ ላይ እና የፍትህ ስርዓቱ ላይ የተቃጣ ከፍተኛ ጥፋት ነው በማለት በስፋት ካተተ በኋላ ፓርቲው በአገሪቱ ለመድበለ ፓርቲ ግንባታ የሚያደርገውን ከፍተኛ አሰተዋፅዖ ከግምት ውስጥ በማስገባት በተግሳፅ እንዲታለፍ መወሰኑን የግራ ዳኛው ሁሴን ይመር በንባብ አሰምተዋል፡፡

ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ በፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት የፓርቲው ተወካይ አመራሮች እንዳስረዱት ከሆነ ለውይይት ተብለው በቢሮ ውስጥ ጉዳዩን ለመስማት 3 ወንጀል ችሎት ዳኞች /ቤት ውስጥ ለመግባት በመጠባበቅ ላይእንዳሉ፤ በችሎት በአስተናባሪው አረፍ እንዲሉ ተነግሮአቸው በመጠባበቅ ላይ እንዳሉ ችሎቱ ስራ መጀመሩን እና ምንም በማያውቁት ሁኔታ ምንም ዓይነት አስተያየት ሳይሰጡ ትዕዛዝ/ውሳኔ እንደ ተነበበላቸው ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹም በፍርድ ቤቱ ድንገተኛ ውሳኔ መገረማቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓርብ ሐምሌ 27 ቀን 2004 . በፍርድ ቤቱ ለአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲተከሳሽ አቃቤ ህግበሚል /ቤቱ ፓርቲውን ማነጋገር እንደሚፈልግ ቀጥሮ የነበረ ቢሆንም በዕለቱ ፓርቲውን በመወከል ዋና ፀሐፊው አቶ አስራት ጣሴ በፌደራሉ ከፍተኛ /ቤት ልደታ ምድብ 3 ወንጀል ችሎት ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ አቶ አስራት በዳኞች /ቤት ተጠርተው ፓርቲው በነ አንዱዓለም የፍርድ ውሳኔን በመቃወም ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ከዳኞች ጋር ሲነጋገሩ እሳቸው ጉዳዩን በደንብ ባለመከታተላቸው ከሌሎች አመራሮች ጋርና ከፓርቲው የህግ አማካሪ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ መልስ እንደሚሰጡ በመግለፃቸው ለትናንት ሰኞ ከሌሎች አመራሮች ጋር እንዲመጡ በመግለፅ እንደሸኟቸው ተጠቁሟል፡፡

No comments:

Post a Comment