Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday 2 April 2012

ኃይሌ የወርቃማው እግሮችህ ውለታ በምላስህ እንዳይደበዝዙ!

ኃይሌ የወርቃማው እግሮችህ ውለታ በምላስህ እንዳይደበዝዙ!
ሙያን ለባለሙያ አለመተው የሀገራችን ዋነኛ ችግሮች አንዱ ነው።በጨረባ ለብለብ ሰርተፊኬት፣ በፓርቲ አባልነት፣በሬድዮ አንድ ዙር ድራማ አርቲስት የሚለውን ታፔላ የለጠፉ ሞራልም ብቃትም የሌላቸው ጋዜጠኛ ብጤዎች እንደ ኢትዮፒካው ብርሃኔ ንጉሴ (በአማርኛ ዝግጅት አቅራቢ አማርኛን አስቦ የሚያወራ) ሰይፉ ፋንታሁን (የሸገር አራዶች ሰፊአፉ ይሉታል)የሀገራችንን ወግና ባህል
በ፵ዓመቱ ያልገባው የትልቅ ቀላል የሆነ ጎርፍ ያመጣው ጋዜጠኛ ኃይሌን ይዞት ገደል ገብቷል።በዓለም ላይ ቀላሉ ነገር ምክርና ቦክስ ነው፣ለሰጪው እንጂ ለተቀባዩ ከባድ ነው።የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ኃይሌ፣ ሰንደቃችንን ከፍ አድርጎ ሀገራችንን ያስጠራት ኃይሌ፣ድህነትን ጣዕሟን ቀምሷት ያደገው ኃይሌ በመምህራኖች ጉዳይ ላይ አስተያየት መጠየቅም አልነበረበትም፣ቢጠየቅም ስለ መምህራን የሚያገባው ነገር፣የሚመለከተው ጉዳይም አይደለም።ኃይሌን አዘንኩበት።
ዛሬ መሞዳሞድ መሸፋፈን የለብንም አካፋን አካፋ ማለት አለብን።ኃይሌ ስለ መምህራን ከሚዘባርቅ፣ የመለስ መንግስት ከሱ ክብረወሰን በፈጠነ ማይክሮ ሰከንድ ልማቱን አፋጥኖ ሀገራችንን እንደሚያሳድግ ከሚሰብከን፣ባደገበት የአርሲ ገጠር መንደር ውስጥ ሌት ከቀን የሚማስኑ ታታሪ አርሶ አደሮችን ስራ የማይወዱ ህዝቦች ብሎ በጅምላ ከሚፈርጅ የሀይማኖት ሊቅ ይመስል ዐመት በዐላት በዙ ብሎ በማያገባው ጥልቅ ከሚል ለምን ስለ እራሱ በትክክል አይመልስም?
ስለ ኃይሌ ወደዳችሁም ጠላችሁም እውነታውን እነግራችኋለሁ።መርማሪ ጋዜጠኞች፣የታሪክ ተመራማሪዎች ፍንጩን ይዛችሁ ድረሱበት ኃይሌ ሆላንድ ውስጥ ወጣት ሆኖ ለተወሰነ ጊዜ ኖርዋል በወቅቱ ከታላቅ ወንድሙ ጋር ሆላንድ ውስጥ ሲቀመጥ የነበረውን የሩጫ ብቃት ሲያየው ለሆላንድ ቢሮጥ ከፍተኛ ቀረጥ(ግብር)መክፈል፣የማስታወቂያ ገቢዎች ማሳወቅ፣ሀብት ማስመዝገብ፣የገንዘብ ዝውውርና የስጦታ ሽልማቶችን ማስመዝገብ፣ለታዋቂ ሰዎች የሚጣለው የማህበራዊ አገልግሎት ወጭዎች ወዘተ...እጁ ለማይፈታው፣ወርቃማ እግሮች እና ረዥም ምላስ ለታደለው ኃይሌ አልተዋጡለትም። ሆላንድን ትቶ ለሀገራችን የሮጠው በነደደ የሀገር ፍቅር ስሜት ብቻ ነው ብላችሁ አታስቡ(ግን እንኳን እሮጠልን)በዓለም አቀፍ የስፖርት ህግ የሚገዛ ሰው ቢሆንማ ኖሮ ስለ አለው ሀብት ሲጠየቅ የወንድ ልጅ ደመወዝና የሴት ዕድሜ አይነገርም የሚባለውን የባልቴት ተረት ባልተረተብን ነበር፣ ከማስታወቂያ ስንት ታገኛለህ? ሲባል የሀገር ውስጡ ብዙ አይደለም የውጭው ይሻላል ግን ምን ያረግልሀል? አይልም ነበር።ገቢን ማሳወቅ ግዴታ ነው፣የዴቪድ ቤክሀም፣የሊዮነል ሜሲ፣የሁሴን ቦልት፣የኖቫክ ጆኮቪች የታላላቅ ስፖርተኞች ሳምንታዊ ዐመታዊ ገቢያቸው ይታወቃል።ኃይሌም ገቢውን ማሳወቅ አለበት ኢትዮጵያም ከዓለም አቀፉ የስፖርት ስነምግባር መርሆዎች ውጭ መሆን የለባትም። ስለ መምህራን ሳይሆን ስለ እራስህ ንገረን ኃይሌ፣ስንት ገንዘብ በባንክ አለህ?ምንያህል መዋዕለ ንዋይህን አፍስሰሀል?ከማስታወቂያ ገቢ ስንት ይደርስሀል?ምን ያህል በመቶኛ ግብር ትከፍላለህ?እነዚህንና ተዛማጅ ጥያቄዎችን ካንተ መልስ እንሻለን።የመምህራኖችን ጉዳይ የትምህርት ሚንስቴር ከመንግስት ጋር የሚወጣው ጉዳይ እንጂ አንተንም ሰፊአፉን ይቅርታ ሰይፉን ማለቴ ነው አያገባችሁም። አሁንም ለሀገራችን የዋልከውን ውለታ ዘንግቼ አሊያም፣በጥላቻ ውስጥ በስሜት ተመርቼ አስተያየቴን እንዳልሰጠሁኝ ልነግርህ እወዳለሁ።አንተን ጠርተው ነው ሀገራችንን የሚጠሩት፣አንተን ጠርተን ነው ደረታችንን የምንነፋው ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ እንዲል ይደረክ ብሔራዊ ጀግናችን ነህ አሁንም የአደባባይ ጀግናችን ነህ።የራሴን ፌስቡክ ገብተህ ብታየው ምስልህን ታየዋለህ።ነገር ግን ባንዴራችንን ከሚዘቀዝቁት ጎራ አትሰለፍ።የወርቃማው እግሮችህ ውለታ በምላስህ እንዳይደበዝዙ።ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

No comments:

Post a Comment