ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት
ዜና:-ከአራት ቀናት በፊት የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ይፋ ባደረገበት ወቅት
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፤አቶ መለስን ተክተው በጠቅላይ
ሚኒስትርነት እንደሚሰሩ መወሰኑን ይፋ ቢያደርግም፤ በተለይ በህወሀት በኩል በተቀሰቀሰ ከፍተኛ ተቃውሞ እስካሁን የ
አቶ ሀይለማርያም ሹመት ሊጸድቅላቸው እንዳልቻለ የኢሳት የውስጥ ምንጮች ጠቁመዋል።
አቶ ሀይለማርያም ፤የአቶ መለስ አስከሬን ከብራሰልስ አዲስ አበባ የገባ ዕለት ምሽት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሢሰጡ፤ “መለስን መተካት ከባድ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።
አቶ ሀይለማርያም ይህን ያሉት፤ በእርግጥ ከልባቸው ይሆን?ወይስ የስልጣን ሽኩቻው ሰለባ ላለመሆን ካደረባቸው ስጋት? ወይስ በሌላ አስገዳጅ ተጽዕኖ፤ እስካሁ የታወቀ የለም። ከዚያም በማግስቱ በዕረፍት ላይ የሚገኘው ፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ መጠራቱ ተነገረ። ስብሰባው የተጠራው የአቶ ሀይለማርያምን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት ለማጽደቅ ነበር። ሆኖም የስብሰባ ጥሪ በተደረገ በዚያኑ ዕለት ምሽት የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስቴር ስብሰባው ላልተወሰነ ጊዜ እንደተላለፈ አስታወቀ።
ስብሰባው
የተላለፈበትን ምክንያት ግን አልገለፀም። የኢሳት የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት፤ ስብሰባው ሊሰረዝ የቻለው በአቶ
ሀይለማርያም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት በተለይ በህወሀት እና በብአዴን ቡድኖች መካከል ከፍ ያለ ሽኩቻ በመፈጠሩ
ሳቢያ ድርጅቱ አንድ አቋም ላይ ሊደርስ ባለመቻሉ ነው። ለዚህም ነው የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከትናንት
በስተያ ምሽት በዜና እወጃው ከሶስት ቀናት በፊት አቶ መለስን ተክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል ያላቸውን አቶ
ሀይለማርያም ደሳለኝን፦” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር” በማለት በቀድሞው ማዕረጋቸው
የጠራቸው፦ ከዚህም ባሻገር በሌሎች የሥልጣን ቦታዎች ላይ ያለው ፍትጊያ አይሎ መውጣቱን የጠቀሱት ምንጮቹ፤ቀደም ሲል በከፍተኛ የድርጅቱ አባላት መካከል የነበሩ ቂሞችም የሚፈነዱበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ብለዋል። አቶ በረከት ስምዖን ከትናንት በስተያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለስልጣናት በታጋይ መለስ መስመር አንድ ላይ እንዲሄዱ ሲማጸኑ መደመጣቸው ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment