Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Friday, 24 August 2012

ሳምሶን ማሞ ክስ በሚኒስተር ዴኤታው ትዕዛዝ ሊቋረጥ ነው


ለሁለት አመት የንግድ ፍቃድ ሳያድሱ በሁለት ድርጅቶች ሲሰሩ ተገኝተው ታስረው በዋስ የወጡት ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ በፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ትእዛዝ ክሱ እንዲቋረጥ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡

እንደ መረጃ ምንጫችን ታስረው በዋስ ተለቀው ሐሙስ ነሐሴ 17 ቀን 2004. የፌደራሉ ከፍተኛ / ቤት 16 ወንጀል ችሎት የቀረቡት አቶ ሳምሶን ማሞ በጠበቃው አማካኝነት ክሱ መቋረጡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ምንጮቻችን እንደገለፁት ከሆነ በዕለቱ ዐቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰማለት ይዞ የቀረበ ሲሆን የሳምሶን ጠበቃ ሚኒስቴር ዴኤታው ክሱ እንዲቋረጥ ደብዳቤ የጻፉ ስለሆነ ጊዜ ሳይባክን ክሱ ይዘጋልን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ዐቃቢ ህግ በበኩሉ በእርግጥ ደብዳቤው ለእኛም የደረሰን ቢሆንም ምስክርነቱ ተሰምቶ ይቋረጥ ሲል ፍቤቱን ጠይቋል፡፡ በመቀጠልም ምስክርነቱ ከሚሰማ ይቀጠርና እንነጋገርበት የሚል ሀሳብ በማቅረባቸው በጉዳዩ /ቤቱም ደብዳቤው በግልጽ የተጻፈ ስለሆነ ምስክርነቱን መስማቱ ጊዜ ማባከን ነው ካለ በኋላ በመዝገቡ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሌላ ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ በርካታ ዜጎች የንግድ ፈቃድ ባለማደስ እየተከሰሱ በታሰሩበትና በተቀጡበት አገር ለሳምሶን ማሞ ፍትህ ሚኒሰቴር ክሱ እንዲቋረጥ ደብዳቤ መፃፉ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

No comments:

Post a Comment