Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Friday 24 August 2012

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ

ነሀሴ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የፕትርክና ታሪክ አወዛጋቢ የሆኑት ብጹወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የመንግስት ባለስልጣናት እና ሌሎች ዲፐሎማቶች በተገኙበት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን የቀብራቸው ስነስርአት ተፈጽሟል።

ከሃምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ 20ኛ አመት በአለ ሲመታቸውን ሲያከብሩ የነበሩት አቡነ ጳውሎስ፣ በድንገት ማረፋቸው የብዙዎች መነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ ነው። በተለይም የእርሳቸውን ሞት ተከትሎ የአቶ መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት ይፋ መሆን ኢትዮጵያውያን ነገሩን ከሀይማኖት ጋር እንዲያያዙት ግድ ብሎአቸዋል።

አቡነ ጳውሎስ በልማቱ ዙሪያና ኤች አይ ቪ ኤድስን በመከላከል ረገድ አወንታዊ ተግባራትን መፈጸማቸው ቢነገርም፣ ጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ከሁለት በመክፈልና በማዳከም፣ የገዢው ፓርቲ መሳሪያ በመሆን እና ከህዝብ ጎን ባለመቆም እንዲሁም ለአለማዊ ቅንጦት ከፍተኛ ቦታ በመስጠታቸው ይወቀሳሉ። በተለይም በቅርቡ የብጹአን አባቶች መደብደብ እና ሀውልታቸውን በቁማቸው ማሰራታቸው ለከፍተኛ ትችት ዳርጓቸው እንደነበር ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment