Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Friday 25 May 2012

“ደሙን እንጠጣዋለን” የትግሬ ነጻ አውጪዎች የሚመኩበት ሙያ

ከእሰከ ነጻነት

ሰላም መብታችሁ ለተረገጠ፤ ደማችሁ ለመጠጣት ተራ ለሚጠበቅላችሁ ወገኖቼ ሁሉ

አቧራ የጠጣውን ብእሬን ከስርቻ ፈላልጌ ለመሞነጫጨር ያነሳሳኝ ሰሞኑን አበበ ገላው የፈጸመው ገድል አደለም፡ እሱ መናገር ከምችለው በላይ አስፈንድቆኛል፤ አስደምሞኛል፤Ethiopian Journalist Abebe Gellaw protesting against Meles Zenawi በአንድ የትግሬው ነጻ አውጪ መሪ ከመምጣቱ በፊት በወጣ ጽሑፍ ላይ አሰተያየት ስሰጥ ከተቃውሞ ሰልፍ ያለፈ ነገር ማድረግ ይቻል ይሆን የሚል ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡ አበበ ገላው ከምጠብቀው በላይ መልሶልኛል፤ አካላዊ፤ ውጫዊ ሞት ሳይሆን ውስጡን ገሎታል፡ሊያገግም፤ ሊያንሰራራ በማይችልበት ሁኔታ አቁሰሎታል፡ ካሁን በሗላ የትግሬ ነጻ አውጭው መሪ ያለው እድል ጭራው እንደተቆረጠ እባብ ራሱን በራሱ መርዝ መጨረስ ብቻ ነው፡፡ በዚህ የጀግንነት ተግባሩ አበበ ገላውን አመስግኜ ወደተነሳሁበት ልመለስ።
ከላይ እንደጠቀሰኩት ይህን ጽሑፍ ለመሞነጫጨር ያነሳሳኝ የአበበን ገድል ተከትሎ የሚሰነዘሩ አሰተያየቶች ናቸው በተለይም ከትግሬ ነጻ አውጪው መሪ ደጋፊ በእሳት የስልክ መልእክት መቀበያ ላይ ያስመዘገበው፡ “…ጠቅላይ ሚንሰትራችንን ማዋረድ ሙያ መስሏችሁ……… አበበን ደግሞ ደሙን እንጠጣዋለን…” ሙሉውን መልእክት ለማዳምጥ አዚህ ላይ ይጫኑ።
መቸም ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ተጠቅሞ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸመን፤የሐገርን ሐብት እና ጥቅም አሳልፎ ለባዕድ የሸጠን፤ የሰጠን፤ ወርድና ቁመቱ ሊለካ የማይችል ሰቆቃ በሰው ልጅ ላይ የፈጸመን፤ ወንጀለኛ ማጋለጥ ለወያኔዎች እንኳን ሙያ መብት መሆኑ ሊዋጥላቸው እንደማይችል ግልጽ ነው፡ ለነሱ ሙያ ማለት የሰው ደም መጠጣት ነው።
የአበበን ደም እንጠጣዋለን ያልከው ሰዎዬና አጋሮችህ፤
አዎን ትክክል ብለሃል ደም ትጠጣላችሁ ያዉም እያማረጣችሁ ካማራ የኦሮሞ፤ ከኦጋዴን የጋምቤላ፤ከአፋር የጉሙዝ፤ ከሲዳማ የቤንች ከሱርማ የሐመር እያላችሁ፡ ባጠቃላይ በየዘሩ እየነጣጠላችሁ ጠጣችሁት፤ ምኑ ቅጡ ምን የቀራችሁ የደም አይነት አለ? የህጻን፤ የጎልማሳለ የሴት፤ የወንድ፤ የእርጉዝ፤ የመጫት፤ ያዛውነት፤የ እመበለት የባሃታዊ ደም እንኳ አልቀራችሁም፡ የማ ቀራችሁ? የክርሰቲያኑ፤ የእስላሙ፤ የኦርቶዶከሱ፤ የፕሮቴስታንቱ፤ የዋቄፈታ፤ የባህል አማኝ፤ የዝህ እምነት ተከታይ የዝያ እምነት ተከታይ እያላችሁ እያማረጣችሁ ጠጣችሁት።
ከአሜከላ ውስጥ የበቀለው ወይን ገ/መድህን አርአያ በደንብ አስረግጦ ነግሮናል ከ8 ሚሊየን ህዝብ በላይ ደም እንደጠጣችሁ፤ ስልጣን ከያዛችሁ ጀምሮ ደማቸውን የጠጣችሁት 3 ሚሊየን አማሮችን፤ ከአለም እይታ ጋርዳችሁ ደማቸውን የጠጣችሁት የኦጋዴን ወገኖቻችን ቁጥር ስንት እንደሆነ እንኳን አይታወቅም፤ በየሰርቻው በየጉራንጉሩ እየተሰወሩ ደማቸው የተጠጣው ስንቱ ተቆጥሮ፤ ያ ሁሉ ሲደማምር እሰከ አሁን ከ10ሚሊየን በላይ ሕዝብ ደም ጠጥታችሓል፡ ያም አልበቃችሁ ገና ልትጠጡ ትዘጋጃላችሁ።
እናንተ የህዝብን ደም ስትጠጡ የእህቱን፤ የወንድሙን፤ ያጎቱን፤ ያክስቱን፤ የዘመዱን፤ የወገኑን ደም የሚቀዳላችሁ አላጣችሁም ፡ ለአብነት ያህል ታምራት ላይኔ፤ ተፈራ ዋልዋ፤ ኩማ ደመቅሳ፤ አባተ ኪሾ፤ ሃይለማርያም ደሳለኝ፤ ግርማ ብሩ፤ ሽፈራው ሽጉጤ፤ ኦሞት ኦለም፤ አባ ዱላ ገመዳ፤ አብዲ ረሽድ ዱለኔ፤ ዝርዝሩ ብዙ ነው።
እናንተ የተደራጃችሁት ደም ለመጠጣት ነው እየጠጣቸሁም ነው፡ ለመጠጣትም እየተዘጋጃችሁ፤ እያወጃችሁ ነው ከናንተ ጋር ከዚህ ያበለጠ ጊዜ ማጥፋት አሰፈላጊ ስላልሆነ ደማቸው በትግሬ ነጻ አውጭ ለመጠጣት ሰልፍ ወደያዙ ወገኖቼ ልመለስ።
ከሰሜን እሰከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያላችሁ ከ80 በላይ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖቼ፤ ላንተ፤ ላንቺ አንድ ጥያቄ በአክብሮት ላቅርብ፡
ደምሽ በትግሬ ነጻ አውጭ እስኪጠጣ ተራ ትጠብቂያለሽ፡ አንተስ የትግሬ ነጻ አውጭ ደምህን እስኪጠጣው ሰልፍ ይዝህ ትጠብቃለህ? ለአቅመ አዳም ያልደረሰች ልጅህን እፊትህ እንደ አለም ደቻሳ ጎትተው ደሟን ሲጠጧት ዝም ብለህ ታያለህ? ወይስ ከዚች ደቂቃ በሗላ የትግሬ ነጻ አውጭ ቡድን የማንንም ደም አይጠጣም ብለህ፤ ከዛሬ በሗላ የትግሬ ነጻ አውጭ ቡድን የኔንም፤ የልጄንም ደም አይጠጣም ብለሽ ደማቸው ከሚጠጡ ጋር ተሰለፋለህ ተሰለፊያለሽ?
በቃ ለማለት እና ወንጀለኞችን አንገት ለመቀንጠስ ብዙ ሰው ሳይሆን፤ጦር ጠመንጃ ሳያሰፈልግ ቁርጠኝነትና ድምጽ ብቻ በቂ መሆኑን አበበ ገላው አሰተምሮናል።
እስኪ እዚህ ላይ ቆም ልበልና ያለፈው ሰላማዊ ሰልፍና የአበበ ገላው ገድል የትግሬ ነጻ አውጭውን እውነተኛ ማንነት ከማጋለጥ ያለፈ ፋይዳው ምንድን ነው የሚለውን ከመዳሰሴ በፊት ስለ ጥገኝነት አባዜ/ከሌላ የመጠበቅ አባዜ በእንግሊዘኛው (dependency syndromes) ትንሽ ልበል
የጥገኝነት አባዜ ወይም ከሌላ የመጠበቅ አባዜ በምን የገለጻል?
የመሰኩ ባለሙያዎች ከሰው የመጠበቅ አባዜን እንደ በሽታ ይቆጥሩታል፤
ዶ/ር ፊል ባርትል ይህንን እንደዚህ ይገልጹታል፡ The “dependency syndrome” is an attitude and belief that a group cannot solve its own problems without outside help. It is a weakness that is made worse by charity. ትርጉሙ “የተረጅነት አባዜ/ ከሌላው የመጠበቅ አባዜ” አንድ ማህበረሰብ የውጭ እርዳታ ካልተጨመረበት በስተቀር የራሱን ችግር ራሱ መፈታት አልችልም የሚል ዝንባሌ ወይም እምነት ነው፡ እርጥባን ደግሞ ይህን ድክመት የበለጠ ያባብሰዋል።
በዚህ የተጠቃ ግለስብ/ማህበረሰብ የሚከተሉት ይታዩበታል
• ምንም አይነት ውሳኔ በራሰ መወሰን አለመቻል፤ ለጥቃቅን ወሳኔዎች ሁሉ ምክር ወይም የሌሎችን አጽድቆት(አፕሩቫል) መጠበቅ
• የግል ሓላፊነትን ወይም ተጠያቂነትን መሸሽ፡ የግል ውሳኔን ከሚጠይቁ ሰራዎች ወይም ሁኔታዎች መራቅ እና ሌሎች እንዲሰሩት መጠበቅ
• ከሰው መጣላትን፤ በሃሳብ መለያየትን አጥብቆ መፍራት፡ከሰው መጣላት ወይም መለየት እጅግ የሚያሰከፋው (አጉል የይሉኝታ ተጠቂ መሆን)
• ተችትን አግዝፎ መመልከት (Over-sensitivity to criticism)
• ጨለምተኝነት፤ በራስ አለመተማመን፤በራስ ብቻ መኖር የማይቻል ነው ብሎ ማመን
• ድጋፍ ወይም ሃሳቡን አጽዳቂ ላለማጣት ከሰዎች ጋር አለመግባባትን ማሰወገድ (ከህሊናው ጋር አየተጣላም ቢሆን)
• ሌሎች የሚያሳድሩበትን ጫና፤ ጭቆና፤ ግፍ ለመታገስ ዝግጁነትን ማሳየት (ጊዜ ይፍታው፤ እግዜር ያዉቃል፤ እኔ ምን አቅም አለኝ የሚል ራስን መደለያ፤ ማታለያ መፈለግ)
• የራስንና ሰብዕናና ፍላጎት፤ዝቅ አርጎ የሌላዉን ስብዕናና ፍላጎት አጉልቶ መመልከት፡ አድርባይነት
• ወደ ንትርክ፤ ግጭት፤ ጭቅጭቅ ከሚያመሩ ሁኔታዎች መራቅ እንዲያም ሲል ምንም እንዳልተፈጠረ መቁጠር (መደንዘዝ)
በማህበረ ሰባችን ውሰጥ ከላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች አብዛኛዎቹ ወይም ጥቂቶቹ ይታያሉ የሚል እምነት አለኝ ቊጥሩ ሊበዛም ሊያንስም ይችላል ግን ሌላን የመጠበቅ አባዜ ያለብን ለመሆኑ ግን ብዙ መከራከር የሚቻል አይመስለኝም።
አሁን ግን የዚህ አባዜ ጭጋግ መገፈፍ አየጀመረ ነው፡ ሜይ 18 እና 19 ከተደረገው ስልፍም ሆነ ከአበበ ገላው ገድል የምናስቀረው ትልቁ ዘላቂ ጠቀሜታ ማህበረ ሰባችንን አኔን ጨምሮ ማለቴ ነው፤ከዚሁ ከተረጅነት አባዜ/ሌላን ከመጠበቅ አባዜ ማላቀቅ ነው፡፡ ሌላ ካለጠበቅን፤ በግሌ ውጤት ላመጣ እችላለሁ ብለን ካመንን፤ ጠመንጃ ሳይያዝ አምባገነኖችን አንገት መቀንጠስ እንደሚቻል ከአበበ ገላው የምናስቀረው ትልቅ ትምህርት ነው።
አንድ ገሃድ ሃቅ ግን ማንም ልብ የማይለው ቁም ነገር
“ይችን አለም በህይወት የሚሰናበታት የለም፡ ሁሉም የሚሰናበታት በሞት ነው”
አካላዊ ሞት አይቀርም ትልቁ ሞት ግን ለጊዜያዊ አካላዊ ጥቅም ሲባል፤ ወይም ትርጉም በሌለው ፍርሃት ታስረን የህሊና ሞት ስንሞት ነው።
በመጨረሻም፤ አማራ፤ ኦሮሞ፤ ጉራጌ፤ ኦጋዴንያ፤ አፋር፡ ሐመር፡ አኟክ፤ኑዌር፤ጋሙ፤ የም፤ ዳውሮ፤ ህዲያ፤ አገው፤ ወላይታ፤ (ሁሉን መዘርዘር ስለማይቻል ይቅርታ እየጠየቅሁ) እስላም፤ ክርስቲያን፤ ዋቄፈታ፤ … በሚል ተከፋፍለን በየጎጆአችን የትግሬ ነጻ አውጭ ደማችንን እስክጠጣ እንጠብቃለን ወይስ ደማችን ሊጠጣ የተዘጋጀን ሁሉ ባንድ ላይ ተጠራርተን የደም ጠጪዎችን እድሜ እናሳጥራለን?
ደምሽ በትግሬ ነጻ አውጭ እስኪጠጣ ተራ ትጠብቂያለሽ፡ አንተስ የትግሬ ነጻ አውጭ ደምህን እስኪጠጣው ሰልፍ ይዝህ ትጠብቃለህ? ለአቅመ አዳም ያልደረሰች ልጅህን እፊትህ እንደ አለም ደቻሳ ጎትተው ደሟን ሲጠጧት ዝም ብለህ ታያለህ? ወይስ ከዚች ደቂቃ በሗላ የትግሬ ነጻ አውጭ ቡድን የማንንም ደም አይጠጣም ብለህ፤ ከዛሬ በሗላ የትግሬ ነጻ አውጭ ቡድን የኔንም፤ የልጄንም ደም አይጠጣም ብለሽ ትነሻለሽ፤ ትነሳለህ?
መለሱን ላነቺ ላነተ እተዋለሁ፤
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

No comments:

Post a Comment