Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Sunday 1 April 2012

እውቀታችን ህዝባችንን ከወያኔ ጥቃት ለመከላከል ያስችለናል!



ግፈኛው የወያኔ ቡድን ከምንግዜውም በበለጠ በመገናኛ ብዙሃን ላይ የማጥፋት ዘመቻውን በአዲስ መልክ አጠናክሮ ቀጥላል:: ይህ የወያኔ አጥፊ እርምጃ በየ አቅጣጫው ከተነሳው የህዝብ አመጽ ለማምለጥ የተደረገ ሙከራ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ሙከራው ከንቱ ልፋት አንደሆነ ልናስገነዝባቸው አንወዳለን::
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ የወያኔ የማይረባ ሙከራ የትም እንደማያደርሰው ብንገነዘብም ለጊዜው ህብረተሰቡን መጉዳቱ የማይቀር መሆኑን አናምናለን:: ስለሆነም ይህንን የወያኔ የግፍ እርምጃ ለመከላከል የምንችለውን ሁሉ ለማገዝ ወስነናል::

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ የታገዱ ድህረገጾችን ማየት የሚያስችሉ የፕሮክሲ ዌብሳይቶችን በየቀኑ እዚህ ገጽ ላይ ለማስፈር መወሰናችንን እያስታወቅን : በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ሰው እነዚህን አስተማማኝ የሆኑ ዌብሳይቶችን ተጠቅሞ በወያኔ የታገዱ ማንኛውንም አይነትድህረገጾችን በቀላሉ መመልከት አንደሚችል ለህዝባችን ስናበስር ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል::

ኢትዮጵያ ለዘላለም በነጻነት ትኑር!
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ

No comments:

Post a Comment