ነሀሴ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አቶ በረከት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በሀይወት ዘመናቸው አቶ መለስ የያዙት ዓላማ የጥቂቶች ዓላማ ከሆነ ሞት ነበር ” ብለዋል ።
የመንግስትና
የኢህአዴግ አመራርም የህዝቡን መልዕክት ተቀብለን ጠቅላይ ሚኒስትሩን አርዓያ አደርገን ለመከተል ወስነናል የሚሉት
አቶ በረከት፤ ሌሎች ባለስልጣኖችና የኢህአዴግ አመራር አካላት፣ ህዝቡ እና የአለማቀፉ ማህበረሰብ ከጎናቸው እንዲቆም
ተማጽነዋል።
ኢሳት በትንናት ዘገባው አንድ የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣንን በምንጭነት በመጠቀም ፣
የኢህአዴግ ባለስልጣናት በአቶ መለስ ሞት የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ስትራቴጂ መንደፉቸውን መግለጻችን ይታወሳል።
የኢህአዴግ ስልት ህዝቡ በየወረዳዎች በተዘረጋው ድንኳን እየወጣ ለአቶ መለስና ለኢህአዴግ ያለውን ድጋፍ
እንዲገልጽና ስሜታቸው የተዳከመውን የመንግስት ባለስልጣናት እና የኢህአዴግ ካድሬዎችን እንዲያበረታታ ማድረግ ነው።
አቶ በረከት “በ መለስ አጥንት” በማለት ዛሬ ለባለስልጣኖቹና ለህዝቡ ያቀረቡት ጥሪ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረውን መከፋፈል እና ውጥረት እንደሚያሳይ ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት።
ለአቶ
መለስ ስትሉ ደግፉን እያሉ መማጸን አገዛዙ የገባበትን የፍርሀት ድረጃ እንደሚያሳይ፣ ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በላይ
መዳከሙንና በውስጥ ፍንዳታ ሊፈረካከስ እንደሚችል ነው የኢህአዴግ አባል የኢሳት የመረጃ ምንጭ የጠቆሙት። አብዛኛው ህዝብ የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ብሩህ የሆነ ጊዜ ይመጣል ብሎ ተስፋ ያደርጋል። አቶ ሀይለማርያም ዳሰለኝ በዛሬው እለት ቃለመሀላ ይፈጽማሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ ፓርላማው ስነስርአቱን ሰርዞታል።
የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነ ሰርዓት በአዲስ አበባ ይካሄዳል። በየክልሉ የሚገኘው ህዝብም በእየደንኳኖች እየሄደ እንባውን እንዲረጭ ይደረጋል። አቶ መለስ የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነትን ማስከበር የቻሉ መሪ ናቸውና የአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች በእኝህ መሪ የተሰማቸውን ሀዘን የሚገልፁበት ስርዓትም እንደሚኖር አቶ በረከት ተናግረዋል። በርካታ ተቺዎች ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ከሰሜን ኮሪያ ሁኔታ ጋር እአመሳሰሉ በተቸት ላይ ናቸው።
ዘጋቢያችን
ያጠናከረው ሪፖርት እንደሚያሳየው ደግሞ ዛሬ ከረፋዱ ጀምሮ የወረዳና የቀበሌ ካድሬዎች በየቀበሌው ድንኳን በመጣል
ሰው በተለይም የፓርቲው አባላት እና ስራቸው ከቀበሌና ከወረዳ ጋር የተያያዘ የመንግስት ሰራተኞች እየሄዱ
እንዲያለቅሱ ቅስቀሳ አካሂደዋል።
የኢህአዴግ ካድሬዎች በየሰፈሩ የሚገኙ ታዋቂ ሽማግሌዎችን፣ ነጋዴዎችን
እና ታዋቂ ሰዎችን ወደ ድንኳኑ በመውሰድ ሰዎች ሰብሰብ ብለው እንዲያለቅሱ ሲያደርጉ ውለዋል። አብዛኛው የመንግስት
መስሪያቤቶች በአግባቡ አገልግሎት መስጠት የቀነሱ ሲሆን በተለይም ወረዳ ላይ እና በቀበሌ ደረጃ ስራ ሁሉ የለቅሶቤት
እንቅስቃሴ ሆነዋል። በአንጻሩ የባለስልጣናት ቤተሰቦችና ወዳጆች ቤተመንግስት እየሄዱ ለቅሶ የሚደርሱ ሲሆን
የተወሰኑ በኑሮዋቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ከቤተመንግስት በር ላይ ሆነው ሲያለቅሱ ተስተውሏል።
No comments:
Post a Comment