Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 23 May 2012

ጠቅላይ ሚንስትሩ አንገታቸው ብቻ ሳይሆን ቅስማቸውም ተሰብሮዋል

ዋለልኝ መኮንን | May 23rd, 2012 at 10:28 am | |
ዋለልኝ መኮንን
ባሳለፍነው ሳምንት በዕለተ አርብ አንድ ጠቅላይ ሚንስትራችንንና ደጋፊዎቻቸውን ያሳፈረ ያናደደና ያስቆጣ በሌላው በኩል ደግሞ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያስደሰተ ክስተት በአሜሪካዋ Washington DC ከተማ ተከስቶ ነበረ:: ይህንን ክስተት የኢትዮጵያ ህዝብ ባገኝው የመረጃ ቴክኖሎጅ በመጠቀም ያየነው ምስል ያነበብነው ፅሁፍ የጠቅላይ ሚንስትራችንን መደንገጥ መሸማቀቅ መቆዘም አንገት መድፋት ከመጠን በላይ አስደስቶናል በተቃራኒው ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩ ተንዘራዛሪዎችና ደጋፊዎች እጅግ በጣም እንዴት ተደፈርን እያሉ ሲጮሁ ተስተውለዋል::
የጠቅላይ ሚንስትራችንን መደንገጥ መሸማቀቅ መቆዘም አንገት መድፋት ከመጠን በላይ ያስደሰተው የኢትዮጵያ ህዝብ ደስታውን እየገለፃ ይገኛል:: ብዙሃኖቹ የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡ ተስተውለዋል ተደምጠዋል ተሰምተዋል:: ከተሰጡት አስተያየቶች እጅግ ብዙዎቹ አቶ አበበ ገላውን ጅግና አንበሳውን አይጥ አሳከለው ብለው የሚያወድሱ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትራችን ለካ ወንድ የሚመስሉት በኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥና በውስጡ በሚቀመጡት ሰዎች ላይ ነው ሲሉ ተደምጠዋል:: እንደውም አንድ ጉደኛዬ “ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢሰባዊና ኢፍታዊ ስራቸው ከጋኑ ሞልቶ እየፈሰሰ ስነነበረ አንድ ቀን እንደዚ ጉድ እንደሚሰሩ ስለሚያውቁ የታላላቅ ስብሰባ ጉዞዎቻቸው በሙሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ነበረ ባለፈው አርብ ግን ሀትሪክ ተሰሩ” አለኝ::ምክንያቱም ላለፉት 21 አመታት አንድም የህዝብ አስተያየትና እርምት ተቀበለው አያውቁም እሳቸው ያሰቡትና የተናገሩት ተቀባይነት ካላገኝ አለም ትገልበጥ የሚሉ ናቸው::
አንዱ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩ አትንኩኝ ባይነትና ለብዙ አመታት በውሸት የገነቡት መንግስት በአቶ አበበ ገላው በቅፅበት ዶግ አመድ ሆነ አለኝ:: በአለሙ ህብረተሰብ ዘንድ ጠቅላይ ሚንስትራችን ታታሪ ታማኝና አስተዋይ መስለው ለመታየት እስካለፈችዋ አርብ ድረስ ያልወጡትና ያልወረዱት ተራራ አልነበረም:: በተለይ እስከመቼ በልመና ህዝቦቻቸውን እንደሚያስተዳድሩ የማያውቁትን ብዙ የአፍሪካ መሪዎችን አፍ በማስከፈት የሚታወቁትና ብሎም በትላልቅ የልመና ስብሰባዎች ላይ የሚወከሉት ጠቅላይ ሚንስትራችን ለ 21 አመታት የገነቡት ግድብ መንገድ ትምህርት ቤት ጤና ጣቢያ ከመዘለፍና ከመተቸት አላዳናቸውም:: ይህ ተቃውሞ በምንም መልኩ ተሰልቶ የሚያሳየስ አሁን ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው መንግስት በብዙሀኑ ህዝብ ተቀባይነት ያላግኝ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ህዝቡም ፍትህ ነፃነትና እኩልነት የተጠማ ባገኝው አጋጣሚ ግን እየጮኸ ያለ ጪኸቱም የታፈነ መሆኑን ያሳያል::
ለአየር ከደረሱ አስተያየቶች መካከል ጠቅላይ ሚንስትሩ እስከአሁን ጎበዝ ታማኝና ታታሪ ደጋፊም ሆነ የህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይና የሌሎች ተለጣፊ ድርጅቶች አባላቶች የሉዋቸውም ብሎ ያቀረበው ምክንያትም ደጋፊዎቹም ሆኑ የህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይና የሌሎች ተለጣፊ ድርጅቶች አባላቶች ድሮ ከነበሩበት አዕምሮአዊ መዳበርና የአመለካከት ደረጃ በስንዝር አለመቀየራቸውና ለመቀየር ጥረት አለማድረጋቸው ነው:: ውሸት ሲበዛ እውነት የሚሆን ስለመሰላቸው አይን ያወጣውን የህገ ወጥ ህይወታቸውን መንግስታዊ አሰራራቸውን በግድ ትክክለኛና ህጋዊ ነው ብሎ ለማሳመን ከመጣር አንድ ቀን ሳይቆጠቡ ላለፉት 21 አመታት እራሳቸውን ከመዋሸት አልፈው የኢትዮጵያን ህዝብና የአለሙን ማህበረሰብ እያወናበዱት የህዝቡን ስልጣን ሀብትና ንብረት በጉልበት ነጥቀውታል ዘርፈውታል::ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲሳሳቱ እያዩ እሰይ አበጀህ እያሉ አገራችንንና ታሪካችንን በጠራራ ዕሀይ አስዘረፉን እነሱም ያሻቸውን ዘረፉ:: እንደውም ከተማችን ውስጥ ሆን ተብሎ የህዝብ ወገንተኝነት አላቸው እንዲባል አነዚህ የህዝብና የሃገር ሀብት የዘረፉ ግዙፍ አቅም የፈጠሩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች ለጠቅላይ ሚንስትሩ አንታዘዝም ወደማለት ደረጃ ደርሰዋል የሚባል ውሸት ልክ ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በየመንደሩ እየተወራ ነው::
ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣናትና በሀገርና በህዝብ ሀብት ዘረፋና በጥቅም የተሳሰሩ ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩ ግለሰቦች ቃልቻችን እንዴት ይደፈራል በማለት ቁጣቸውን መቆጣጠር አቅቶአቸዋል:: ሁሉም የወያኔ ባለስልጣናት የተለመደ ቅጥፈታቸውን አሁንም ቀጥለውበት አንዱ አይኔን ግንባር ያድርገው ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ሲል ሌላው ደግሞ የሀያሉ የአሜሪካን መንግስት መሪ ላይም ጫማ ተወርውሮባቸው የለ! ብሎ ጠቅላይ ሚንስትሩና አጫፋሪዎቻችው ላይ የተወረወረውንና የአቶሚክ ቦምብ ያህል ያቆሰላቸውን የአቶ አበበን ተገቢ የሆነ የጀግንንት ስራ ለማጣጣል ሞከር አድርገው ነበረ አልተሳካላቸውም::
በመጀመሪያ የVOA(voice of America) የዜና ዘገባ ብዙ ከሀገር ውጭ መረጃ የማግኝት እድልና አማራጭ ላልነበራቸው ኢትዮጵያውያን ብሎም ትክክለኛውን በጠቅላይ ሚንስትሩ የደረሰውን ክስተት በስልክና በኢንተርኔት መልክት ለሰሙ ሰዎች እጅግ ግራ ያጋባ ነበረ ግራ ከማጋባትም አልፎ በውጭ ሀገር የሚገኙትን እውነተኛና ሚዛናዊ የመረጃ ምንጮቻቸውን እስከመጠራጠር ደርሰው ነበር:: ዘጋቢያቸው በስብሰባው ላይ የተከሰተውን በጠቅላይ ሚንስትሩ የደረሰውን ትክክለኛ ክስተት መዘገብ ከሙያ ግዴታ ሆነ ድርጅቱ ከተቃቃመበት አላማ አንፃር አይን ያወጣ ስህተት ነበረው:: ለምን መደባበቅ እንደፈለገና እውነተኛውን እንዳልዘገበ መልሱን ለራሱ ለዘጋቢውና የህንን አይን ያወጣ ቅጥፈት ለተከታተለና ለታዘበ የኢትዮጵያ ህዝብ ትቼዋለው::አገር ውስጥ ያለችም አንዲት ተንዘራዛሪና ህዝብን እያደነቆረች ያለች ሴቲዮ(Mami) አቶ አበበ ገላውን ለመተቸት ሙከራ ማድረጋን ሰምቼ እንዴት ነደደኝ መሰላቹ:: ሴትየዋ ለነገሩ ያልሞከረችው ስራ የለም ነበረ ስላልተሳካላት ግን በስለላና የህዝብን የአመለካከት አቅጣጫ በማስቀየር የምትተዳደር እንደሆነች ዐሀይ ካሞቀባት ሰነበተ:: እንደዚ አይነት ሰዎች ባለ ሁለት ስለት ቢላ ይባላል ነገም ሌላ ቦታ የሚበላ ካገኙ መለያ መቀየር ብቻ ነው::
እንደውም ጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ የመሳቀቅ የመቅበዝበዝና አንገት የመድፋት አደጋ ከደረሰ በሃላ ለያዝ ለገላጋይ ያስቸገሩት አንዳንድ በነፃው የውድድር አለም ውጤታማ መሆን ያልቻሉና ያልተሳካላቸው ዘርዛሮችና ሌሎችም በራስ መተማመን ያቃታቸውና ሆዳቸው አምላካቸው ተሆኑ ግለሰቦች ነበሩ:: እነዚህ ግለሰቦች የህዝብን ድምፅ ለማፈን ለሰሩት ለወደፊቱ በውለታ ከሚያገኙት ጥቅም በተጨማሪ በወያኔ መንግስት ሙሉ ወጪያችው ተሸፍኖላቸው ለወያኔ አባላቶችና ደጋፊዎች ለፖለቲካ ቅስቀሳ የምትጠቅምና አገር ቤት ለሚገኙ ከመንግስት የመረጃ ተቃማት ውጭ ምንም አማራጭ ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን ለወሬ ፍጆታ የምትሆን ትንሽ የድጋፍ ሰልፍ ብጤ አዘጋጅተው እንደነበረ በወሬ ደረጃ ተሰምቶአል:: እንደውም አንዱ ምን አለ መሰላቹ መጀመሪያ የወያኔን ማልያ ለብሼ ብሬን ከነከስኩኝ በኻላ መለስን ስቃወም ዋልኩኝ ብሎ ቅሌቱን በአደባባይ አናፈሰው::
በጣም የሚያስቀውና ከስህተታቸው መማር አለመፈለጋቸውን ገሀድ ያወጣባቸው በጉልበት አገርንና ህዝብን እያስተዳደረ ያለው መንግስትና በተጨማሪም ጥቂት የጠቅላይ ሚንስትሩ ደጋፊዎች የህወሀት አባላቶችና የወያኔ ተለጣፊ ድርጅቶች አባላቶች ጠቅላይ ሚንስትሩ የደረሰባቸውን አደጋ ለመሸፋፈን ያደረጉት ጥረት ነበር:: በመጀመሪያ የፈፅሙት ደባ አቶ አበበ ገላው ጠቅላይ ሚንስትሩን ልክ ልካቸውን ሲነግራቸውና አንገታቸውን ሲደፉ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አገር ቤት እንዳይታይ ባደራጁአቸው የመረጃ መረብ ጠላፊ ድርጅቶች እንዲታፈን ማድረግ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ልክ እንደተለመደው በኢትዮጵያ ቴሌቤጅንና ራዲዮ ጠቅላይ ሚንስትሩ የ ስብሰባ በተሳካ ሁሌታ እንደፈፅሙ የሚናገር ተራ የውንብድናና የማጭበርበር ዜና ከኢትዮጵያ ቴሌቤጅንና ራዲዮ ውጭ ሌላ የመረጃ አማራጭ ለሌለው አገር ቤት ላሉት ኢትዮጵያውያን መለፍለፍ ነበረ::
የወያኔ መንግስት በአንድ በኩል የመረጠኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው እያለ በሌላ በኩል የኢትዮጵያን ህዝብ ምንም አይነት ትክክለኛ መረጃና የመረጃ አማራጭ እንዳያገኝ ለማድረግ የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችን በገፍ አስገብቶ ማፈኑንና ማጭበርበሩን ተያይዞታል:: በሀገራችን በአሁኑ ሰአት መንግስትን በአደባባይ መቃወም አይደለም ሌሎች ወገኖቹ ወያኔን ሲቃወሙ መስማትም ማዳመጥም ማንበብም ማየትም በህግ ተከልክሎዋል:: አሁን ወያኔ የቀረው የማፈኛ መንገድ የመረጃ መረብን(Internet) ልክ እንደ ግንቦት 7ና ኦሮሞ ነፃነት ግንባር አሸባሪ ነው ብሎ በህግ ደረጃ በአሻንጉሊቱ ፓርላማ ማኖ አስነክቶ ማፅደቅ ነው::

No comments:

Post a Comment