Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday 22 May 2012

አቶ መለስ በገጠማቸው ተቃውሞ አንገታቸውን ደፉ


 - ጋዜጠኛ አበበ ገላው አቶ መለስ ላይ ተቃውሞ ሲያቀርብ የሚያሳየው የዩቲውብ
- የቪዲዮ ምስል ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታይ ተደርጓል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች
- ስለጉዳዩ የደረሰኝ መረጃ የለም ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
- እንዲህ አይነት ነገር ያጋጥማል አቶ በረከት ስምኦን

/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአሜሪካን አገር በገጠማቸው ድንገተኛ ተቃውሞ ከፍተኛ ድንጋጤ እንደፈጠረባቸውና አንገታቸውን መድፋታቸውን የተለያዩ ድረገፆች ዘገቡ፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ስለጉዳዩ የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ ሲናገሩ፤ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን፣ በአቶ መለስ ላይ የተፈፀመውን ክስተት እውነትነት ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አረጋግጠዋል፡፡ የተለያዩ ድረገፆችና ማህበራዊ ሚዲያዎች በምስል በማስደገፍ ካሰራጯቸው መረጃዎች መረዳት እንደተቻለው ፕሬዝደንት ኦባማ በአሜሪካን በካምፕ ዴቪድ ሬገን ማዕከል ባዘጋጁት በምግብ ዋስትና ላይ የሚመክረው የቡድን ስምንት ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ተናጋሪ ከነበሩት አራት መሪዎች መካከል አቶ መለስ አንዱ ነበሩ፡፡ ሦስቱ መሪዎች መልዕክታቸውን በአግባቡ ያስተላለፉ ሲሆን አቶ መለስ ተራ ደርሶአቸው ንግግር ሲጀምሩ ያልተጠበቀና አስደንጋጭ የተቃውሞ ድምጽ ሲቀርብባቸው በፊታቸው ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ታይቷል፡፡
በስብሰባው አዳራሽ ፊት ለፊት የተቃውሞና የድጋፍ ሰልፍ ታይቷል፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን አቶ መለስ በዚያ ስብሰባ ላይ መገኘታቸውን በማውገዝ የተቃውሞ ሠልፍ ያደረጉ ሲሆን ጥቂት ደጋፊዎቻቸውም ለድጋፍ ሰልፍ ወጥተው እንደነበር
ዘገባዎቹ ያሳያሉ፡፡ ይህን ሰልፍ አልፈው ወደ አዳራሹ የገቡት አቶ መለስ፤ የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ማህበር አባል የሆነው ጋዜጠኛ አበበ /ሚሩ የጀመሩትን ንግግር አቋርጦ ተቃውሞውን በድንገት አሰምቷል፡፡ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ከአዳራሽ ከወጣ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ማብራሪያ እንደገለፀውወደ አዳራሹ ከመግባታችን በፊት /ተንሳኤ ተስፋዬ በርሄ የተባለ የአቶ መለስ ጠባቂ ወደ እኔ ቀርቦሀበሻ ነህ እንዴ?› ብሎ ጠየቀኝ፡፡ ምን አገባህ? አልኩትአይ ኢትዮጵያዊ መስለህኝ ነውአለኝ፡፡ አይደለሁም አልኩት፡፡ ኢትዮጵያዊ የምሆነው በአገሬ ውስጥ በነፃነት መኖር ስችል ነው አልኩት፡፡ሄደህ ስላላአላየህ
ነው እንጂ አገሪቱ ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡ እናንተ እዚህ ሆናችሁ ዝም ብላችሁ ትጮሃላችሁአለኝ፡፡ አንተ የመጣኸው ጌታህን ልትጠብቅ ነው፡፡ እኔ የመጣሁት ደግሞ እውነት ልናገር ነው አንገናኝም ብዬው ጥዬው ሄድኩኝብሎአል፡፡ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ቀጥሎ ሲናገርምአቶ መለስ መናገር ሲጀምሩ እንድናገር እድሉን ባላገኝም ያገኘሁትን ዕድል በመጠቀም አቶ መለስን አጋልጫአለሁ›› ብሏል፡፡ ጋዜጠኛ አበበ ገላው በመጀመሪያ የአቶ መለስን ስም ጠርቶ ሶስት ጊዜ ‹‹…አምባገነን ናቸው፡፡›› ካለ በኋላ እስክንድር ነጋና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ በማለት ጠይቋል፡፡ ቀጥሎም መለስ ነፍሰ ገዳይ ናቸው የሚል ወቀሳውን አቅርቧል፡፡ ያለ ነፃነት የምግብ ዋስትና የሚል ይዘት ያለው አቋሙንም በአዳራሹ አስተጋብቷል፡፡‹‹ ነፃነት! ነፃነት! ነፃነት!›› በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰምቷል፡፡
የጋዜጠኛ አበበ ገላውን ንግግር ፕሬዝዳንት ኦባማና የአሜሪካን ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም የተቀሩት የቡድን ስምንት ሀገራት መሪዎችና ተሰብሳቢዎች በጠቅላላ በትኩረት ተከታትለውታል፡፡ ‹‹ለእኔ ትልቅ ቀን ነው፡፡ የአቶ መለስን ውሸት
ያጋለጥኩበት ነው፡፡ ከእንዲህ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አቶ መለስን እርቃናቸውን ማስቀረት አለብን፡፡ በእርግጥ እርቃናቸውን የቀሩ ሰው ናቸው፡፡›› ብሎአል፡፡ ዜጠኛ አበበ ገላው ተቃውሞውን ከገለፀ በኋላ የነበረውን ሁኔታ ሲያብራራንግግሬን እንደጨረስኩ የአሜሪካን ሴኪውሪቲ ሰዎች ፖሊሶችን ጠሩ፡፡ አራት ፖሊሶች መጥተው ወደ አንድ ጥግ አሲዘው ጠየቁኝ፡፡ምንድነው ያልከው?› አሉኝ፡፡ _______ምንም አላልኩም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፀመውን በደል ነው ያጋላጥኩት አልኳቸው፡፡ መንጃ ፍቃዴን ተቀብለው ተመለከቱ፡፡ ከፈለጋችሁ እሰሩኝ አልኳቸው፡፡ አይ አናስርህምአሉኝ፡፡ እንደያውም አንዱ ፖሊስእኔ
ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር፡፡ ምን እንደሚሰራ አውቃለሁ፡፡ የተናገርከው ነጥብ አለውበማለት ጀርባዬን መታ መታ አድርጐኛል፡፡ሲል ተደምጧል፡፡ በመቀጠልምከስብሰባው እንደወጣሁ የአቶ መለስ አጃቢጠብቅ እንገልሃለንብሎኛል፡፡ ይህንኑ ለፖሊሱ ነግሬዋለሁ፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ ከአርብ ለሊት ጀምሮ ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች እንዳመለከቱት ጋዜጠኛ አበበ ገላው አቶ መለስ ላይ ተቃውሞ ሲያቀርብ የሚያሳየው የዩቲውብ የቪዲዮ ምስል ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታይ ተደርጓል፡፡
በካምዴቪድ ስለተፈጠረው ሁኔታ እንዲያስረዱ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የጠየቀቻቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ስለ ጉዳዩ የደረሳቸው ምንም አይነት መረጃ እንደሌ ገልፀዋል፡፡ ፍኖተ ነፃነት በመቀጠል ስለክስተቱ እንዲያብራሩ የጠየቀቻቸው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን፣ በአቶ መለስ ላይ የተፈፀመውን ክስተት አምነው፣ ‹‹እንዲህ አይነት አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ›› ካሉ በኋላ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዳልሰጠው ተናግረዋል፡፡ ክስተቱን የሚያሳየው የዩቲውብ መስመር እንዳይታይ ያደረገው እገዳ እንዳልነበረም ገልፀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment