Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday, 7 August 2012

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የዶላር እጥረት ተከሰተ

ሐምሌ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም -
ኢሳት ዜና:-የውጭ ባለሀብቶች የውጭ አገር የንግድ ስራዎችን ለመስራት ኤልሲ ( ሌተር ኦፍ ክሬዲት) ለመክፈት በሚሄዱበት ጊዜም ይሁን ሌሎች ለትምህርት ወይም ለህክምና ወደ ውጭ አገር ለመሄድ የሚፈልጉ ሰዎች ዶላር ለመግዛት ወደ ባንኮች ሲሄዱ፣ ዶላር የለም በሚል እንደሚመለሱ ታውቋል።
አቶ መለስ ከ6 ወራት በፊትበቂ የሆነ የዶላር ክምችት መኖሩን ተናግረው የነበረ ሲሆን፣ አሁን የታየውን የዶላር እጥረት ምን እንደፈጠረው አልታወቀም። ይሁን እንጅ ብዙዎች እንደሚገምቱት አንዳንድ ባለሀብቶች ከአቶ መለስ ዜናዊ ጤና ጋር ተያይዞ ተቀማጭ ገንዘባቸውን ወደ ዶላር በመቀየር ማሸሽ መጀመራቸው ምናልባትም ችግሩን አባብሶት ሊሆን ይችላል።
ብሄራዊ ባንክ ባለሀብቶች ሊተር ኦፍ ክሬዲት እንዳይከፍቱ እገዳ መጣሉም ተሰምቷል።
ዶላር መልሶ ከገበያ መጥፋቱ ባለፉት 3 ወራት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቶ የነበረውን የገንዘብ ግሽበት ወደ ነበረበት ደረጃ እንዳይመልሰው ተሰግቷል።
ኢሳት ባለፈው ሳምንት በአገሪቱ የሚታየው የንግድ እንቅስቃሴ መዳከሙን፣ በገጠር አካባቢዎች ኢንቨስት ያደረጉ ባለሀብቶች ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ የውጭ አገር ባለሀብቶችና ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ ከመሄዳቸው በፊት መረጃዎችን ማጣራት መጀመራቸውን መዘገቡ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ አብዛኛውን የውጭ ምንዛሬዋን በውጭ አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ከውጭ እርዳታ እንደምታገኝ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment