Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday, 7 April 2012

እስቲ ወደኋላ በትዝታ ልመልሳችሁ………..

ያልተላከው ደብዳቤ
በተወዳጁ አደም ሁሴን

እስቲ ወደኋላ በትዝታ ልመልሳችሁ………..መቼም በወጣትነት በተማሪነት ወቅት እንደየ ጊዜና ዘመኑ የማይረሳ ጣፋጭና አስገራሚ የህይወት ገጠመኝ እንደምናሳልፍ እገምታለሁ ወይም ብጠረጥ የሚደንቅ አይመስለኝም፡፡
የኔን የተማሪነት ዘመን እናውጋ……አንድ ገርል ፍሬንድ እንዲኖርህ ትፈልጋለህ እንበል ቀትታ ሄዶ ማነጋገር ነውር ነው ወይም ደግሞ የሚደፍርም የለም እሷስ ብትሆን ስታናግርህ አይደል……….! እናም እንዴት እንደምታናግራት ሊጨንቅህ ይችላል እናም በወቅቱ በሰፊው የተለመደው ደብዳቤ መጻፍ ነው የፍቅር ደብዳቤ እሱንም ቢሆን አዋቂ፤ምርጥ ጸሀፊ መሆን ይጠይቃል፡፡ማንም ተነስቶ ደብዳቤ አይጽፍም……የወደድካት ልጅ ልቧ እንዲራራ፤ያንተ እንደስትሆን ከፈለክ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ቃላት መምረጥ አለብህ፤ጥቅስ መደርደር፤አባባሎችን መጠቀም ፤አበባ መሳል ፤ልብ ቅርጽ ላይ ጦር ሰክተህ ደም ማንጠባጠብ አለብህ ቢቻል ከደብዳቤው ጋር ደስ የሚል የህንድ ፖስት ካርድ ይሄ ሀሚት አፕ አቻ ከቆንጆ ሚስቱ ጋር ያለበትን ከጀርባው ከ ኤስ ለ ቲ ብለህ ጽፈህ…… ፡፡ በቃ ምን አለፋህ ጥንቃቄ የተሞላበት ጽሁፍ ካልሆነ የልጅቷን ልብ አራራለሁ ብለህ ጭራሽ ልቧን አምርረኅው ቁጭ ትላለህ፡፡
አንድ የትምህር ቤት ጓደኛ ነበረኝ የፍቅር ደብዳቤ በመጻፍ የሚታወቅ እሱ የጻፈው ደብዳቤ የደረሳት ተፈቃሪ ልቧ የማይራራ የለም እውነት ይገርመኛል ሀሪፍ ጸሃፊ ነው በቃ ፍቅር ሲይዝህ እሱ ጋር መሄድ ነው፡፡ ከዛ ልክ ሀኪም ዘንድ ወይም አጥፍተህ ዳኛ ዘንድ እንደቀረበ ጥፋተኛ ትናዘዛለህ ውይም ችግርህን ታወያየዋለህ፡፡
#ምኗን ነው የወደድካት?; ይልሃል ፡፡ በቃ ትንሽ ማፈርህ አይቀርም ትሽኮረመማለህ….ግን ፍቅረኛህን ከማጣት አይበልጥምና ትናገራለህ፡፡ ይገርመኝ የነበረው ይሄ ጓደኛዩ ሲጠይቅህ ኮስተር ብሎ ነው በስሜት ተውጦ ያዳምጥሃል፡፡ አንተም ትናዘዛለህ…………
#እሷን እያየሁ እያሰብኩ ምግብ አልበላ ውሃ አልጠጣ አለኝ አማርኛ ትምህርት አረብኛ ሆነብኝ፤ እሷን ሳይ መራመድ አቃተኝ ትንሽ ጠጠር እንቅፋት እየመታኝ ይህው እግሬ ተላላጠ
ወዘተ…..; ትነግረዋለህ እሱም አዳምጦህ ሲጨርስ የራሱን ጥበብ መጠበብ ይጀምራል፡፡
(እናንተስ የፍቅር ደብዳቤ ጽፋቹ አታውቁም?)…….. በነገራችሁ ላይ አንድ የተባረከ ዳዊት ዋሲሁን የተባለ ወዳጄ እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ ነሸጥ ሲያደርገኝ የምለጥፈውን ሙከራዎች እያደነቀ እያደነቀ ቆየና
#በዚህማ መቅረት የለመትም;
ብሎ ዌብ ሳይት ከፈተልኝ መቼም እውቀትህ ይባረክ በሉልኝ አንድ ቀን ስለዚህ ሰው አንድ ነገር ማለቴ አይቀርም የሆነው ሆኖ መልካም ፈቃዳቹ ከሆነ እንዲህ በትነሽ በትንሹ ቡጭቅ ቡጭቅ እያደረኩ ከማሰቃያቹ እዛ ላይ ሙልውን እንድታነቡ ልጋብዝ adamhussen.blogspot.com ብላችሁ እዩት ፡፡
! ! !
ደረጀ ፍቅሩ የሚባል ወዳጅ አለኝ መቼም ታውቁታላችሁ (ስርየት) የሚባል ፊልም ደራሲ ነው (ጋጋ) የሚባል አስፈሪ ገጸ ባህሪ የሚተውንበት
#አዲስ አበባ ደበረኝ;
ሲለኝ ና እለውና ይመጣል ያለሁበት ሀገር እንገባበዛለን ቀዝቀዝ ያለ ቢራ እየጠጣን እንጨዋወታለን የማይነሳ የማይጣል ነገር የለም ሲበዛ ቀልደኛ ነው ጨዋታ ያውቃል የደረስኩትን የተወንኩበትን ፊልሜን እይልኝ አለና ጋበዘኝ በደስታ አየሁት፡፡ በቃ ከዛን ጊዜ በኋላ የአማርኛ ፊልም አይቼ አላውቅም የራሴ ምክንያት አለኝ በቀደም ግን እንዲሁ ከአንድ ወዳጄ ጋር በዚሁ ጉዳይ ስንነጋገር (ውይይታችን ይቆይ………. ፊልሞችን ግን ልጋብዛችሁ)
 

No comments:

Post a Comment