Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 25 August 2012

የሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ከህዝብ እይታ መጥፋት አነጋጋሪ እንደሆነ ነው

ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑት ባለሀብቱ ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አልአሙዲን በብጹወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነስርአት እንዲሁም፣ በአቶ መለስ ዜናዊ አስከሬን አቀባባል ዝግጅት ላይ አልተገኙም። አንዳንድ ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ባለሀብቱ በሳውዲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ይህንን መረጃ ግን ከነጻ ወገን ማረጋጋጥ አልተቻለም። የባለሀብቱ ኩባንያ የሆነው ሚድሮክ ሰራተኞች በአቶ መለስ ዜና እረፍት ሀዘናቸውን ሲገልጹ የባለሀብቱ ስም አልተጠራም።

No comments:

Post a Comment