Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Sunday 1 April 2012

ሰንደቅ ዓላማውን የዘቀዘቁት መለስ

ሰንደቅ ዓላማውን የዘቀዘቁት መለስ የራሳችንን ወደብ ሰጥተው የሰው ሀገር ወደብ ሲቀላውጡ ነው ወደብ ሸቀጥ ነው በገንዘብህ የምትገዛው፣ከፈለጉ ግመላቸውን ውሀ ያጠጡበት ወዘተ... ያልቀባጠሩት የለም ነበር ተሳዳቢው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ለሳቂታውፓርላማ፣ለአሳርኛው ህዝባችን።አሁን ደግሞ አማራጭ ወደብ ፍለጋ፣ላይታች ሲማስኑ እያየን ነው፣ለምን ያኔ እንዲያ ብለው ነበር የሚላቸው የለም ተጠያቂነታቸው ለማን መሆኑን የተደነገገ ማሰሪያ ህግም የለም።ካሻቸው ፓርላማውን(ወጉ አይቀር መቼም ፓርላማ ልበለው)የዐይናቸው ቀለም ከደበራቸው መበተን ይችላሉ፣በህግ የተፈቀደ አንባገነንነት ያላት ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ትመስለኛለች።
ወደብ ወሳኝ ነገር አለመሆኑን የነገረን መለስ ዛሬ ደግሞ ወደብ ፍለጋ ኬንያ ድረስ ሲኳትን እያየን ነው።ዜናውን ያበሰረን ኢቲቪ ነበርወደብ አልባ ሆኖ ካለችግር መኖር እንደሚቻል የነገረንም ኢቲቪ ነበር፣ሰውዬውም የመረጃ ማዕከሉም አልተቀየሩም።በኬንያ የሚገነባው ወደብ ለኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ለአዲሲቷ ጎጆ ወጪ ደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ መሆንና ከወደቡ ጋር የነዳጅ ማጣሪያ አብሮ እንደሚሰራ ኢቲቪ አበሰረን፣የራሳችንን ወደብ፣የነዳጅ ማጣሪያ፣ባህር ሀይል አሳልፈን ለምን እንሰጣለን?ተብለው ሲጠየቁ ለሰላም ብለው መሆኑና ይህን ጥያቄ የሚያነሱ ጦርነት ናፍቂዎች ናቸው ሲሉን የነበሩት ሰውዬ ዛሬ ስለ ሌላ ሀገር ላይ ስለሚሰራ ወደብ፣የነዳጅ ማጣሪያ፣ ጅቡቲ ላይ ስላለን የባህር ሃይል ጠቃሚነት ይለፍፉብናል።ሰላም ለማምጣት የተባለው የኤርትራ ጉዳይም ከሰባት ዐመት በላይ ሊዘልቅ አልቻለም፣ወደቡም ሰላሙም የለም ግን ማን ይጠይቅ?

No comments:

Post a Comment