Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday 22 May 2012

መለሰን አየነው፤ታደለ መኩሪያ

 አነበሣ ገላለሁ ይለን የነበረው፣
ዘሆን አድናለሁ ሲለን የነበረው፣
ነብር አጠምዳለሁ ሲለን የነበረው፣
ጣቶችን ቆርጣለሁ ሲለን የነበረው፣
የደደቢት ጀግና የፓርላማ አቶራ፣
የአጋዚን ሠራዊት በሆዱ የገዛ፣
ሲያገሳ የኖረ እንደ ዳልጋ አንበሣ፣
ከኔ ሌላ ጅግና አይኖርም እርም ነው፣
ለሃያ ዓመታት ሲለን የነበረው፣
በፍርሃት ተውጦ መለሰን አየነው።
የአበበ ገላውን ድምጹን በመስማቱ፣
መለሰ ዜናዊ ተደፋ ካናቱ።
በትዕቢት ተሞልቶ ሰማይ ላይ ቢሰቀል፣
እንደወጣ አልቀረም ተመለሰ ከምድር።
መለሰ ዜናዊ ከእንግዲህ ታሪክ ነው፣
ተሟጧል ሕይወቱ ያለው በድኑነው።

No comments:

Post a Comment