Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday 21 May 2012

በጋሞጎፋ ዞን የሚገኙ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ከፍተኛ ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገለጡ

ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የመንግስት  ባለስልጣናት በፈጠሩት ችግር ለዘመናት  አብረው የኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች እርስ በርስ ለመጋጨት ተፋጠዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጠዋል።
የደምባ ጎፋ ወራዳ አስተዳዳሪና ምክትል አስተዳዳሪ ሰሞኑን ወደ ዛንዳ  ቀበሌ በመሄድ ግጭት ለመፍጠር መሞከራቸውን አንድ የአካባቢው ተዋቂ አዛውንት ተናግረዋል::
አዛውንቱ በአካባቢያቸው ያለው ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንም ይገልጣሉ ። እርሳቸው እንደሚሉት ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ የሚማሩ ተማሪዎች የኢህአዴግ አባል ካልሆኑ ለመማር በማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል::

No comments:

Post a Comment