Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday, 22 August 2012

ተቃዋሚዎች ያለፈው የግፍ ስርአት ተመልሶ የማይመጣ መሆኑን በትግላችን የምናሳይበት ውቅት ላይ እንገኛለን ሲሉ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ገለጡ

ነሀሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የግንቦት 7 ንቅናቄ መሪ የሆኑት ኢኮኖሚስቱ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የመለስ ዜናዊ ዜና እረፍት በግላቸው ስለፈጠረባቸው ስሜት እና በአገሪቱ ላይ ሊያመጣ ስለሚችለው መጥፎ ወይም ጥሩ አጋጣሚ ተናግረዋል
የተለያዩ ሀይሎች እጃቸው ላይ ያለውን ካርድ የሚጫወቱበት መንገድ የኢትዮጵያን እጣ ፋንታ እንደሚወስን ዶ/ር ብርሀኑ ተናግረዋል::
በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የሚታየውን የስልጣን ክፍተት ተከትሎ አገሪቱ ወደ መጥፎ ጎዳና እንዳታመራ ግንቦት7 ምን አማራጮችን ያቀርባል ለተባሉት ፣ ድርጅታቸው ሲመሰረት ጀምሮ አማራጮችን ግልጽ ማድረጉን ገልጠዋል::
ድርጅታቸው ግንቦት7፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የስልጣን ክፍተት ቢፈጠር መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ አስተባብሮ አመራር ለመስጠት ተቋማዊ ብቃቱ ምን ይመስላል ለተባሉት ዶ/ር ብርሀኑ ሲመልሱ፣ ግንቦት7 በአለፉት 4 አመታት ድርጅታዊ ብቃቱን ማጎልበቱን በሙሉ ልብ ተናግረዋል::

No comments:

Post a Comment